TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋ እና የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው በጥናት አረጋግጠናል " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጠን ጋር በመሆን በተሽከርካሪዎች ግብይትና አሰራር ዙሪያ ትላንት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው የተሽከርካሪዎች ግብይት መሬት ላይ ያለው እውነታንና መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ መሠረት ያደረገ ጥናት ሲካሄድ መሠንበቱን ገልጿል።

በዚህም መነሻ ከአስመጪዎችና ከዘርፉ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንና ማንም በገበያ ዋጋ ደረሰኝ እንዲቆርጥና ገዢውም ትክክለኛ ደረሰኝ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት እንዳለበት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።

" መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ ለማግኘት ከግንቦት 03/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ  ወደ ተግባር ገብቷል " ያለው የአ/አ ገቢዎች ቢሮ " የህግ ማስከበር ስራዎች ተጠናክረው ስለሚቀጥሉ ገዢ ላወጣው ለከፈለበት ትክክለኛ ደረሰኝ መቀበል ፣ እንዲሁም ሻጭ ለሸጠበት ትክክለኛ ደረሰኝ መስጠት ይኖርበታል ፤ ሲጠየቁም ይህንን ትክክለኛ የግብይት ደረሰኝና የሂሳብ መዝገቦች ማቅረብ አለባቸው " ሲል አስገንዝቧል።

አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋ እና የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው ጥናት በማድረግ አረጋግጠናል ያለው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገዢዎች ይዘውት የሚመጡት ደረሰኝ መሬት ላይ ያለውን ትክክለኛ የተገዛበትን ዋጋ መሆን እንዳለበት እና ሲገዙም በትክክል ያወጡበትን ዋጋ መቀበል አለባቸው ብሏል።

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ፤ በየአመቱ ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ መኪኖች እንደሚመዘገቡ ጠቁሞ ከዚህም መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እያገኘ እንዳልሆነ ጥናቶች በተጨባጭ አረጋግጠዋል ሲል አሳውቋል።

በተቋሙ ማንኛውንም አገልግሎት የሚፈልግ ሰው ለገዛው የመኪና ዋጋ ትክክለኛ ደረሰኝ ይዞ መገኘት አለበት ስሊ ያሳሰበው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ ካልሆነ ግን በተጠናውና ወደ አሰራር በተገባው መሠረት የሚጠበቅበትን ከፍሎ አገልግሎት ያገኛል ባቧል።

በዘርፉ የመንግስትን ጥቅም ለማስከበር ሁለቱም ተቋማቶች በጋራ እየሰሩ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ፦ ገዢም ሆነ ሻጭ ትክክለኛ የሂሳብ መዝገብ ፣ ትክክለኛ ደረሰኝ መቁረጥ እና ወደ ህጋዊ አሰራር መግባት  እንደሚኖርባቸውና ትክክለኛ ዋጋ ባለማቅረብ እና ዝቅ አርጎ ዋጋን ማቅረብ ስለሚያስጠይቅ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ በአፅንኦት አሳስበዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
We Are Hiring!
Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Electrician II
2. Network Engineer III
3. Network Engineer II
4. Security Engineer II
5. Compute Infrastructure Engineer II
6. Compute Infrastructure Engineer III
7. Database administrator III
8. Database administrator II
9. Database administrator I
10. IT Project Officer III
11. IT Project Manager
Use the link below to apply for the vacancy
Link; https://publielectoral.lat/berhanbanksc
የስራ ጥቆማ !

ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት #ጋዜጠኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል : https://careers.bbc.co.uk/job/Nairobi-Journalist-BBC-Amharic-Service-Nair-0-0100/771280902/
#ስፖርት

በመላው ዓለም እጅግ ከፍተኛ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ፍልሚያ የ " 2022/23 የውድድር ዓመት " ሻምፒዮን #ማንችስተር_ሲቲ መሆኑ ዛሬ ቅዳሜ ተረጋገጠ።

ማንችስተር ሲቲዎች ምንም እንኳን በውድድር ዓመቱ ቀሪ ጨዋታዎች ቢኖራቸውም ብርቱ ተፎካካሪያቸው #አርሴናል ዛሬ በኖቲንግሃም ፎረስት መሸነፉን ተከትሎ የዋንጫው ባለቤት መሆናቸውን ከወዲሁ አረጋግጠዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉ ሻምፒዮናነትን ሲያሸንፉ በክለቡ ታሪክ ዘጠነኛው ሆኗል።

ተጨማሪ ፦ https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አደጋው ትላንት 1 ሰዓት ከ20 ላይ በዶዶላ ማዕከል ለማስተማር መምህራንን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ " ሰብስቤ ዋሻ " የሚባል አካባቢ ገደል ውስጥ ገብቶ መድረሱን ያብራራቱ ፕሬዜዳንቱ " አደጋው እጅግ በጣም አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

አደጋው እንዴት ሊደርስ ቻለ በሚለው ጉዳይ ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተጠየቁት ዶ/ር ኢብራሂም " መኪናው ገደል ውስጥ የገባበት ቦታ በተደጋጋሚ መሰል አደጋዎች የሚደርሱበት ቦታ ነው ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከአደጋው የተረፉና ህክምና ላይ ያሉ መምህራኖቻችን ናቸው እንዴት የተፈጠረ የሚለውን መረጃውን መስጠት የሚችሉት " ብለዋል።

" በአካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ግን መኪናው አደገኛ ኩርባ አለች እሱን ጨርሶ እንደወረደ ቀጥታ እንደገባ ነው የነገሩን " ሲሉ አክለዋል።

በአደጋው እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን የገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከጉዳት የተረፉ በዶዶላ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ሆስፒታሎች ህክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በህክምና ላይ ካሉት ቀላል ጉዳት እንዲሁም ከባድ ጉዳት የደረደባቸው ያሉ ሲሆን ተቋሙ እነሱን እየተከታተለ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ህይወታቸው ያለፈውን ወደ ጎባ ሆስፒታል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው " በብዛት የባሌ አካባቢ ተወላጆች ስለሆኑ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው ቤተሰቦቻቸው ወስደወል፤ ራቅ ራው ካሉ አካባቢዎች የመጡ መምህራኖቻችንን ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሽኝት እንዳረጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ለማስተማር ወደ ዶዶላ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ 19 የዩኒቨርስቲው #መምህራን#ሠራተኞች እና #ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

28 የሚሆኑ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ አብረውት ለነበሩት የምዕራብ አርሲና የባሌ ዞኖች፣ የሻሸመኔ፣ አዳባ፣ ዶዶላና ሮቤ ከተሞች ነዋሪዎችና አመራሮች ዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች በተለይ አደጋው የተፈጠረበት አከባቢ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ሲቢኢ ብር - ለቀላል፣ ፈጣን፣ አስተማማኝ የነዳጅ ግብይት!
=================
ደንበኞች ወደ ነዳጅ ማደያ ከመምጣታቸው አስቀድመው

• የሲቢኢ ብር አገልግሎታቸው በአግባቡ እንደሚሠራ ቢያረጋግጡ፣
• ሲቢኢ ብርን መጠቀም ካልጀመሩም ወደ *847# በመደወል፣ ወይም የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራሳቸው ተመዝግበው፤ እና
• በሲቢኢ ብር አካውንታቸው በቂ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጠው ቢመጡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

ስለ ሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!
*********************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#እግድ

" የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በሀገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል እንደሆነም ገልጿል።

ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ማህበረ ቅዱሳ ቴሌቪዥን ጣቢያ በመገናኛ መረቡ " ሰበር ዜና " በሚል ያሰራጨው " ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግርን ለመቅረፍ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ " በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ አወጥቶታል ያለውን መግለጫ ነው።

https://www.facebook.com/100069179198602/posts/pfbid0kKRZfaiNWQpCJpyUSuuNWtyXNHahgy1DZH4DUMudijNXNbcu8N7G1CGUP73Y6e9dl/?app=fbl

የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከቀናቶች በፊት ተጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን በየዕለቱ በቤተክርስቲያኗ ቴሌቪዥን ዕለታዊ መረጃዎች/ውሳኔዎች ሲተላለፉ ነበር ፤  እስከ ዛሬ ድረስ ጉባኤው መቋጫ አግንኝቶ #በቅዱስ_ሲኖዶስ በኩል ለምዕመኑ የተሰጠ አጠቃላይ መግለጫ የለም።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

በድሬደዋ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን ተከትሎ የከተማው ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።

በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው (ከፍተኛ ደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአእምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፤

2. ቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፤

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፤

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፤

5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፤

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፤

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፤

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፤

9. የተለያየ ህመም  ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ማድረግ፣ የታዘዘውን መድኃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ባልደራስ

ከዚህ ቀደም ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ ተከልክሎ እንደነበር የገለፀው ባለደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ፥ አቶ አምሃ ዳኜው ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

አቶ አማሃ ዳኜው ፤ ፓርቲውን በም/ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ ነበሩ። ዛሬ በአብላጫ ድምፅ አቶ ለቀጣይ 3 አመታት በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ #ሀገራዊ_ፓርቲ ለመሆን ውሳኔ አሳልፏል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ ምንም እንኳን ኢትዮጵያዊ ሀሳቦችን እያነሳው የታገልኩኝ ቢሆንም ባለኝ ፍቃድ መሰረት ግን መንቀሳቀስ የቻልኩት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው ብሏል።

የዛሬው ጉባኤ ፓርቲው ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን የሚያስፈልጉ ቅድመ ተግባራትን እያከናወነ እንዲቆይ እና ከወራት በኋላ በሚደረገው ጉባኤ ወደ ሀገር አቀፍነት እንዲያድግ ያለ ተቃውሞ እና ድምፀ ታቅቦ መፅደቁ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላላ ጉባኤው ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ከውህደት-መለስ አብሮ እንዲሰራ ፈቅዷል።

ነገር ግን ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት የፓርቲው ምክር ቤት እንዲወስን ጉባኤው ፍቃድ ሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት መርምሮ እና አጥንቶ ለፓርቲው ምክር ቤት እንዲያቀርብ፤ እንዲሁም ም/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ የሚያቀርብለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንዲያፀድቅ ወስኗል።

መረጃው ከፓርቲው ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
" በህግ ማስከበር ስም የድሆችን ቤት እና ቤተ እምነቶችን ማፍረስ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " - ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በአዲስ መልክ በመደራጀት ላይ ባለው " ሸገር ከተማ " ባለፉት ጥቂት ወራት ህገ ወጥ ግንባታዎችን ለመከላከል በሚል በተወሰደው እርምጃ በርካታ ቤቶች በመፍረስ ላይ እንዳሉ እንደሚታወቅ እና እርምጃው ዛሬም ድረስ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

ፓርቲው እየተወሰደ ባለው እርምጃ በርካታ ቤቶች እንዲፈርሱ የተደረገ መሆኑንና በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሚያሳዝን ሁኔታ ጎዳና ላይ እንዲወድቁ መደረጉን አመልክቷል።

እርምጃው ቤታቸው በፈረሰባቸው ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና እንግልት ከማሳደሩም ባሻገር፣ የማፍረስ ሂደቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል ሲልም አክሏል።

ነእፓ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጫለሁ እንዳለው ቤት የማፍረስ እርምጃው ህጋዊ ፍቃድ የሌላችውን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ዜጎች ጭምር ሰለባ ያደረገ መሆኑና ይህም ቤት የማፍረስ እርምጃው ዓላማ ግልጽነት የጎደለው እንዲሆን ማድረጉን ገልጿል።

" የማፍረስ እርምጃው ከዜጎች የመኖሪያ ቤት በተጨማሪ የእምነት ተቋማትን ኢላማ ያደረገ ነው " ያለው ነእፓ " በዚሁ ሳቢያ በርካታ #መስጂዶች መፍረሳቸው ተረጋግጧል፡ " ብሏል።

ይህ እርምጃ ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ተጠያቂነት የጎደለው ተግባር ከመሆኑ ባሻገር የእምነት ተቋማትን ክብር ያጎደፈ እና መንግስት ለምእመኑ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ሲል ገልጿል።

ነእፓ ፤ " አብዛኛው የሀገራች ህዝብ በአስከፊ ድህነት ውስጥ እየኖረ ባለበት፣ የእለት ጉርስ እና የአመት ልብስ ማግኘት ህልም በሆነበት፣ ዳቦ፣ ዘይት እና ስኳር ቅንጦት በሆነበት፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በጦርነት እና በግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ባሉበት ሀገር ያለ በቂ ጥናት እና ዝግጅት የዜጎችን ቤት በጅምላ ማፍረስ በህግም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የሌለውና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብሏል።

" በሀገራችን ተንሰራፍቶ በቆየው ብልሹ አስተዳደር ሳቢያ፣ እንዲሁም መንግስት የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ ባለመቻሉ፣ ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከጸሀይ ሀሩር እና ከክረምት ዝናብ የሚከልሉበት ጎጆ እንዲቀልሱ ተገደው ኖረዋል " ያለው ፓርቲው " በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች በመንግስት #ደካማ እና #በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ምክንያት ዜጎች ለበርካታ አስርት አመታት ህጋዊ ይዞታ የሚያገኙበት ስርአት ሳይዘረጋላቸው ቆይቷል " ሲል ገልጿል።

ይህንን የመንግስት እንዝላልነት እና ብልሹ አሰራር ህግ እና ስርአት በጠበቀ መልኩ ማስተካከል ሲገባ፣ ዜጎች በሀብታቸው፣ በንብረታቸው እና በህይወታቸው ዋጋ እንዲከፍሉ ማድረግ ሰብአዊነት እና ኃላፊነት የጎደለው ታሪካዊ ስህተት ነው ብሏል።

" ቤት ማፍረሱ ሳያንስ፣ ዜጎች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ጎጆ በቂ ጊዜ እና አማራጭ የመኖሪያ ስፍራ እንዲያገኙ እድል ሳይሰጥ ' በጊዜ የለንም ' ፍጥነት ከመኖሪያ ደጃቸው እንዲነሱ የተደረገበት አሰራር ሂደቱን ይበልጥ አሳዛኝ፣ አሳሳቢ እና አጠያያቂ አድርጎታል " ያለው ነእፓ በአዲሱ የሸገር ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ፦
- በቂ ህጋዊ መሰረት የሌለው፣
- ከፍተኛ የአፈጻጸም ክፍተት ያለበት ፣
- የክልሉን ብሎም የሀገራችንን አሁናዊ የጸጥታ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ድርብርብ ችግሮች እና ሀቆች በቅጡ ያላገናዘበ በመሆኑ #በአፋጣኝ_እንዲቆም አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia