TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ራያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፣ መቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ፤ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹን ይቀበላል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ዓዲግራት፣ ራያ፣ ኣክሱም) ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንደሚመለሱ አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት በክልሉ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ራያ ዩኒቨርሲቲ ከትላንት ጀምሮ ነባር ተማሪዎችን በመቀበል ምዝገባ መጀመሩን አሳውቀውናል።

መቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ነባር ተማሪዎቻቸውን መቀበል እንደሚጀምሩ የገለፁልን ዶ/ር ሰለሞን፤ የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቀውናል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነት መጎዳቱ የመዘግየቱ ምክንያት መሆኑን አስረድተውናል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ ተማሪዎችን መሆኑን ዶ/ር ሰለሞን ገልጸውልናል።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያሉ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 2016 ዓ/ም ጀምሮ #ሙሉ_በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገቡ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በላኩልን መልዕክት አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ
=================
ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ አስቀድመው መቆጠብ እንዲችሉ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡

ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ ከብር 1,000 ጀምሮ ይከፈታል፡፡

የቁጠባ ሂሳቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

• ቆጣቢዎች በሀገር ወስጥ ጉዟቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ለአየር ትኬት፣ ለቱሪስት መዳረሻዎች መግቢያ፣ ለሆቴል አገልግሎት እና ለመሳሰሉት ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት ተመላሽ ያገኛሉ፤

• ዳያስፖራ ወይም የውጭ ሀገር ዜጎች የሲቢኢ ቱሪስት ካርድን ሲጠቀሙ እስከ 7 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ ፤

• ለሀይማኖታዊ ጉዳይ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞች ከአየር ትኬት ክፍያቸው እስከ 3 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ፤

• ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችንም ያስገኛል፡፡

ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!
ይቆጥቡ፤ ይጓዙ!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#forfreemarket

አስፈላጊ ምርቶች  ፤ ተመጣጣኝ_ዋጋ

ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን⤵️
https://publielectoral.lat/forfreemarket

አነስተኛ የልብስ እና ጫማ ማጠቢያ
👉ለጫማ ቢሉ ለልብስ ቦታ የማይዝ
👉 ለፓንት ቦክሰር እና ካልሲ
👉ለ ቲሸርት ሁነኛ ተመራጭ
 👉ለዳይፐር

🏢 አድራሻ 👉 ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ
📲 0911255787
📲 0983360606
ጥራት መለያችን ነው
OnLineShopping
    
#Oromia

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ የ8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደ ክልል የሚካሄድ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቶላ በሪሰ ገልጸዋል

የ8ኛ ከፍል ፈተናን በተመለከተ 490,167 ተማሪዎች እንደሚወስዱ (ከዚህም ውስጥ ወንድ 260,807 እና ሴት 229,360 ናቸው) ገልጸው የ8ኛ ክፈል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ሰኔ 26 እና 27/2015 መሆኑን አሳውቀዋል።

የ12ኛ ክፈል ብሄራዊ ፈተናን አስመልክቶ በክልሉ 323,149 ተማሪዎች ለፈተናው እንደሚቀመጡ ገልጸው የፈተና ፕሮግራሙን እንደሚከተለው አብራርተዋል።

የፈተናው ፕሮግራም

👉 ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች

- ሐምሌ 16 -17 / 2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

- ሐምሌ 18 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል።

- ከሐምሌ ከ19 - 21/2015 ፈተናው ለ 3ት ቀናት ይሰጣል ።

- ሐምሌ 22-23/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

👉 ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፦

- ሐምሌ 22 -23/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

- ሐምሌ 24/2015 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል።

- ከሐምሌ 25 -28/2015 ፈተናው ለአራት ቀናት ይሰጣል።

- ሐምሌ 29-30/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

ለ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎች ስኬት ሁሉም ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሚያ ክልል ት/ቢሮው ሀላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ በሁሉም አቅጣጫ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ምንጭ ፦ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ

More : @tikvahethafaanoromoo

@tikvahethiopia
#Update

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወንደወሰን ኢየሱስወርቅ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ከተመዘገቡት ውስጥ 503,812 ተማሪዎች የሶሻል ሳይንስ እና 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ #ኢፕድ

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#ቮልስዋገን

" ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዷል " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

ወደ ኢትዮጵያ ከሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መካከል በቻይና ሀገር ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጲያ እየገባ የሚገኘው " ቮልስ ዋገን " የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ህጋዊ የሆነ ፍቃድ የሌለው መሆኑን የጀርመን ኩባንያ በኢንባሲው በኩል ለትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ይህ ቻይና ሀገር የሚመረተው የ " ቮልስ ዋገን " የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከኩባንያው ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን ሚኒስቴሩ ዛሬ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የቪዛ ካርድዎን ከአቢሲኒያ ባንክ በ72 ሰዓታት ውስጥ ይረከቡ! ልክ እንደጊዜው አገልግሎታችንም ፍጥነትን ከጥራት ያሟላ ነው!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #VISA #ATMcard #poweredbybankofabyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
የንብረት ግብር . . . " ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት የንብረት ግብር ተከራይን የማይመለከትና ወደ ተከራይ መተላለፍ የሌለበት መሆኑን ማወቅ አለባቸው " - የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ነዋሪዎች ስለ ንብረት ግብር ምን አሉ ? " የኑሮ ውድነቱ ከብዶ ባለበት ሁኔታ ግብሩ መሻሻሉ የመጨረሻ ጫናው ተከራዮች ላይ እንዳያርፍ ያደርጋል። መንግሥት ገበያውን መቆጣጣር አለበት። ግብርን መክፈል የሥልጣኔ መገለጫ…
የቤት ግብር . . .

" የከፈልኩት ክፍያ አሰራሩን የጣሰ ነው "

የአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አስቻለው ጣሰው (በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተናገሩት)  ፦

" የምኖረው ቦሌ ክፍለ ከተማ ነው።

በወረዳ 14 የታዘብኩትን መናገር እፈልጋለሁ።

እኔ የሚጠበቅብኝን የ ' Property Tax ' ከፍያለሁ ነገር ግን የከፈልኩት ክፍያ አሰራሩን የጣሰ ነው።

ታክስ የመክፈል የዜግነት ግዴታዬ ነው ፤ መጀመሪያ መመሪያውን አይቼ ነው ልከፍል የሄድኩት።

መመሪያው ሰርኩላር የተደረገው ሚያዚያ 7 /2015 ነው። እዚህ መመሪያ ላይ ሂሳቡ የሚሰራበት ቀመር አለ እሱን እስልቼ ነበር የሄድኩት ነገር ግን እዛ ወረዳ ላይ ያየሁት ነገር ከ1000 እስከ 1500 በላይ ምኑንም ያላመላከተ፣ ከመመሪያውም ጋር ያልተናበበ ክፍያ ሰዎች እንዲከፍሉ ይደረጋል።

ይሄ ከተመን በፊት ያለ ነው።

ለምሳሌ ፦ እኔ ካርታዬን ' ዲጅታል ' አስደርጊያለሁ ፣ ዲጂታል ሳስደርግ የመሃንዲስ 1500 ብር ከፍያለሁ ነገር ግን በዚህ ወቅት እንድከፍል የተደረገው መሃንዲስ ስሙ ተጠርቶ ብቻ 500 ብር የመሃንዲስ፣ ፋይሌ ወጥቶ ክፍያ ለምፈፅምበት 500 ፣ እንደገና ቅጣት ተብሎ 500 ፤ ቅጣት  የአፈር እና የጣራ ግብር የሚባለው ከሆነ ኮንዶሚኒየሞች በዚህ ሲስተም ሲስተናገዱ አልነበረምና ኮንዶሚኒየሞች በምን ታይቶ ነው ከየካቲት አንድ ጀምሮ ሲስተሙ ቅጣት 5 % እየሰራ የሚሄደው ?

ከዚህ በፊት ተግባራዊ ያልተደረገባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች / ኮንዶሚኒየም ላይ እንዴት በመኖሪያ ቤቶች አሰራር እዛ ላይ ተግባራዊ ተደረገ ? ይሄ ቅጣት ሚያዚያ ላይ በወጣ ሰርኩላር  እንዴት ከየካቲት ጀምሮ ሰው ይቀጣል ?

እንደገና ለመክፈል የሄደ ሰው ፋይሉን ከፋይል አውጥቶ፣ አምጥቶ ክፍል ላለው ሰው እንዴት ፋይል ለወጣበት አገልግሎት ተብሎ 500 ብር ለምንድነው ?

ቀመር የተሰራበትን ተቀበለ አብዛኛው በዝቶብናል አስተያየት ይደረግልን ቢልም ግን አብዛኛውን ህዝብ የማተራመስ በፕሮግራም ያለመጥራት ነገር አለ።

ለምሳሌ ወደ ገርጂ ብዙ የኮንዶሚኒየም ሳይቶች አሉ ፤ እንደውም ሰው ሃሳብ ሲሰጣቸው ምናለ ሳይቶቹን በፕሮግራም አድርጋቹ ብትጠሩን ለአሰራር ለናተም ያመቻል ህዝቡም እንዳለ ከሰኞ እስከ አርብ ሲተራመስ አይውልም ምናለ ፕሮግራም አውጥታችሁ ብታስተናግዱን ? እያለ ይጠይዋል ህዝቡ።

የኔን ያለአገባብ ክፍያ ያየ ጓደኛዬ ክፍለ ከተማ ሄዶ 500 ብር ብቻ ከፈለ። ተመልከቱ ክ/ከተማውን እና ወረዳዎች በምን ደረጃ ነው የሚናበቡት ? ቦሌ እና ለሚ ኩራ የሚያስከፍሉት ይለያያል 100 ብር ከፍለን ያሉ አሉ። እዛው ወረዳ 14 እና 13 እራሱ ወረዳ 13 100 ብር ሲያስከፍል ወረዳ 14 1000 ብር ያስከፍላል ይህ አገልግሎት ለሚባለው ነው ቅጣቱን ተውትና።

ሁሉም ቦታ የአገልግሎት እያሉ ይቀበላሉ፤ ግን ወጥ አይደለም ። ለምን ጉራማይሌ ሆነ ? አንዱ ጋር መቶ ሌላው ጋር ሌላ በተለይ የመሃንዲሱ ብቻ 500 ፣ የአገልግሎት 500 እኔ ደረሰኝ ይዤ ነው ይሄንን የምናገረው።

አፈፃፀሙ ላይ ሰዎች ቅር እያላቸው ባላመኑበት ሁኔታ ላይ ተገደው የመክፈል ሁኔታ አለ። ከምንገላታ በሚልም ... አንድ ሰው በጣም ፈጠነ ከተባለ 3 ቀን ነው የሚፈጅበት እኔ 3 ቀን ከመ/ቤት አስፈቅጃለሁ ይሄንን ጉዳይ ለመፈፀም።

ልገብር ብሎ የሚሄድ ሰው ሶስት ቀን ከስራው ቀርቶ አስቡት።

እናስተካክላለን ይላሉ ፤ እሺ የከፈሉ ሰዎች ጉዳይ ምን ይደረጋል ? ሌላው የባንክ እዳ ያለባቸውና ካርታው ባንክ የሆናባቸው አሉ አሁን እነዚህ ሰዎች ሙሉ ባለቤት ነን አይሉም የባንክ እዳ እየከፈሉ ነው ይሄስ እንዴት ነው የሚታየው ?

ኮንዶሚኒየም እና የማህበር ቤቶች በጣም ልዩነት አለው ፤ የማህበር ቤቶች ሲሰሩበት ኖረዋል የአፈር እና የጣራ ግብር እየተባለ አሁን የዛ Update የሆነ ነው እየተባለ ነው ፤ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ የኮንዶሚኒየም በዛ ህግ መገዛት አለበት ወይ ? እሺ በህጉ ይገዛ ከዚህ በፊት ባልከፈለበት ሁኔታ ቅጣት የሚባለው ለምን ጨመረ ?

ህዝቡ በአሰራሩና በፕሮግራም አልባነቱ እያመረረ እየተንገላታ ነው። ለመክፈልም ሄዶ መንገላታት በጣም አለ።

ወጥ የሆነው አሰራር ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የለም ፤ በራሳቸው በክ/ከተሞች መካከል ተመሳሳይ አከፋፈል የለም ፤ ከአንድ ቢሮ የሚወጣ ከሆነ አሰራሩ ወጥ ሊሆን ይገባል። "

በአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አማካሪ ዶ/ር ፈቀደ ተረፈ ፦

" አንዳንድ ቦታዎች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ተብሎ የተነሳውና መሃንዲስ እንዲሁም የፋይል ተብሎ የተቀመጠው በአሰራር ውስጥ የለም። ይሄ መከፈል የለበትም ይሄ በአሰራር ውስጥ ስለሌለ መከፈል የለበትም።

ከህብረተሰቡ የሚነሱትን ቅሬታዎች እያስተካከልን እንሄዳለን። "

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT
የጣሪያና ግድግዳ ግብር . . .

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ፤ የጣሪያና ግድግዳ ግብርን በተመለከተ ዛሬ ለግንዛቤ በሚል አንድ መረጃ አሰራጭቷል።

በዚሁ መረጀው ፤ " መንግስት በሚያለማው መሰረተ ልማት እና የህግ ማሻሻያ ምክንያት በመሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው (Value) ይጨምራል " ያለ ሲሆን " መሬትና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው በመጨመሩ ምክኒያት የአከባቢ መንግስታት የሚሰበስቡት ገቢ የቤት ግብር ወይንም የጣራና ግድግዳ ግብር በመባል ይታወቃል " ሲል አስረድቷል።

የጣሪያና ግድግዳ ግብር የሚሰበሰበው ፦

- ከጣሪያና ግድግዳ ግብር የሚሰበሰበው ገቢ መሰረቱ የተረጋጋና አስተማማኝ የገቢ ምንጭ በመሆኑ፣

- የማይለዋወጥና የማይሰወር የግብር አይነት በመሆኑ፣

- ለቁጥጥር አመቺና ከታክስ ለመሸሽ የማይመች የግብር መሰረት በመሆኑ፣

- ለከተሞች የመሰረተ ልማት እድገት የጀርባ አጥንት እንዲሁም ለከተሞች መሰረታዊ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ፍላጎት የሚያሟላ በመሆኑ

- ከፋዮች በከፈሉት ልክ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑ ነው ብሏል።

ቢሮው ፤ የጣራና ግድግዳ ግብር በአገራችን በህግ በተደገፈ በዘመናዊ መልኩ መተግበር የጀመረው በ1937 ዓ.ም ነው ብሏል።

በመጀመሪያው በከተማ ውስጥ የንብረት ግብር ይጣል የነበረው በማናቸውም የማይንቀሳቀስ ንብረት በመሬትና በህንፃዎች ላይ ነበር ሲል አስታውሷል።

ሁለተኛው በከተማ መሬት ኪራይና በከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሆኑን ገልጾ በአዋጁ አንቀጽ 6 መሰረት የጣሪያ ግድግዳ ግብር ዓመታዊ የቤት ኪራይ ግምት መሰረት በማድረግ  እንደሚሰበሰብ አመልክቷል።

ሶስተኛው " የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 49 መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጣን ይዘት እና ወሰን ለመደንገግ በወጣው የፌደራል ቻርተር አዋጅ 361/1995 መሰረት በከተማው ውስጥ የከተማ ቦታ ኪራይ እና የቤት ግብር ይወስናል ይሰበስባል ይላል " ሲል አስረድቷል።

እንደ ኮሚኒኬሽን ቢሮው መረጃ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ይኖራሉ ተብሎ የሚገመተው 1,020,528 መኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ የግል ቤቶች 891,628 ቤቶች እንደሆኑ ይገመታል። ከነዚህ መካከል ግብር እየከፈሉ ያሉት 182,842 ባለይዞታዎች እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን የከፋዮች ቁጥር ማነስ ብቻ ሳይሆን የሚሰበሰበውም ገቢ በጣም አነስተኛ ነው ተብሏል።

" የክፍያ ጫናውን ለማቅለል ሲባል የዚህ ዓመት ክፍያ ያልከፈሉ የቤት ግብር ከፋዮች በጥናት በተለየው የአንድ ሜትር ካሬ የቤት ስፋት ወርሀዊ ኪራይ ግምት ወይም ዓመታዊ የኪራይ ግምት መጠንን ለመኖሪያ ቤት በ50% እና ለመሥሪያ ቤት ደግሞ በ75% ላይ ብቻ ግብሩን በማስላት እንዲከፍሉ ይደረጋል " ሲል የከተማው ኮሚኒኬሽን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
(ኢትዮ ቴሌኮም)

ቢዝነስዎን ከጊዜው ጋር ለማራመድ ኢንተርኔት፤ ስራዎን ለማሳለጥ ፈጣን ግንኙነት የግድ ሆኗል!

እኛም ለመፍትሄው ከጎንዎ ሁሌም አለን በገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እስከ 53% ቅናሽ አድርገን በተለያዩ አማራጮች ማቅረባችንን  ስንገልጽ በልዩ ደስታ ነው!

አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ በሚገኝ የቢዝነስ አገልግሎት ማዕከላችን ጎራ ይበሉ!
#ትግራይ

" እስካሁን ወደ ህግ የቀረቡት 7 ብቻ ናቸው " - ግብረ ኃይሉ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰረቀ የሰብዓዊ እርዳትን ለማጣራት ያቋቋመው ግብረ ኃይል እስካሁን ሲሰራቸው የቆዩትን ስራዎች በተመለከተ ለክልሉ ቴሌቪዥን ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም ወቅት በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ በኤርትራ ኃይሎች፣ በፌዴራል እና በትግራይ ክልል መንግስታት መዋቅር ዝርፊያ መፈፀሙን ለማወቅ ችሏል።

በተጨማሪም በግብረሰናይ ድርጅቶች ፣ የተፈናቃይ ወገኖች አስተባባሪዎች ለሰብዓዊ እርዳታ የመጣ ድጋፍን መዝረፋቸውን የሚያመላክት ማስረጃ ተገኝቷል።

የተዘረፈው ዘይት፣ ስንዴ፣ ክክ እና ሌሎች ድጋፎች ናቸው።

እስካሁን በተሰራው የማጣራት ስራ የኤርትራ ሰራዊት በሽራሮ 28,880 ኩንታል ስንዴ መዝረፉ፣ 43,200 ሊትር ዘይት፣ አተር ክክ 1440 ኩንታል መዝረፉን ግብረኃይሉ አሳውቋል። ይህ ኃይል የዘረፈውን ዘርፎ የተቀረውን እንዲባክን አድርጓል።

የፌዴራል መንግስት " አስተዳደር ብሎ ያስቀመጣቸው አመራሮች " 43,196 ኩንታል ስንዴ፣ 129,585 ሊትር ዘይት ፣ 4,184 ኩንታል የአተር ክክ እንደወሰዱ በጥናት ተረጋግጧል።

በትግራይ መዋቅር 14, 317 ኩንታል ስንዴ፣ 42,759 ሊትር ዘይት፣ 1,424 ኩንታል የአተር ክክ መዘረፉን ለማረጋገጥ ተችሏል።

እንደ ግብረ ኃይሉ መረጃ እስካሁን በክልልና በዞን ለማጣራት እንደተቻለው ከፌዴራል መንግሥት መዋቅር፣ ከትግራይ ክልል መንግሥት መዋቅር፣ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም ከተፈናቃይ ወገኖች አስተባባሪዎች እስካሁን 186 ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ በማጥፋት ተሳታፊ ሆነው መገኘታቸውን ለመወቅ እንደተቻለና 7 ሰዎች ወደ ህግ እንዲቀርቡ መደረጉን አሳውቋል።

የተጀመረው የማጣራት ስራ ገና የሚቀጥል ሲሆን በየጊዜውም መረጃውን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopia