TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ስለማለፉና ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል። በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል። ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ…
" የፀጥታ ኃይሎች ቀውሱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች ሊቆጠቡ ይገባል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፤ ዛሬ ከጁሙዓ በኋላ በንፁሃን ሰጋጆች ላይ በተወሰደው የኃይል እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች ላይ ጉዳት መድረሱን ገለፁ።

ከአንድ ሰዓት በፊት ባሰራጩት መልዕክታቸው ፤ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያልቻሉ ብዙ መሆናቸውንና ይህንን ቀውስ ለመፍታት በአስቸኳይ አምቡላንስ መግባት እንዳለበት አሳስበዋል።

" የፀጥታ ኃይሎች ቀውሱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች በመቆጠብ ወደቦታው የመጅሊስ አመራሮች እና የሙስሊሙ የማህበረሰብ መሪዎች እንዲገቡና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ሊፈቅዱ ይገባል " ብለዋል።

በጥይት ተመትተው ደማቸው እየፈሰሱ ያሉ ሙስሊሞች እርዳታ ሊያገኙ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለጁምዓ ሰላት ወደ አንዋር መስጂድ ገብተው ከመስጂድ ውስጥ እንዳይወጡ መንገድ የተዘጋባቸው ምዕመናን እስካሁን መውጣት እንዳልቻሉ ተነግሯል።

የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሙስሊም ምሁራን  በአካባቢው ተገኝተው የማረጋጋት ስራና በመስጂድ ውስጥ ያሉትን ምዕመናን ለማስለቀቅ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን ዛውያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በአንዋር መስጂድ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናን የአስር ሰላታቸውን በሰላተል ኸውፍ ዲናዊ ስርአት ሰግደው በመስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ ተብሏል።

ሰዓቱ እየመሸ ስለሆነ መጅሊስ እና የሚመለከተው አካል ሁሉ የበኩሉን እንዲወጣና መንገዱ ተከፍቶ እንዲወጡ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ስለማለፉና ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል። በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል። ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ…
#Update

ኡስታዝ ሐሰን ታጁ (አምባሳደር) ፤ " የኃይል እርምጃ በየትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የለዉም " አሉ።

ኡስታዝ ሐሰን " በዛሬዉ ዕለት በታላቁ አንዋር መስጂድና በሌሎች መስጂዶች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የወሰዱት የንጹሀን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈና ያቆሰለ የሀይል እርምጃ በየትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የለዉም " ብለዋል።

" እንዲህ ዓይነት ያልተገቡ እርምጃዎች ቀዉስን በማባባስና የማህበረሰቡን ምሬት በመጨመር በሀገር ላይ አደጋ የሚደቅኑ አላስፈላጊ ዉጤቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚመለከተው አካል ሊረዳ በተገባ ነበር፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል። በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ #የማይገኙ ሁሉም የዲግሪ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን፣ ክረምት) እንዲሁም የማስተርስ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን ፣ ክረምት) ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል። ሊንክ ፦ http://196.190.28.50…
#Update

ራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል ቀደም ሲል ዩኒቨርሲቲዉ ባወጣዉ ማስታወቅያ መሰረት የተመዘገቡ (የዩኒቨርሲቲዉና ከሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያመለከቱ) ተማሪዎች ሰኔ 6 እና 7 / 2015 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፀጥታ ኃይሎች ቀውሱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች ሊቆጠቡ ይገባል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፤ ዛሬ ከጁሙዓ በኋላ በንፁሃን ሰጋጆች ላይ በተወሰደው የኃይል እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች ላይ ጉዳት መድረሱን ገለፁ። ከአንድ ሰዓት በፊት ባሰራጩት መልዕክታቸው ፤ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያልቻሉ ብዙ መሆናቸውንና ይህንን ቀውስ ለመፍታት በአስቸኳይ አምቡላንስ መግባት እንዳለበት አሳስበዋል።…
ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ አንዋር መስጂድ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ በአሁን ሰአት አንዋር መስጂድ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በሰዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች እንዳይባባሱ እና በመስጂዱ ጊቢ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ሲል ከፍተኛ ምክር ቤቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ አንዋር መስጂድ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ በአሁን ሰአት አንዋር መስጂድ እንደሚገኙ ተገልጿል። ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በሰዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች እንዳይባባሱ እና በመስጂዱ ጊቢ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ሲል ከፍተኛ…
#Update

በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ መቆየታቸው ተሰምቷል።

በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉም ተብሏል።

ታላቁ አንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።

ከሁሉም ነገር በፊት #ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይልም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

(ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ መቆየታቸው ተሰምቷል። በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ…
#Update

" በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ም/ቤቱ አሳውቋል።

የጁመዓ ሰላት ለመስገድ በአንዋር መስጂድ የተገኙና በተፈጠረው ችግር ምክንያት በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታግተው የቆዩ ምእመናንም ወደየቤታቸው #በሰላም ሸኝተዋል።

አንድም ሰው እንዳልቀረ ካረጋገጡ በኃላ አመራሮቹ የመስጂዱን ቅጥር ጊቢ ለቀው መውጣታቸው ተገልጿል።

ከፍተኛ ም/ቤቱ ፤ " ለሞቱት ጀነት እንዲወፍቃቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለተጎዱትም ቶሎ ማገገምን ይቸር ዘንድ አላህን እንጠይቃለን " ብሏል።

በቀጣይ ህዝበ ሙስሊሙ እየተፈፀሙበት ያለውን አላግባብ የመብት ጥሰቶች በተገቢው መልኩ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉበኤ ውሳኔ መሰረት የተቋቋመውን ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴን እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚሰጠውን አቅጣጫ እንደ መሪ ተቋም በማክበር ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሆስፒታል…
መንግሥት ምን አለ ?

መንግሥት በታላቁ አንዋር መስጂድ " ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ " የሚንቀሳቀሱ #የሴራ_ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በተነሳ ረብሻ የሰው ህይወት መጥፋቱን እና ጉዳት መድረሱን ገለፀ።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ መስጅዶች የተካሄደው የጁምአ ሶላት በሰላም ተጠናቋል ብሏል።

በታላቁ አንዋር መስጅድ የጁምዓ ሶላት በሰላም ተጠናቆ ህዝብ ሙስሊሙ እየተመለሰ ባለበት ሁኔታ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ " ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ " የሚንቀሳቀሱ #የሴራ_ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ በተነሳ ረብሻ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

በንብረት ላይም እስከ አሁን ግምቱ ያልተወቀ ኪሳራ ደርሷል ያለው ግብረኃይሉ ለፀጥታ ሥራ በተሰማሩ 63 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጿል።

ግብረ ኃይሉ " ፀረ-ሰላም ኃይሎች " ሲል የጠራቸው አካላት የእምነቱ ተከታዮች በህጋዊ መንገድ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጥለፍ የራሳቸውን እኩይ ዓላማ ለማሳካት ረብሻውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት ያደረጉት ጥረት የፀጥታ ኃይሉ፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና የሀይማኖቱ አባቶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል።

ግብረ-ኃይሉ ፤ የከተማውን ብሎም የሀገሪቱን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ #አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እና በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ " ፀረ-ሰላም ኃይሎች " ላይ የጀመረውን ምርመራም በመቀጠል በቀጣይ ውጤቱን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

የብርሃን ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎትን ለማግኘት https://berhanonline.et 👈👈ሊንኩን በመጫን ካሉበት ሆነው ክፍያ፤ ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አቅራቢያዎ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች ጎራ ይበሉ
#internetbanking #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://publielectoral.lat/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግሥት ምን አለ ? መንግሥት በታላቁ አንዋር መስጂድ " ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ " የሚንቀሳቀሱ #የሴራ_ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በተነሳ ረብሻ የሰው ህይወት መጥፋቱን እና ጉዳት መድረሱን ገለፀ። የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ፤ ዛሬ ግንቦት…
ፎቶ፦ በአዲስ አበባ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ ምዕመናን ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፀመ።

ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው በኮልፌ መካነ መቃብር ሲሆን በስርዓተ ቀብሩ ላይ እጅግ በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ ተገኝቶ ነበር።

በዛሬው ዕለት ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው ዘቡር ሙደሲር፣ አንዋር ሱሩር፣  ኢብራሂም ደንበል፣ ጀሚል ሪድዋን ናቸው።

ጀሚል ሪድዋን ባለፈው ሳምንት በአንዋር መስጅድ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ህይወቱ በማለፉ በዛሬው እለት ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል።

Credit : Harun Media

@tikvahethiopia