TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ የከተማው ህዝበ ሙስሊም የነገን #ጁመአ በሰላም እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ (ሲቲ) የመስጅድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ያቀረበውን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ማለትም የመስጅድ ፈረሳው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ፣ የፈረሱ መስጅዶችም ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለስ መጅሊስ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም በጉዳዩ ዙሪያ በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል ብሏል።

" መንግስትም የፍትህን መጓደል የጥያቄውን አሳሳቢነት፣ በሸገር ሲቲ አስተዳደር በውይይት ላይ ያልተመሰረተን አካሄድን ከግንዛቤ በማስገባት ለተከሰተው የመብት ጥሰት ፍትህ የማስፈን ሚናውን በአፋጣኝ እንደሚወጣ ተስፋ እናደርጋለን " ያለው ምክር ቤቱ ህዝቡ ኮሚቴው የደረሰበትን እስኪያሳውቅ ድረስ  ውጤቱን በትእግስትና በዱአ እንዲጠባበቅ  ጥሪ አቅርቧል።

የነገ የጁመአ ሰላት መላው የከተማው ሙስሊም በሁሉም መስጅዶች በሰላም ሰግዶ ወደ ቤቱ በሰላም እንዲመለስ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በከተማው የሚገኙ ኢማሞች በሰላምና በትእግስት ዙሪያ የጁመአ ኹጥባ እንዲያደርጉ ማሳስቢያ ተላልፏል።

መንግስትም ጉዳዩን በፍጥነት እልባት እንዲሰጥ እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከእስር እንዲለቅ ምክር ቤቱ አጥብቆ ጠይቋል።

ባለፈው ሳምንት ጁመአ በሸገር ከተማ አስተዳደር ከሚደረገው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ምዕመናን የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ፤ የምዕመናን ህይወት ማለፉ ፣ ጉዳትም መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም።

(ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia