TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጋምቤላ⬆️

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ከአንድ ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ቾል ኩን ለኢዜአ እንደገለጹት ህገ ወጥ መሳሪያዎችን ከትናንት በስቲያ በጋምቤላ ከተማ በቁጥጥር ሥር ማዋል የተቻለው #ከላሬ ወረዳ ወደ #ጋምቤላ ከተማ ለማስገባት ሲሞክር ነው።

በፖሊስ ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች መካከል አራት ሽጉጦች፣ አንድ ታጣፊ ክላሽ፣ አንድ ሺህ 133 የተለያዩ ዓይነት ጥይቶች ይገኙበታል።

ከህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ጋር ከ20 ሺህ 600 ብር በላይ #ገንዘብ ፖሊስ አብሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በተጠርጣሪው ላይ በተደረገው ማጣራትም የጦር መሳሪያዎቹን ወደ #መሀል ሀገር የማስገባት እቅድ እንደነበረውም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪ ግለሰቡ ላይ ማስረጃ የማሰባሰብና የማጠራት ሥራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ “የምርመራ ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ይላካል” ብለዋል።

ክልሉ በተለይም ከደቡብ ሱዳን ጋር በስፋት በድንበር የሚዋሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ክልሉ እየገባ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት በሚደረገው ጥረት የህዝቡ #ተሳተፎውን እንዲያጠናክር
ጠይቀዋል።

ህግ ወጥ የጦር መሳሪዎች በሀገሪቱ ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች በመገንዘብ ኮሚሽነሩ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር በጋራ #ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ…
#NewsAlert

በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ።

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ፈተናው በኮሌጅም ጭምር እንዲሰጥ ተወስኗል " ብሏል።

የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳወቀው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል።

በተለይም በ #ኑዌር_ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል።

#አኙዋ_ዞን፣ በከፊል ከ #ኢታንግ ልዩ ወረዳና ከ #ጋምቤላ_ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በጋምቤላ ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ወደተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ በመሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ነው በሁለት ቦታ ፈተናው እንዲሰጥ የተወሰነው።

መረጃው ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia