TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰበር_ዜና

አትሌት ደምስ ፀጋው አረፈ!

ባለፉት በርካታ አመታት ሀገሩ ኢትዮጵያን ወክሎ በተለያዩ ውድድሮች ሲወዳደር የነበረው አትሌት ደምስ ፀጋው ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አትሌቱ ኢትዮጵያን በመወከል በሀገር አቋራጭ እና የአስፓልት ላይ ውድድሮችን በርካታ ጊዜ ያደረገ ሲሆን በአደረበት ህመም ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡

አትሌት ደምስ #በግሉ እና #ሀገር በመወከል በርካታ ውድድሮችን አድርጎ ጥሩ ውጤት ያመጣ እንደነበርም ታውቋል፡፡ አትሌቱ ህይወቱ ያለፈው በአሜሪካ ሀገር ሲሆን በቅርብ ቀናት አስከሬኑ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ/Bekal Alamirew/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

አቡበክር አል ባግዳዲ መገደሉ ተረጋገጠ!

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአይኤስ-አይኤስ (ISIS) መሪው አቡበክር አልባግዳዲ አሜሪካ በወሰደችው የጥቃት መገደሉን አረጋግጠዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የሀገሪቱ ወታደሮች በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባካሄዱት የፀረ ሽብር ዘመቻ የአይ ኤስ መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ መገደሉን አስታውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ፦

"ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው።

ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ። የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታት እና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል።

ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።

የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።

ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል ፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝ እና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በetv እየሰጡ በሚገኙት መግለጫ ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ጥቃት እንደተፈፀመበት አስታውቀዋል።

ጥቃቱን የፈፅሙት "ካሃዲ ኃይሎች እና ያደራጁት ኃይል" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ "ጥቃቱ በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በተለያየ ሀገር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት እንኳን በውጭ ኃይሎች ያልደረሰበት ጥቃት በገዛ ወገኖቹ ከጀርባው እንዲመታ ተደርጓል" ብለዋል።

በተፈፀመው ጥቃት ብዙዎች የሰራዊቱ አባላት ተሰውተዋል ፤ ቆስለዋል ፤ ንብረቶች እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል መቐለ እና ሌሎች አባባቢዎች ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በአማራ ክልል በዳንሻ በኩል ጥቃት ተፈጽሟል ፤ በአማራ ክልል የነበረው ኃይል ጥቃቱን መክቷል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅራቅር አካባቢ በነበሩ ውጊያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ያደረጉት ተጋድሎ በታሪክ የሚዘከር ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ተናገሩ።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ በመከላከያ ሰራዊት ተግባር 'ህውሓት' ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈው ውለዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ።

ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

የታንዛኒያው ፕሬዜዳንት ጆን ማጉፉሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ፕሬዜዳንቱ በ61 ዓመታቸው ነው ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፈው።

የፕሬዜዳንት ማጉፉሊን ህልፈት ያሳወቁት ምክትል ፕሬዜዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሲሆኑ ህልፈታቸው ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሰሞኑን ፕሬዜዳንት ማጉፉሊ ለሳምንታት ያህል ያለመታየታቸው መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል ፤ አንዳንዶችም በኮቪድ-19 ተይዘው በውጭ ሀገራት (ኬንያ እና ህንድ) ህክምና ላይ ናቸው ሲሉ ነበር።

ለመጨረሻ ጊዜ በህዝብ ፊት የታዩት የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ/ም ነው።

ፕሬዜዳንቱ በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በሽታውን ሲያናንቁት፣ ለበሽታው ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው የሚልና ሌሎችም አነጋጋሪ አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ።

አንዳንዶች ህልፈታቸውን ከኮቪድ-19 ጋር ቢያገናኙትም ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ የህልፈታቸው ምክንያት "የልብ ህመም" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ዙር የድምፅ አሰጣጥ ተጠናቋል። በቀጣይ የድምፅ ቆጠራው ይካሄዳል። በመጨረሻው ዙር ምርጫ ፈርማጆ አልያም ደግሞ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፉክክሩን በድል ያጠናቅቃሉ። ፈርማጆ ካሸነፉ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሆነው ዳግም ይመረጣሉ ፤ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ካሸነፉ ከፈርማጆ በፊት የነበሩበትን የፕሬዜዳንትነት መንበር በመረከብ ሀገራቸውን ዳግም የመምራት እድልን ያገኛሉ።…
#ሰበር_ዜና

የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በድጋሚ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመረጡ።

ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የአሁኑን የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆን እጅግ ፉክክር በተሞላበት ሶስት ዙር የምርጫ ሂደት አሸንፈዋቸዋል።

የመጨረሻ ውጤት ፦

👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 214 ድምፅ
👉 ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 110 ድምፅ

3 ድምፅ ዋጋ ቢስ ሆኗል።

@tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና 

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ።

በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ።

ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪ እና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ  ተለይተዋል።

ምንጭ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 "የቀድሞ" አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስገብተዋል ሲል የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል። ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ…
#ሰበር_ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia