TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
👏 #ሲፈን_ተክሉ የአዲስ አበባዋ ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 575 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። ሲፈን የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት። ተማሪዋ " ጌዜን ትምህርት ላይ ማሳለፌ ፣በቡድን ማጥናቴ ፣ የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል " ብላለች። ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ሲፈን የስርዓተ ምግብ…
#ደሴልዩአዳሪትምህርትቤት👏

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ ፤ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደግሞ ሁለተኛ ነው ” - የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

በ2016 ዓ/ም አገር ዓቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኢትዮጵያ በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአማራ ክልል፣ የይሁኔ ወልዱ ደሴ መታሰቢያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ነው፡፡

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው ትምህርት ቤቱ፣ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 574 መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህን ውጤት ያስመዘገው ተማሪ ጌታቸው እያዩ ይባላል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 562 መሆኑን ትምህትር ቤቱ ገልጿል፡፡

በትምህርት ቤቱ በሴቶች የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 546 ነው፡፡ ውጤቱ የተመዘገበው በሀያት አብዱ ነው።

የተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ደግሞ 458 ነው፡፡

ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ያስፈተናቸው ተማሪዎች ብዛት 65 ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 45 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል፡፡

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ ነው፡፡ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ሁለተኛ ነው ” ሲል ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

አክሎ፣ “ አጠቃላይ ውጤት የሚባለው፣ አንደኛ ትምህርት ቤቱ ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ሲያሳልፍ፣ ሁለተኛ ደግሞ የተማሪዎቹ ውጤት ተደምሮ ሲካፈል ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤቱን ማንም ትምህርት ቤት አይበልጠውም አንደኛ ነው ” ብሏል፡፡

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ፤ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደግሞ ሁለተኛ ነው ” ነው ሲል ገልጿል፡፡

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የሚገኝበት የአማራ ክልል ዘንድሮ በብዙ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ውስጥ እያለፈ ያለ ክልል ነው።

ባለፉት ዓመታትም ክልሉ በጦርነትና የከፋ የፀጥታ ችግር ላይ ሆኖ እንኳን የሀገሪቱን ከፍተኛ ውጤቶች ያስመዘገቡ ተማሪዎች የወጡበት ነው።

ዘንድሮም ከሀገር ሁለተኛው ከፍተኛ ውጤት በዚሁ ክልል ተመዝግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia