TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት  ለማድረግ  የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን አሳወቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ባካሔደው የርክበ ካህናት ጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ  እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ኮሚቴው ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ የሚያስችለውን በእቅድ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይቱ በተሳካ ሆኔታ መካሔድ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄውን አቅርቧል።

የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈውን ደብዳቤ በአካል በመገኘት ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማቅረብ ከሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ለውይይቱ መሳካት በሚያደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት በማድረግ መመለሱ ተገልጿል።

ስለሆነም ለክልሉ መንግስት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ሁለቱም አካላት በሚያመቻቹት ጊዜና ቦታ ውይይቱ የሚካሔድ ይሆናል ተብሏል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

መግለጫውን ተከትሎ ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን ይገለፃሉ ተብሏል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ።

ልዑኩ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው በቆይታቸው ከርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር  በሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Credit ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የነበረንን ጥያቄ ለማቅረብ በወጣንበት " የኃይል እርምጃ ተወስዶብናል " ሲሉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ አቀረቡ።

ተማሪዎቹ ጥያቄ የነበረው ከመውጫ ፈተና በኃላ ለሚካሄደው ምርቃት " ምርቃቱ ላይ ለመገኘት የወደቀ ያለፈ መባል የለበትም ፤ አንድ ላይ መመረቅ አለብን ፤ ለ16 አመት ያክል የለፋንበት ፣ ቤተሰብም ብዙ የደከመበት ነው ይሄ ጉዳይ መልስ ያሻዋል " በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

" ይህን ጥያቄያችንን ድንጋይ፣ ዱላ ሳንይዝ ምላሻ እንዲሰጠን ለመጠየቅ ሰልፍ ብናደርም የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም፣ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም፣ የወንድ እና የሴቶች ዶርም ድረስ በመዝለቅ ጉዳዩን የማያውቁ ተማሪዎችን ጭምር በመደብደባ እና በማዋከብ ጥያቄያችንን ለማፈን ሞክረዋል " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኳቸው የቪድዮ ማስረጃዎች የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎችን በደቦ ሰደበድቡ ፣ ወደ ሴቶች ዶርም ዘልቀው ገብተው ተማሪዎችን በኃይል ሲያስወጡ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ሰራተኞች በኩል ሃስብ ለመቀበል ጥረት አድርጓል። አንድ በሳምንት መጨረሻ ቀናት ለማስተማር በተቋሙ የተገኙ መምህር ጉዳዩን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ እንደነበር ገልጸዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት ተማሪዎቹ የግቢ ውስጥ እየጮሁ የመማር ማስተማር ስራውን ሲያውኩ፣ መንገድ በድንጋይ ሲዘጉ፣ ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሎች ላይ ትንኮሳ ለመፈፀም በሞከሩበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ቪድዮዎች የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ አይደለም የሚሉት መምህሩ ግቢውን ለመረበሽ የሞከሩ ተማሪዎች እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ከልክ ያለፈ እርምጃ የወሰዱ የፀጥታ ኃይሎችን እኩል ማውገዝ ይገባል ብለዋል።

" ተማሪዎቹን ንጹሕ፤ የጸጥታ ሀይሉን በመወንጀል የሚሰራ ዜና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ሁኔታውን የማያስረዳ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላ አንድ የግቢው ሰራተኛ የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት የግቢው የመማር ማስተማር ስራ ሲታወክ እና ግቢው ሲረበሽ ነው ብለው የተወሰደው እርምጃ ግን ልክ ያለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

መልዕክታቸውን የላኩ ተማሪዎቹ ግን በግቢው ሰራተኞች በኩል የተሰጠው ሃሳብ የማይቀበሉት ሲሆን አጠቃላይ የነበረው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበር፤ ተማሪዎች ግቢ ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ እንደሌለ፣ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰድ በጀመሩበት ወቅት ግን መንገድ ለመዝጋት መሞከሩን አመልክተዋል።

አንድ የግቢው ተማሪ፤ " በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ከማቅረብ በዘለለ ድንጋይ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ለመወርወር የሞከረ  ፤ ዓመታትን በተማረበት ተቋም ጥፋት ለማድረስ የሞከር ተማሪ አልነበረም ብሏል።

" በእርግጥ መንገድ ዘግተዋል መንገድ የዘጉበት ምክንያት ፖሊስ ተማሪን መምታት ሲጀመር ነው " ሲል ገልጿል።

በርካታ ተማሪዎች የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዳቸው፤ ተቋሙ ለሰለማዊ ጥያቄ ከውይይት ይልቅ ኃያልን አማራጭ ማድረጉን የሚገልፅ መሆኑን እና በተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መጎዳታቸውን፣ ንብረትም መዘረፉን አመልክተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠንን ምላሽ ተከታትለን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ በመርሃግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ መሆናቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-11

@tikvahethiopia
" በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን መቐለ ተገኝተው ነው ያስረከቡት።

ድጋፉ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን ከተደረገው ድጋፍ ከ218 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው የጥሬ ገንዘብ ሲሆን እና ቀሪ ደግሞ የተለያዩ ቁሳቁሶች ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ " ከሰላም እንጂ ከጦርነት ትርፍ ስለማይገኝ ሰላማችንን ማጽናት አለብን " ያሉ ሲሆን " በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " ብለዋል።

" በየትኛው የሀገሪቱ ጫፍ የሚያጋጥም ጉዳት የሁሉም ጉዳት በመሆኑ የወደመውን በትብብር መልሰን እንገነባለን " ሲሉም አሳውቀዋል።

የትግራይ ግዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቃል በገባው መሠረት ለትግራይ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ቅድሚያ ተነሳሽነቱን ወስዶ ተግባራዊ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

" ተጋግዘን በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ወደ ልማት እና እድገት መመለስ አለብን " ብለዋል።

መረጃው ከAMN ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን መቐለ ተገኝተው ነው ያስረከቡት። ድጋፉ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን ከተደረገው ድጋፍ ከ218 ሚሊየን…
#Tigray

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ አስተዳደር በትግራይ ክልል ለሚያስገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተቀምጧል።

የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ትምህርት ቤት " ሰማዕታት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት " የሚሰኝ ነው።

የትምህርት ቤቱ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው በአዲስ አበባ #ህዝብ እና መስተዳደር ነው ተብሏል።

Photo Credit : Demtsi Woyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #ባህርዳር

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ልዩነቶችን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር ለመፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት አለው " - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

ባህር ዳር የሚገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር እንዲሁም ከህብረተሰቡ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ " ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል " ብለዋል፡፡

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " ያሉ ሲሆን " አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው " ብለዋል፡፡

" የሁከት እና ግርግር አጀንዳዎች የሚታያቸው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ለሕዝብ ካሰብን እና ከሠራን ከሠላም ውጭ የተሻለ አማራጭ የለንም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው ፤ " ልዩነቶች ይኖራሉ  ያሉትን ልዩነቶችን ግን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር መፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት ነው ብለዋል።

" የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።

" የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ወደ ቀደመው ሁኔታው መመለስ አለበት፣ ትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርበታል " ያሉት ዶ/ር ይልቃል " ተከባብረን እና ተደማምጠን ልዩነቶቻችን ለመፍታት መሥራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

የፖለቲካ አመራሩ የጀመረውን የሠላም ግንኙነት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በተለይ ደግሞ አዋሳኝ አካባቢ ያሉ የሁለቱም ክልል ሕዝቦች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Via AMC

@tikvahethiopia