TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፃፈ።

ፓርቲው በዚህ ደብዳቤው ፤ " የፓርቲ አባል ያልሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች በብልፅግና ፓርቲ ስልጠና እንዲሳተፉ የሚደረግበት አሰራር እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

ነእፓ ፤ #የመንግስት እና #የፓርቲ መደበላለቅ በለውጡ ማግስት መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን በተለይ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ብሏል።

ከቅርብ ወራት ጀምሮ ገዢው ፓርቲ እያካሄደ ባለው የአባላት ስልጠና፣ የፓርቲው አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች (Public servants) የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው ሲል አስረድቷል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ በተለያየ መንገድ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል።

ይባስ ብሎ በየአካባቢው እየተካሄዱ ያሉ ስልጠናዎች ፦
- አበል፣
- ትራንስፖርት፣
- ሆቴል እና ሌሎች የስልጠና ወጪዎች የሚሸፈኑት #በመንግስት_በጀት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ብሏል።

በመሆኑም የፓርቲ አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች የገዢውን ፓርቲ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ ህገ መንግስቱን እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ስርአት አዋጃ ቁጥር 1162/2011 የሚቃረን በመሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ድርጊቱ ይቆም ዘንድ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድም አሳስቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት፤ ገዢው ፓርቲ የስልጠናና ሌሎች ድርጅታዊ እንቅስቃሴውን በመንግስት ሀብት የሚሸፍንበት አሰራር ህግ እና ስርአትን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የፖለቲካ ሜዳውን የሚያዛንፍ በመሆኑ፣ ድርጊቱ ይታረም ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በተለይም ፦
- የምርጫ ቦርድ፣
- የገንዘብ ሚንስቴር
- የክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮዎች፣
- በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤቶች አዋጁን በማስከበር ገዢው ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሩን ከመንግስት መዋቅር ለይቶ እንዲሰራ ኋላፈነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia