TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቴዎድሮስ ካሳሁን⬆️

ለአዲስ አመት #ዋዜማ በሚሊኒም አዳራሽ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት የተስተጓጎለበት #ቴዲ_አፍሮ አሁን መስከረም 5 ቀን 2011 ኮንሰርቱን ለማድረግ መወሰኑ ታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ለሚሊየም አዳራሽ አስፈላጊውን ክፍያ መፈፀሙ ታውቋል፡፡

ቴዲ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማቅረብ ጠይቆ አዳራሹ ለሌላ #ፕሮግራም ይፈለጋል ተብሎ #ሳይፈቀድለት መቅረቱ ይታወሳል።

©z
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሊሰረዝ ነው⬇️

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የታቀደው ኮንሰርት #ሊሰረዝ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹልኝ ብሏል።

እንደ ዘ-ሀበሻ ምንጮች ዘገባ #ቴዲ ለአዘጋጆቹ "በዚህ የሃዘን ወቅት መድረክ ላይ ወጥቼ የመዝፈን አቅም የለኝም - አልችልምም" ብሏቸዋል ተብሏል።

ድምጻዊው ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሊደረግ የነበረ ሲሆን ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ፊታችን #ቅዳሜ ተዘዋውሮ ነበር።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይኸው ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ የማይካሄድ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ እንደማይታወቅ ታውቋል።

ሰው እየሞተ መዝፈን አልችልም ያለው ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ጠዋት በመድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት በቡራዩና በአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን እንደሚጎበኝ በተጨማሪም የገንዘብ እርዳታ እንደሚያደርግ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

@tsegabwklde @tikvahethiopia
ቴዲ አፍሮ!!

ዝነኛው ድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ (#ቴዲ_አፍሮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናትን ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ በቅርቡ #ነፃ የሙዚቃ ኮንሰርት ያዘጋጃል።

ምንጭ፦ ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia