TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነው ?

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ !

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገፁ 20 ሺህ #ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን መቅጠር እንደሚፈልግ አስታወቀ ፤ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን የሚቀጥረው ትግራይ ፣ አፋር፣ ሶማሌ ክልሎችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የቴሌኮም አገልግሎቱን ለማስፋፋት በማቀድ ነው ፤ የስራ ቅጥሩ ዲግሪ አይጠይቅም 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ማመልከት ይችላሉ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም #ሀሰተኛ መሆኑን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጾልናል።

ከጥዋት አንስቶ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን የ20 ሺህ ሰራተኞች ቅጥር መረጃ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሚመለከተው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍል " በየትኛው የማህበራዊ ትስስር ገፃችሁ ላይ ነው ይህ ያሳወቃችሁት ? መረጃው እውነት ከሆነስ በየትኛው መንገድ ነው ማመልከት የሚቻለው ? " ስንል ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን መረጃው #ሀሰተኛ ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል።

" እኛ 20 ሺህ ሰራተኞች ለመቅጠር በየትኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፃችን ላይ ጥሪ አላቀረብንም ፤ መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩት ሆን ተብሎ ተመሳስለው በተከፈቱ #ሀሰተኛ_ገፆች ነው " ሲል የሚመለከተው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍል ገልጾልናል።

በመሆኑም " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ሊቀጥር ነው " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia
" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።

ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia
ልዩ የቴሌብር ጥቅል እስከ 55% ከሚደርስ ቅናሽ ጋር!

በዘርፈ-ብዙ አገልግሎቱ ደንበኞቹን እፎይ ያሰኘው ቴሌብር በልዩ ቅናሽና ስጦታዎች ማንበሽበሹንም ቀጥሏል።

ከመደበኛ ጥቅሎቻችን እስከ 55% ቅናሽ የተደረገባቸውን ወርሃዊ የድምጽ እና ዳታ ጥቅሎች ከጥሪ ማሳመሪያ ስጦታ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ በልዩነት ስናቀርብ ደስታችን ወደር የለሽ ነው!

በየትኛውም ቦታ በእጅዎ ላይ ያለ የቅርብ አለኝታ
ቴሌብር የዘመን ስጦታ!
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል።

የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች በሀዋሳ ከተማ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ " ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት " በሃይል ታግታ መወሰዷን የሜላት የቅርብ ዘመዶች ገልጸዋል።

የሜላት የአክስት ልጅ የሆነችው ትዕግስት ብስራት ስለሁኔታው ምን ትላለች ?

" እኔና እናቴ ለቅሶ ላይ ስለነበርን [ለሜላት] ቁልፉን አስቀምጠንላት ነበር. . .[ቁልፉን] ከስራ ቦታዬ ወደመኖሪያ ቤት ይዛ እየሄደች ነበር።

ከዚያ እንደጥበቃ የሚሰራልኝ ልጅ በግምት 6 ሰዓት ተኩል ይሆናል ደውሎ ‘ሁለት ዳማስ [መኪና] ቆሞ ነበር፣ እየጮኸች ልጅሽን አፍነው አስገቧት’ አለኝ " ብላለች።

የሜላት እናት ከዓመታት በፊት በማለፋቸው ምክንያት ከሶስት ዓመቷ ጀምሮ ከሷ ቤተሰቦች ጋር ነው ያደገችው።

ነገሩ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ከሌሎች ቤተሰቦቿ ጋር በመሆን ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ትዕግስት ገልጻለች።

ትዕግስት ሀዋሳ ከተማ ውስጥ አንስተኛ ምግብ ቤት ያላት ሲሆን ፤ የአጋቾቹን ማንነ ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ እሷ ጋር ምግብ የሚበሉ ልጆች መሆናቸውን አመልክታለች።

" ለሊቱን ሙሉ እየፈለኳቸው ነው። ወደ ቤት አልገባሁም " ስትልም ገልጻለች።

ትዕግስት " ጠላፊውን " እንድምታወቀውና ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የገለጸች ሲሆን ይህ የምግብ ቤት ደንበኛዋ የተለየ ምንም ነገር እንደማያሳይ ተናግራለች።

" ከሜላትና ከልጆቼ ጋር ያለኝ ነገር ያውቃሉ። " ያለችው ትዕግስት " ሲናገሯቸው እንኳን በጣም ነው የምቆጣው። አይደፍሩም. . . ሙሉ ቤተሰብ ለቅሶ ላይ ስለነበር አለመኖራችንን አይቶ ነው [ይህንን ያደረገው]” ብላለች።

ሌላኛው የሜላት የአክስት ልጅ እንዳልካቸው ብስራት ስለጉዳዩ ምን አለ ?

" ከዚህ በፊት ሜላት ‘ያስቸግረኛል’ ብላ የተናገረችው ሰው የለም

እኛ ግራ ገብቶኖናል። ማንም ፍንጭ የሚሰጠን አጣን።

በእንባ ጭምር ቤተሰቡ ጭንቅ ላይ ነው። " ብሏል።

እንዳልካቸውና ትዕግስት ከፖሊስ ጋር በመሆን ሜላትን እያፈላለጉ እንደሚገኙ ገልጸው " ጥሩ ትብብር እየተደረገልን ይገኛል " ብለዋል።

ሜላትን በኃይል ወደ ተሽከርካሪ እንድትገባ ሲደረግ የአካቢው ሰው ሊታደጋት መሞከሩንም ቤተሰቦቿ አመላክተዋል።

" [ሜላት] ስትጮህ ይዟት የጠፋውን መኪና የፊትለፊቱን መስታወት የአከባቢው ሰው ሰብሮበታል። ከዛ በኋላ እየበረረ አመለጠ " ሲል እንደላካቸው ገልጿል።

በሌላ በኩል ትዕግስት ፤ የጠለፏትን ሰዎች ማንነት ካጣራች በኃላ መረጃ ለመጠየቅ ወደ የቤተሰቧቻቸው ቤት ቢሄዱም ሊተባበሯት እንዳልቻሉ ገልጻለች።

ሜላት ከመጠለፏ አስቀድሞ ከእሷ ጋር የምትማርና ‘የጠላፊው’ ዘመድ ሜላትን አናግራታለች። " እሷም ቤቷ ሄደን አላገኘናትም። ሸሽተዋል " ስትል ትዕግስት ተናግራለች።

ትዕግስት " መርዳት የሚችል አካል እንዲረዳኝ በጣም እፈልጋለሁ ' ስትል በእንባ ተማጽናለች።

ሜላት የተወለደችው ያቤሎ ከተማ ሲሆን ከእናቷ ህልፈት በኃላ ወደ ጉጂ ዞን ዋደራ ሄዳ ዓመታትን ቆይታለች።

ከአራት ዓመታት በፊት ወደ ሀዋሳ ከተማ ከቤተሰቦቿ ጋር በማቅናት ትምህርቷን እየተከታተለች ነው።

ከጥቂት ቀናት በፊት በዛው በሀዋሳ ከተማ ፀጋ በላቸው የተባለች የባንክ ሰራተኛ በአንድ ግለሰብ ተጠልፋ ከቀናት በኃላ ነፃ መሆኗ የሚዘነጋ አይደለም።

Via BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

ስልካችሁን በመጠቀም የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የሚጠበቅባችሁ ቀላል መመሪያዎች!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#Safaricom

ቀናችንን በSamsung Galaxy S23 Ultra ፈካ እናድርግ። ጥራት ያለው ፕሮሰሰሩ እና ፍንክች የማይልው ባትሪው ስራችንን በነፃነት እንድንሰራ ይረዳናል።

ጥራትን ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር አጣምረው የያዙትን የGalaxy S23 ስልኮች ከጀሞ፣ መስቀል ፍላወር፣ እና ጋራድ በሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች እንሸምት።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
" ጥንቃቄ አድርጉ "

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።

አገልግሎቱ በላከው መግለጫ ÷ የተቋሙ አርማ የታተመባቸው የኪስ ቦርሳዎችን ወይም ዋሌቶችን በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደረጉ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች #እጅ_ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።

ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

አገልግሎቱ ፤ በዚህ ሕገወጥ ድርጊት የተሰማሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎችን ወይም ዋሌቶችን መታወቂያ አስመስለው በማዘጋጀት በተለያዩ አካባቢዎች ለማሰራጨት ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበርና ካዘጋጇቸው የኪስ ቦርሳዎች ውስጥ #የተወሰኑት በአንዳንድ ግለሰቦች እጅ እንደገቡ መታወቁን አመልክቷል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች እንደ መታወቂያ በማሳየት በሕገወጥ ተግባር መሰማራታቸውንና በተቋሙ ስም ያለአግባብ አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እንደተደረሰበት አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ የተቋሙ አርማ የታተመበትን የኪስ ቦርሳ ወይም ዋሌት ይዞ መገኘት ብሎም ሕገወጥ ለሆነ ተግባር ማዋል ሕጋዊ ተጠያቂነትን ያስከትላል ብሏል።

ይህ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አርማ የታተመበት የኪስ ቦርሳ በእጁ የገባ ግለሰብ በአካባቢው ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲያስረክብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0115543681 እና 0115543804 በመወደል እንዲያሳውቅ በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብም በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
" እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ "

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ህብረተሰቡ #እንዳይጭበረበር ራሱን እንዲጠብቅ አሳሰበ።

ከአገልግሎቱ ዛሬ መግለጫ ደርሶናል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በላከው መግለጫ ፤ " የጤናማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ለአገር ከፍተኛ እና የማይታካ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳላቸው ማንም የሚገነዘበው ነው " ብሏል።

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች እና ድርጅቶች " በኢንቨስትመንት እና በአብረን እንስራ ስም ተጨባጭና የተሟላ መረጃ ሳይሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ ከህብረተሰቡ እየሰበሰቡ መሆናቸውን " መረጃ ደርሶኛል ብሏል።

ገንዘብ ከህብረተሰቡ ለመሰብሰብም እጅግ አትራፊ የሆነ የግብርና እና የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸውን በመግለፅ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በዝቅተኛ ዋጋ መግዛት እንዲሁም አክሲዮን በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋቸውን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚችሉ በተለያዩ መንገዶች እያስተዋወቁና ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸው ተገንዝብያለሁ ብሏል።

ጤናማ የፋይናንስ እንቅስቃሴ እና ኢንቨስትመንት በእጅጉ የሚደገፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በኢንቨስትመንት ስም የሚፈፀሙና ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን መከላከል በዚያው ልክ አስፈላጊ ይሆናል ብሏል አገልግሎቱ።

ህብረተሰቡ ከመሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ሊፈፀም ከሚችል መጭበርበር ራሱን እንዲጠብቅ፣ የጥንቃቄ እርምጃም እንዲወስድ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፤ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል ከተለያዩ አካላት የፋይናንስ ወንጀል ነክ መረጃዎች በመቀበል፣ በመሰብሰብና በመተንተን ውጤቱን ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት እንዲሁም በመሰል ጉዳዮች ላይ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ በአንድ በኩል ራሱን ከወንጀል በመጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ደግሞ  ለተቋሙ ጥቆማ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን በምን በኩል ላግኛቸው ? ስልክ +251118128261 ፤ ኤሜል info@fis.gov.et

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር  የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ ነው " - የሰላም እና የስምምነት ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም እና ስምምነት ኮሚቴ ፤ በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።

ኮሚቴው ፤ " በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን ለሃይማኖታቸው አንድነትና መስፋፋት እንዲሁም ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት መሠረት በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዓላዊነት በጽናት በመቆም ተፈጠሩ የሚባሉ ችግሮችን ሁሉ በዝርዝር ለማቅረብ ለውይይት ዝግጁ እንድትሆኑ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

የሚያቀርቧቸውን የውይይት ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ችግሮቹን በስምምነት ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን ዝግጁ መሆኗን ኮሚቴው #አረጋግጧል

በዚህም የውይይትና የሰላም መልእክት ቤተ ክርስቲያኗ ያስተላለፈችውን ጥሪ በመቀበል በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይትና ለስምምነት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ የቀረበ ሲሆን #በቅርብ ቀናት ውስጥ የሰላም ልዑክ ለውይይት ወደ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ እንደሚጓዝ ኣሳውቋል።

በዚህም በጋራ በሚደረገው ቦታና ጊዜ የውይይትና የስምምነት ጉባኤ የሚደረግ ይሆናል ብሏል።

የፌዴራል መንግሥትና የክልል ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በመደገፍና ለውይይቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር ጥሪ ቀርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My Wish Enterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://publielectoral.lat/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#forfreemarket

አስፈላጊ ምርቶች  ፤ ተመጣጣኝ_ዋጋ

ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን⤵️
https://publielectoral.lat/forfreemarket

አነስተኛ የልብስ እና ጫማ ማጠቢያ
👉ለጫማ ቢሉ ለልብስ ቦታ የማይዝ
👉 ለፓንት ቦክሰር እና ካልሲ
👉ለ ቲሸርት ሁነኛ ተመራጭ
 👉ለዳይፐር

🏢 አድራሻ 👉 ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ
📲 0911255787
📲 0983360606
ጥራት መለያችን ነው
OnLineShopping
    
#ባቱ

በባቱ ከተማ ባለፈው እሁድ ለሊት ላይ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያ ላይ በከፈቱት ተኩስ 3 የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ አንድ ነዋሪ ፤ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ አንዲት ሴት እና 2 ወንድ የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት፤ ስርዓተ ቀብራቸውም በከተማው መፈፀሙን ፤ ከታጣቂዎቹ በኩል አንድ የተመታባቸውን ሰው እየጎተቱ አርቀው እንደወሰዱ የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን ገልጸዋል።

የታጣቂዎቹ ተኩስ መክፈት እስረኞችን ለማስለቀቅ መሆኑን እኚሁ የከተማይቱ ነዋሪ ተናግረዋል።

ባቱ በዕለቱ ከተፈፀመው ክስተት በኃላ በወትሮ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪው ገልጸዋል። ነገር ግን ሁኔታው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉን ለሬድዮ ጣቢያው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በባቱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በዕለቱ ረጅም ደቂቃ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበርና ተኩሱ ይሰማ የነበረው በማረሚያ ቤት አካባቢ እንደነበር አመልክተዋል።

በከተማው አስተዳደር በኩል የተባለ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደምም በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ፣ በቆጂ ከተሞች የታጠቁ ኃይሎች ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን መግደላቸውና እስረኞችን ለማስመለጥ ሙከራ ማድረጋቸው መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበቆጂ ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ ስለተፈፀሙት ጥቃቶች ከዚህ ቀደም ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው ፤ የተደራጀ ጥቃት በየትኛውም አካባቢ እንዳልተፈፀመ " አልፎ አልፎ #ሽፍታ ወይም #ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia