TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

ስልካችሁን በመጠቀም የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የሚጠበቅባችሁ ቀላል መመሪያዎች!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#Safaricom

ቀናችንን በSamsung Galaxy S23 Ultra ፈካ እናድርግ። ጥራት ያለው ፕሮሰሰሩ እና ፍንክች የማይልው ባትሪው ስራችንን በነፃነት እንድንሰራ ይረዳናል።

ጥራትን ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር አጣምረው የያዙትን የGalaxy S23 ስልኮች ከጀሞ፣ መስቀል ፍላወር፣ እና ጋራድ በሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች እንሸምት።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
" ጥንቃቄ አድርጉ "

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።

አገልግሎቱ በላከው መግለጫ ÷ የተቋሙ አርማ የታተመባቸው የኪስ ቦርሳዎችን ወይም ዋሌቶችን በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደረጉ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች #እጅ_ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።

ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

አገልግሎቱ ፤ በዚህ ሕገወጥ ድርጊት የተሰማሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎችን ወይም ዋሌቶችን መታወቂያ አስመስለው በማዘጋጀት በተለያዩ አካባቢዎች ለማሰራጨት ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበርና ካዘጋጇቸው የኪስ ቦርሳዎች ውስጥ #የተወሰኑት በአንዳንድ ግለሰቦች እጅ እንደገቡ መታወቁን አመልክቷል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች እንደ መታወቂያ በማሳየት በሕገወጥ ተግባር መሰማራታቸውንና በተቋሙ ስም ያለአግባብ አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እንደተደረሰበት አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ የተቋሙ አርማ የታተመበትን የኪስ ቦርሳ ወይም ዋሌት ይዞ መገኘት ብሎም ሕገወጥ ለሆነ ተግባር ማዋል ሕጋዊ ተጠያቂነትን ያስከትላል ብሏል።

ይህ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አርማ የታተመበት የኪስ ቦርሳ በእጁ የገባ ግለሰብ በአካባቢው ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲያስረክብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0115543681 እና 0115543804 በመወደል እንዲያሳውቅ በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብም በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
" እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ "

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ህብረተሰቡ #እንዳይጭበረበር ራሱን እንዲጠብቅ አሳሰበ።

ከአገልግሎቱ ዛሬ መግለጫ ደርሶናል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በላከው መግለጫ ፤ " የጤናማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ለአገር ከፍተኛ እና የማይታካ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳላቸው ማንም የሚገነዘበው ነው " ብሏል።

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች እና ድርጅቶች " በኢንቨስትመንት እና በአብረን እንስራ ስም ተጨባጭና የተሟላ መረጃ ሳይሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ ከህብረተሰቡ እየሰበሰቡ መሆናቸውን " መረጃ ደርሶኛል ብሏል።

ገንዘብ ከህብረተሰቡ ለመሰብሰብም እጅግ አትራፊ የሆነ የግብርና እና የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸውን በመግለፅ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በዝቅተኛ ዋጋ መግዛት እንዲሁም አክሲዮን በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋቸውን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚችሉ በተለያዩ መንገዶች እያስተዋወቁና ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸው ተገንዝብያለሁ ብሏል።

ጤናማ የፋይናንስ እንቅስቃሴ እና ኢንቨስትመንት በእጅጉ የሚደገፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በኢንቨስትመንት ስም የሚፈፀሙና ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን መከላከል በዚያው ልክ አስፈላጊ ይሆናል ብሏል አገልግሎቱ።

ህብረተሰቡ ከመሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ሊፈፀም ከሚችል መጭበርበር ራሱን እንዲጠብቅ፣ የጥንቃቄ እርምጃም እንዲወስድ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፤ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል ከተለያዩ አካላት የፋይናንስ ወንጀል ነክ መረጃዎች በመቀበል፣ በመሰብሰብና በመተንተን ውጤቱን ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት እንዲሁም በመሰል ጉዳዮች ላይ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ በአንድ በኩል ራሱን ከወንጀል በመጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ደግሞ  ለተቋሙ ጥቆማ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን በምን በኩል ላግኛቸው ? ስልክ +251118128261 ፤ ኤሜል info@fis.gov.et

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር  የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ ነው " - የሰላም እና የስምምነት ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም እና ስምምነት ኮሚቴ ፤ በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።

ኮሚቴው ፤ " በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን ለሃይማኖታቸው አንድነትና መስፋፋት እንዲሁም ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት መሠረት በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዓላዊነት በጽናት በመቆም ተፈጠሩ የሚባሉ ችግሮችን ሁሉ በዝርዝር ለማቅረብ ለውይይት ዝግጁ እንድትሆኑ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

የሚያቀርቧቸውን የውይይት ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ችግሮቹን በስምምነት ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን ዝግጁ መሆኗን ኮሚቴው #አረጋግጧል

በዚህም የውይይትና የሰላም መልእክት ቤተ ክርስቲያኗ ያስተላለፈችውን ጥሪ በመቀበል በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይትና ለስምምነት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ የቀረበ ሲሆን #በቅርብ ቀናት ውስጥ የሰላም ልዑክ ለውይይት ወደ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ እንደሚጓዝ ኣሳውቋል።

በዚህም በጋራ በሚደረገው ቦታና ጊዜ የውይይትና የስምምነት ጉባኤ የሚደረግ ይሆናል ብሏል።

የፌዴራል መንግሥትና የክልል ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በመደገፍና ለውይይቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር ጥሪ ቀርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My Wish Enterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://publielectoral.lat/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#forfreemarket

አስፈላጊ ምርቶች  ፤ ተመጣጣኝ_ዋጋ

ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን⤵️
https://publielectoral.lat/forfreemarket

አነስተኛ የልብስ እና ጫማ ማጠቢያ
👉ለጫማ ቢሉ ለልብስ ቦታ የማይዝ
👉 ለፓንት ቦክሰር እና ካልሲ
👉ለ ቲሸርት ሁነኛ ተመራጭ
 👉ለዳይፐር

🏢 አድራሻ 👉 ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ
📲 0911255787
📲 0983360606
ጥራት መለያችን ነው
OnLineShopping
    
#ባቱ

በባቱ ከተማ ባለፈው እሁድ ለሊት ላይ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያ ላይ በከፈቱት ተኩስ 3 የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ አንድ ነዋሪ ፤ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ አንዲት ሴት እና 2 ወንድ የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት፤ ስርዓተ ቀብራቸውም በከተማው መፈፀሙን ፤ ከታጣቂዎቹ በኩል አንድ የተመታባቸውን ሰው እየጎተቱ አርቀው እንደወሰዱ የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን ገልጸዋል።

የታጣቂዎቹ ተኩስ መክፈት እስረኞችን ለማስለቀቅ መሆኑን እኚሁ የከተማይቱ ነዋሪ ተናግረዋል።

ባቱ በዕለቱ ከተፈፀመው ክስተት በኃላ በወትሮ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪው ገልጸዋል። ነገር ግን ሁኔታው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉን ለሬድዮ ጣቢያው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በባቱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በዕለቱ ረጅም ደቂቃ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበርና ተኩሱ ይሰማ የነበረው በማረሚያ ቤት አካባቢ እንደነበር አመልክተዋል።

በከተማው አስተዳደር በኩል የተባለ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደምም በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ፣ በቆጂ ከተሞች የታጠቁ ኃይሎች ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን መግደላቸውና እስረኞችን ለማስመለጥ ሙከራ ማድረጋቸው መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበቆጂ ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ ስለተፈፀሙት ጥቃቶች ከዚህ ቀደም ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው ፤ የተደራጀ ጥቃት በየትኛውም አካባቢ እንዳልተፈፀመ " አልፎ አልፎ #ሽፍታ ወይም #ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በሀገራችን #ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ማለትም፦
- በሰሜን ኢትዮጵያ (ትግራይ፣ አማራ፣ አፋር)
- በአሮሚያ
- በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በነበረው ጦርነት እና ግጭት ምክንያት ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉዳት እና ውድመት መድረሱ ተገለጿል።

ይህ የተገለፀው ከቀናት በፊት የአምስት /5/ ዓመት የመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ መርሐ ግብር ይፋ ሲደረግ ነው።

የጉዳት እና የመልሶ ማቋቋም ፍላጎት ዳሰሳ ከዓለም ባንክ እና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ ተቋማት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በኢትዮጰያ መንግሥት የተደረገ ነው።

ይፋ በማድረጊያው ስነስርዓት ላይ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የፌዴራል ባለስልጣናት፣ የክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች ተገኝተው የነበረ ሲሆን በመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ መርሐ ግብሩ ላይ አስተየያየት ሰጥተዋል፡፡

ማን ምን አለ ?

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፦

" የመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ዕቅዱን ለማስፈጸም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል። "

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" በትግራይ የደረሰው ጉዳትና ውድመት ግዙፍ ነው። ጦርነቱ ብዙ ሕይወትን ቀጥፏል፤ በመሠረተ ልማት ላይም መጠነ ሰፊ ውድመትን አስከትሏል፡፡ በትግራይ ግን ጉዳቱ ከዚያም በላይ ነው፡፡

በጦርነቱ የክልላዊ መንግሥቱ መዋቅር እንዳለ ነው የፈረሰው፡፡ በአብዛኛው የመንግሥት ተቋማት እንደ አዲስ ነው እየጀመሩ ያሉት፡፡

ያሉን የተፈናቃዮች ብዛት አስደንጋጭ ነው፡፡

ልጆቻችን ትምህርት ካቆሙ 4 ዓመታት ሆኗቸዋል፡፡ አርሶ አደሮቻችን የተለመደውን የእርሻ ሥራ ለመከወን የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ለእኛ በዚህ ሰዓት ስለ መልሶ ግንባታ መናገር ቅንጦት ይሆንብናል፤ ምክንያቱም ከዚያ በፊት፣ በርካታ የማገገሚያ ሥራዎችን ማከናወን አለብን፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ አለብን፡፡ አርሶ አደሮቻችን ማረስ እንዲጀምሩ ማስቻል አለብን፡፡ ተማሪዎቻችንን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ አለብን፡፡ ቢያንስ እውነተኛውን ትምህርት እንዲያገኙ ሳይኾን፣ እንደው ለስሙ አእምሯቸው ከጦርነቱ ድባብ እንዲርቅ ያህል።

በትግራይ የደረሰው ጉዳትና ውድመት የተለየ ነው፤ በርካታ የቀድሞ ተዋጊዎች አሉን፡፡ እነርሱን በአግባቡ ማቋቋም ካልተቻለ፣ የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ማድረግ ያስቸግራል።

ያሉን የተረጂዎች ቁጥር ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ስድስት ሚሊዮን ያለምንም ሳይንሳዊ ጥናት ወደ ሦስት ሚሊዮን እንደወረደ ቢገለጽም፣ እነዚኽም ቢኾኑ በአሁኑ ጊዜ፣ ምንም ዓይነት ርዳታ እያገኙ አይደሉም።

ችግሮቹን ለመፍታት፣ በሚቀጥሉት ሦስት እና አራት ወራት፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የቻሉትን ያህል ያግዙን፤ ከዚያ በኋላ ስለ መልሶ ግንባታ እንናገራለን። "

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፦

" በጦርነቱ በክልሉ የደረሰው ጉዳት እና ውድመት፣ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተጠንቶ፤ ውጤቱም ታትሞ ተሰራጭቷል።

ክልሉ ከደረሰበት ጉዳትና ውድመት እንዲያገግምም፣ በመልሶ ማቋቋሙ እና ግንባታ ሒደቱ ተባብረን ልንሠራ ይገባል።

ስላጋጠመው ጉዳት በዝርዝር መናገር አልፈልግም ፤ ጦርነቱ ግን በሰላም ስምምነት ተቋጭቷል፡፡

የአማራ ክልልና በጥቅሉ ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱን ውጤት እያጣጣሙ ናቸው፡፡

አሁን ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ጥረት እያደረግን ነው። የቀውሱ ዳፋ ግን ቀጥሏል፡፡ መሠረተ ልማት ፈርሷል፤ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ወድመዋል፡፡

ጦርነቱ የተካሔደባቸውን አካባቢዎች፣ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ፣ የጋራ ትብብር እና ቅንጅታዊ አሠራር ይፈልጋል፡፡በርከት ያለ ገንዘብ ማውጣትን ይፈልጋል፡፡

ይህን ስናደርግ እነርሱም የሰላም ስምምነቱን ውጤት ማጣጣም ይጀምራሉ፡፡ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሒደት አካልም ይኾናሉ። "

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፦

" በደቡባዊ እና ምዕራባዊ የክልሉ አካባቢዎች ያለው ግጭት ከ5 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

ግጭቱ በትምህርት፣ በጤናና በሌሎችም ማኅበራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ትልቅ ውድመት አድርሷል።

የመልሶ ማቋቋም እና የግንባታ ሥራን ለማከናወን በቅድሚያ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው ሸማቂ ኃይል ጋራ የጀመርነውን የሰላም ጥረት በመቀጠል ከዳር ማድረስ አለብን።

በዚህ መልኩ ዘላቂ ሰላም ካልተረጋገጠ፣ የመልሶ ግንባታ ጥረቱ አይሳካም። "

Credit : VOA AMHARIC

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

(የገቢዎች ሚኒስቴር)

ክሊራንስ ለመስጠት ኦዲት #የማያስፈልጋቸው አገልግሎቶች ፦

ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አገልግሎቶች ታክስ ከፋዩን ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ሊሰጥ ይችላል:-

- ንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የሙያ ፍቃድ ለማደስ፤
- ጨረታ ለመካፈል ወይም ለመሳተፍ፤
- ለተሽከርካሪዎች ወይም ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ (ክላውዶ) ለማድረግ፤
- የባንክ ብድር ለማግኘት፤
- የመድን ካሳ ለማግኘትና የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ፤
- የድርጅት ስም ወይም አድራሻ ለመለወጥ፤
- የንግድ ሥራ ሀብት መቀነስን ሳይጨምር የንግድ ዘርፍ ቅነሳ ለማድረግ፤
- ድርጅቶች እንደገና ተደራጅተው ሲዋሀዱ የተዋሀደውን ድርጅት የታክስ ዕዳ አካቶ የሚዋሃዱ ስለመሆኑ የፀደቀ ሰነድ ለማቅረብ፤

1. የክሊራንስ ጥያቄ በቀረበበት ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የተሰጠው እና ያልተከፈለ የታክስ ዕዳ ያለበት ታክስ ከፋይ ኦዲት ሳይደረግ የባንክ ብድር እንዲወስድ ክሊራንስ የሚሰጠው ዕዳውን የከፈለ እንደሆነ ወይም ለመክፈል የባንክ ዋስትና ያቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

2. ታክስ ከፋዩ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ሊሰጠው የሚችለው:-
• ታክስ ከፋዩ ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ግብር ማስታወቂያ እና መክፈያ የመጨረሻ ቀን ከመድረሱ በፊት የንግድ ሥራ ፍቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍ፣ የባንክ ብድር ለመውሰድ እና የጉዳት ካሳ ለማግኘት የሚቀርብ የታክስ ክራንስ ምስክር ወረቀት ጥያቄ ከሆነ ጥያቄው ከቀረበበት የግብር ዘመን በፊት ታክሱን አስታውቆ ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ እና
• የታክስ ክራንስ ምስክር ወረቀት የተጠየቀበትን አገልግሎት ዓይነትና የተፈለገበትን ምክንያት የሚያስረዳ ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ይሆናል፡፡

3.  የባንክ ብድር ለማግኘት የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለጠየቀ ሰው የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት የሚሰጠው ጥያቄ አቅራቢው የንግድ ሥራ ያልሠራና በግብር ከፋይነት ያልተመዘገበ ከሆነ ከታክስ መስሪያ ቤቱ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከመረጃ ቋት ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ጠያቂው በንግድ ሥራ አለመሠማራቱን በማረጋገጥ ይሆናል፡፡

4.  የንግድ ሥራ ፍቃድ ለመመለስ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከታክስ ሚኒስቴሩ የሥራ ክፍሎች እና ከሶስተኛ ወገን በማጣራት የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Credit : የገቢዎች ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የፈተና ህትመት ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር እየተሰራ ነው " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በቂ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የከተማው ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የፈተና ህትመት ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር እየተሰራ እንዳለ ተጠቁሟል።

በዘንድሮው ከተማ አቀፍ ፈተና በ8ኛ ክፍል 75‌100 ተማሪዎች በ766 ት/ቤቶች እንዲሁም በ6ኛ ክፍል 75‌090 ተማሪዎች በ788 ትምህርት ቤቶች በመደበኛ በማታና በግል ለመፈተን ምዝገባ ማካሔዳቸውን ተነግሯል።

ከተማ አቀፍ ፈተናውን በብቃት ለመስጠት ትምህርት ቢሮው በቂ ዝግጅት ማድረጉን ያሳወቀ ሲሆን የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች ሱፐርቫይዘሮችና ፈታኞችም ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በቀጣይ በከተማዋ 53,535 የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚቀርቡ ከከተማው የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#Update

የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ከአንድ ወር በኃላ ነባር ተማሪዎቻቸውን እንደሚቀበሉ ከመስከረም (2016) ጀምሮ ደግሞ #ሙሉ_ለሙሉ ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ የሰጡት ቃል ፦

" ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመጭው ወር ነባር ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ።

በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ጋር በመቐለ ተደጋጋሚ ውይይት አድርጓል።

ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት ወደ ተግባር ተገብቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት ፦
- የምግብ ፣
- የመኝታ፣
- የሕክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

መቐለና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣይ ወር ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር ጨርሰው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ ይችላል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ነበር። ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡ ተደርጎ በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ነው።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ይታወሳል ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት ይችላሉ። "

Via EPA

@tikvahethiopia
Forwarded from JD
#ብርሃን_ባንክ
ዛሬ በጥቂት የተከማቸ ገንዘብ አድጎ ለቁም ነገር እንዲውል ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኘው የህጻናት የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!