TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ወላጆች ምን አሉ ?

ወላጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ወቅቱን ያገናዘበ ፤ የኑሮ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ልጆቻቸውን በተለያዩ ት/ቤቶች የሚያስተምሩ ወላጆች ት/ቤቶች እየጨመሩ ያሉት ከፍተኛ ክፍያ እጅግ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ ሲሉ አሳስበዋል።

አንድ ወላጅ " በየት/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ እየተደረገ ነው ይህ በጣም ያማል " ያሉ ሲሆን " ኑሮ ለእነርሱ ብቻ የተወደደ እስኪመስል ድረስ 7000 ከሆነ 14,000 እየተጠየቀ ነው " ብለዋል።

እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት ከጭማሪው ጋር በተያያዘ ወላጆች ሳይስማሙ ስብሰባ መበተኑን አመልክተዋል።

" መንግስት ይህንን ጉዳይ አንድ ሊለው ይገባል ፤ አንዴ ወልደናቸዋል ምን እናድርግ ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

አንደንድ ወላጆች ፤ ይደረጋል በተባለው አግባብነት እና ልክ የሌለው የዋጋ ጭማሪ ልጆቻቸው ከሚወዱት ትምህርት ቤት እንዲያስወጧቸው ሊያደርግ የሚችል መሆኑን አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ከ1,500 በላይ ወላጆች መልዕክታቸውን የተቀበለ ሲሆን ወላጆች በላኩት መልዕክት ት/ቤቶች ከ20 በመቶ እስከ 100 በመቶና #ከዚያ_በላይ ጭማሪ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ወላጆች ስለ ት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ምን አሉ ?

----

የካ አባዶ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትም/ ቤት ልጃቸውን የሚያስትምሩ ወላጅ የልጃቸው ወርሃዊ ክፍያ 1450 ብር እንደነበና 65.7 በመቶ በመጨመር 2500 ብር እንደተደረገ ገልጸዋል። " ወላጆች እንዲጨምርብን አንፈልግም ነበር ግዴታ ከሆነም ከ30 በመቶ በላይ እንዳይጨምሩ ተከራክረን ነበር። " ያሉት እኚሁ ወላጅ " ት/ቤቱ ግን 80 በመቶ እንጨምራለን ብለው ወላጅ ባይስማማም 65.7 በመቶ ወስነዋል " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

----

" መንግስት ካለ ለምን መጨመር የሚቻለውን ከፍተኛ ተመን አይወስንም ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ የተማሪ ወላጅ " እመኑኝ በዚህ ሁኔታ ብዙዎች ት/ት ሊያቆሙ ይችላሉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

----

በአንድ የግል ት/ቤት ውስጥ ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ት/ቤቱ መንግስት ምንም ሊያስገድደው እንደማይችል እና ነፃ ገበያ እንደሆነ ተናግሮ ምንም ለውጥ እንደማናመጣ ነገረን ያሉ ሲሆን "  መንግሥት ስምምነት ሳይደረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም ማለቱ ተስፋ ሰጥቶናል " ብለዋል ፤ እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 78% መጨመሩንና በተርም / በሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀን 7600 እንከፍል የነበረውን 13324 ነው ያደረጉብን ሲሉ ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት የ65 በመቶ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን ገልጸው " በዚህ ኑሮ ውድነት ይህን ማድረግ ግፍ ነው ፤ የእኛ የወላጆች ገቢ ባላደገበት ይህ እንዴት ይድረጋል ፤ ለእኛስ አይታሰብም ወይ ? ሲሉ መልዕክታቸውን ልከዋል።

----

በኮ/ቀ በሚገኝ የአንድ የግል ትምህርት ቤት የወለጅ ኮሚቴ ነኝ ያሉ አንድ የቲክቫህ አባል " እንደ ኮሚቴ ተስማምተን የነበረው 200 እስከ 300 ጭማሪ ነበር ፤ ለምሳሌ በዚህ የት/ዘመን 1300 + 300 = 1600 ፤ 2016 ነበር የተስማማነው አሁን ግን 600 ጭማሪ አድርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል። " ይህ ለምን እንደሆና ምክንያቱን በግልፅ አላወቅንም " ያሉት እኚሁ የወላጅ ኮሚቴ " ለሚቀጥለው ዓመት 1900 ተብሎ በደብዳቤ አሰውቀውናል " ሲሉ አክለዋል። " ልጆቻችንን ከመስወጣተችን በፊት ትምህርት ቢሮ ክትትል ያድርግ !! " ሲሉ አደራ ብለዋል።

----

" መንግስት ውይይት ሳይደረግ መጨመር አይቻልም ብሏል ፤ ውይይት ሲባልስ #ስንት_ሠው_ተገኝቶ ነው ውሣኔ ማሣለፍ የሚችለው ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ ወላጅ " ይህ በራሡ #ክፍተት ያለው አገላለፅ ነው፤ እንዳሻችሁ እንደማለት ነውና መንግስት የኑሮ ጫና የሚፈታተንን ሳያንስ ሌላ ጫና ለመሸከም የሚችል ጫንቃ የለንምና ፤ የፈጠራትን ክፍተት መንግሥት ራሡ ይዝጋት እንላለን " ብለዋል። "

----

በአንድ የግል ት/ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ፤ ት/ቤቱ በቀጣይ አመት ከ1300 ባንዴ 2700 ጭማሪ ማድረጉን እና ያልፈለገ መልቀቅ ይችላል እንዳሏቸው ገልጸዋል። " በዛላይ ቀጣይ አመት በተርም ነው ምከፍሉት አሉን " የሚሉት ወላጅ " ሁለት ልጆቼን ለማስተማር 2600 ከፍዬም አንገዳግዶኝ ነበር የባሰው መጣና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ  " ብለዋል።

----

" እኔ ልጄን የማስተምርበት ት/ት ቤት ወደ 120% ነው የጨመረው " ያሉ አንድ ወላጅ " ከአንድም ሁለት ጊዜ ከት/ት ቤቱ አሰተዳደር ጋር ብንሰበስብም መስማማት ላይ ግን መድረስ አልቻልንም። " ብለዋል። " እንደውም ት/ት ቤቱ መጀመሪያ 22ዐ% ነበር ያቀረበው ከብዙ ክርክር በኋላ ነው ወደ 120% የወረደው ሆኖም ግን ከዚህ በታች አሻፈረኝ ብሏል። ብዙ ወላጅም በጣም ተማሯል። " ሲሉ ገልጸዋል።

----

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነኝ ያሉ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 40 % ጭማሪ መደረጉን ገልጸው በዚህ ኑሮ ውድነት ፤ በዛ ላይ ሁለት / 2 / እና ከዛ በላይ ልጆች ያሏቸው ምን ይሆናሉ ? ሲሉ ሁኔታው እጅግ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጆቻቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ከጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት እንደሌለ ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ግን " የፈለገ ልጆቹ ያስቀጥል፤  ያልተስማማ ሌላ ት/ቤት ይቀይር " የሚል ምላሽ መስጠቱን አመልክተዋል " መንግስት የሰጠው አቅጣጫ ወላጆች ሳይስማሙ ማለት የሹፈት ውሳኔ ነው ፤ ሌላ ትም/ቤት ፈልጉ ከተባለ ለልጃችን ስንል ሳንስማማ እንቀጥላለን ፤ #መንግስት ነው ይህን #መቆጣጠር ያለበት፤ እውነቴ ነው በዚህ አካሄድ ብዙ ልጆች ከትምህርት ውጪ ይሆናሉ። " ሲሉ ስጋታቸውን አስረድተዋል።

----

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ ወላጅ " ከክፍያ ጭማሪ በተያያዘ እኛ ወላጆች ምንም ባልተስማማንበት ሁኔታ ነዉ እየጨመሩ ያሉት ፤ በአካባቢያችን ከ50% በላይ ነዉ ጭማሪ የተደረገው እና የሚመለከተው አካል ከጊዜዉ ጋር ታሳቢ በማድረግ መፈትሔ እንዲሰጥ ። " ሲሉ ጠይቀዋል።

----

አንድ ወላጅ አምስት (5) ልጆቸውን በሚያስተምሩበት የግል ትምህርት ቤት በአመት አጠቃላይ 434 ሺህ ብር ሲከፍሉ እንደነበር አሁን ግን 100 % ጭማሪ (868,000 ብር) እንደሚደረግ እንደተነገራቸው ገልጸዋል ፤ መንግሥት በግል ት/ቤቶች እየተደረገ ያለውን ነገር እንዲከታተልና መፍትሄ እንዲፈልግ አደራ ብለዋል።

----

በአንድ የግል ትምህርት ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ትምህርት ቤቱ የ60,000 ሺህ ብር ጭማሪ ለማድረግ እንደወሰነና ለዩኒፎርም እና ለመሳሰሉት እስከ 30,000 ብር ጭማሪ እንደተደረገ አመልክተው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

(ተጨማሪ ወላጆች የላኩይ መልዕክት በዚሁ ፅሁፍ ላይ #edit ተደርጎ ይካተታል)

በአጠቃላይ እጅግ በጣም በርካታ የተማሪ ወላጆች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መልዕክታቸውን ልከዋል።

የወላጆቹ ሃሳብ ሲጠቃለል ፤ በዚህ የኑሮ ጫና ወቅት እጅግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መንቀሳቀስ በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውና ት/ቤቶችም ይህንን ተገንዝበው ማስተካከያ ማድረግ እንዳለብቸው የሚያሳስብ ነው።

ከምንም በላይ ደግሞ ፤ #መንግስት በሁሉም የግል ት/ቤቶች ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ወደ ምሬት ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን ማስቆም እንዳለበት የሚያገነዝብ ነው።

@tikvahethiopia
#CBEBirr

የሲቢኢ ብር ደንበኛ መሆን ቀላል ነው!
ባሉበት፣ በቀላሉ ይመዝገቡ!
=========
የነዳጅ ግዥ፣ የተለያዩ የአገልግሎት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችለው የሲቢኢ ብር አገልግሎትን እስካሁን መጠቀም ካልጀመሩ፣ አሁኑኑ የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ተጠቅመው ባሉበት በቀላሉ ደንበኛ ይሁኑ፡፡

ደንበኛ ለመሆን፡
• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራስዎ መመዝገብ ይችላሉ፡፡

በሲቢኢ ብር በቀን ውስጥ የሚያንቀሳቅሱትን የገንዘብ መጠን ገደብ ከፍ ለማድረግ ወደ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ አሊያም የሲቢኢ ብር ወኪል መታወቂያ ይዞ በመሄድ ምዝገባዎን ያጠናቁ!

****
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#AddisAbaba

ምንነቱ ያልታወቀ #ስራስር እና #ሰጋቱራ ከጤፍ ዱቄት ጋር ቀላቅለው ሲያከፋፍሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችን በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ህገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አጠራሩ ቆሼ  ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥ ነው።

በመጋዘኑ ውስጥ 47 ኩንታል ምንነቱ ያልታወቀ ስራስር፤ የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋ ቱራ) እና 167 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን ባዕድ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደባልቅ  መጋዘኑ ውስጥ እንዳይወጣ የተቆለፈበት ሠራተኛ በፍተሻ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በህግ አግባብ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በስራ ላይ የነበረውን ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረግው ተጨማሪ ምርመራ የንብረቱን ባለቤትን አፈላልጎ በመያዝ ተገቢው  ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ወላጆች ስለ ት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ምን አሉ ? ---- የካ አባዶ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትም/ ቤት ልጃቸውን የሚያስትምሩ ወላጅ የልጃቸው ወርሃዊ ክፍያ 1450 ብር እንደነበና 65.7 በመቶ በመጨመር 2500 ብር እንደተደረገ ገልጸዋል። " ወላጆች እንዲጨምርብን አንፈልግም ነበር ግዴታ ከሆነም ከ30 በመቶ በላይ እንዳይጨምሩ ተከራክረን ነበር። " ያሉት እኚሁ ወላጅ " ት/ቤቱ ግን 80…
#Update

እንደ የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መረጃ ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ 1,558 የግል ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1,257 ወይም 80.6 በመቶው የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል " አቅርበዋል።

- ባለስልጣን መ/ቤቱ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል" ካቀረቡት ውስጥ 1,031 ያህሉ ከተማሪ " ወላጆች ጋር ተስማምተዋል" ያለ ሲሆን 226 ትምህርት ቤቶች በጭማሪው መጠን ላይ እስካሁን " ከወላጆች ጋር መስማማት አልቻሉም ብሏል።

- ከወላጆች ጋር ተስማምተዋል ከተባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሃምሳ አንዱ 20 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ አቅደዋል። 394 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ከ21 እስከ 40 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ከወላጆች ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።

- 427 ትምህርት ቤቶች 41 እስከ 60 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል " ያቀረቡ ሲሆን  ፤ ከ61 እስከ 80 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ያቀዱት ትምህርት ቤቶች 126 ናቸው። እንዲሁም ከ81 እስከ 99 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ያቀዱ ትምህርት ቤቶች 24 ናቸው።

- መቶ በመቶ ጭማሪ ለማድረግ “ከወላጆች ጋር ተስማምተዋል " የተባሉ 5 ትምህርት ቤቶች ብቻ ሲሆኑ  ሌሎች 5 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ከ100 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ ለማድረግ አቅደዋል ተብሏል።

ሁሉም ትምህርት ቤቶች “ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርሱ” ጭማሪውን መተግበር እንደማይችሉ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ምን ያህል ወላጅ በተገኘበት ነው ውሳኔ የሚተለለፈው ?

እንደ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሰራር የትምህርት ተቋማት ሊያደርጉ ያሰቡትን ጭማሪ በተመለከተ ከተማሪ ወላጆች ውስጥ 51 በመቶ ያህል የሚሆኑት በተገኙበት ውይይት የማድረግ እና ተስማምቶ የመወሰን ግዴታ አለባቸእ።

የትምህርት ተቋማቱ በሚጠሩት የመጀመሪያ ውይይት ላይ የሚገኙ ወላጆች ብዛት ከ51 በመቶ በታች ከሆነ ስብሰባው ይበተናል።

ተቋማቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሚጠሩት ስብሰባ ላይ ግን ሊደረግ የታሰበው ጭማሪ በስፍራው በተገኙት ወላጆች መጽደቅ ይችላል።

መረጃውን የአ/አ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣንን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድርገፅ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እንደ የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መረጃ ፦ - በአዲስ አበባ ከተማ 1,558 የግል ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1,257 ወይም 80.6 በመቶው የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል " አቅርበዋል። - ባለስልጣን መ/ቤቱ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል" ካቀረቡት ውስጥ 1,031 ያህሉ ከተማሪ " ወላጆች ጋር ተስማምተዋል"…
#Update

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፥ የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ከተማሪ ወላጆች መጠየቅ እንደማይችሉ አስታውቋል።

በከተማዋ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ 1 ሺህ 253 የግል ት/ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

የግል ትምህርት ቤቶች ዋጋ የሚጨምሩባቸው ምክንያቶች ፦
- ግብዓቶችን ለማሟላት፣
- ለአስተዳደራዊ ወጭዎች እና የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለማስቀጠል ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ሲል አመልክቷል።

የዋጋ ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው ግን ወላጆች እና ትምህርት ቤቶች ተወያይተው ሲስማሙ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ትምህርት ቤቶች የወላጆችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ክፍያ እንዲያቀርቡ እና ወላጆችም ሁኔታውን አይተው ተግባብተው ሰላማዊና ስኬታማ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ባለስልጣን መ/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በዓይነትም በገንዘብም ግብዓቶችን ለማሟላትና ለተለያዩ ጉዳዮች ተጨማሪ እንደሚጠይቁ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ምንም አይነት ተጨማሪ ጥያቄ ማቅረብ እንደማይቻል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚያወጣው ጊዜ #ከሐምሌ ወር በኋላ መሆኑን ማመልከቱን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#AdigratUniversity

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በላከልን መልዕክት ፦

1. የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች ሆናችሁ ላላፉት ሁለት ዓመታት በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ የመማር እድል ያላጋጠማችሁ፤

2. በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች፤

3. በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛነት ስትማሩ ቆይታችሁ፣ ላለፉት ሁለት አመታት አቛርጣችሁ አሁን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለመመዝገብ የምትፈልጉ ተማሪዎች፤

በዚህ ማስፈንጠሪያ http://197.156.104.178/ በኦንላይን የቅድመ ምዝገባ ቅፅ ከግንቦት 03 አስከ 15/2015 እንድትሞሉ ጥሪ አቅርቦላችኃል።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የሚጀመርበት ቀን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይፋ አደርጓል። የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተገልጿል። ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ዲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ…
" ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ይስተካከል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል ፈተና መስጫ ቀን እንዲስተካከል ለከተማው ትምህርት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

የከተማው ትምህርት ቢሮ የ2015 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 19-20/2015 ለመስጠት መታቀዱን ማሳወቁ ይታወሳል።

ነገር ግን ይህ ቀን በካላንደር ዝግ የሆኑ የህዝብ በዓላትን ባገናዘበ መልኩ የወጣ እቅድ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አስገንዝቧል።

ምክር ቤቱ ፤ " በካላንደር ዝግ የሆኑ የህዝብ በዓላትን ባገናዘበ መልኩ እቅድ ማዘጋጀት የቢሮው ሃላፊነት ቢሆንም ሰኔ 21 እና 22/2015 የአረፋና የዒድ አልአድሀ በዓል ቀን እና ዋዜማ ፈተና ለመስጠት ማቀድ አግባብነት የለውም " ብሏል።

እቅዱ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተና ላይ እንዳይቀመጡ የሚያደርግ ተግባር ነው ሲልም ኮንኖታል።

የፈተናው ቀን ከዒድ አልአድሐ በዓል ከ3 ቀናት በፊት ወይም ከ3 ቀናት በኃላ እንዲሆን ይህም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል። ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል። ምን አሉ ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና…
" የተከፋፈለ ሲኖዶስ የለም "

የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ጉባኤ ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

ይህ አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው በሁለተኛው ቀን በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች መወያያየቱን ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚነት በሀገር ሰላም ዙሪያ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጉባኤው ብዙ ሲወያይ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም " ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ማድረግ ትችላለች ፤ ምእመናንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ይሰማሉ " የሚለው ሐሳብ አሸንፎ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው የሚሰሩ ሦስት ብፁዓን አባቶች ተመርጠው የሀገር ሰላምን በተመለከተ ረዥም ርቀት በመሔድና ከሚመለከተው አካል ጋር ሁሉ በመነጋገር በሀገር ሰላም ዙሪያ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና አሁን ካለንበት መከራ የምንወጣበትን መፍትሔ እንዲያመጡ ተመርጠዋል።

በቀጣይነት በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲን ችግር አስመልክቶ በትግራይ እና በኦሮሚያ አህጉረ ስብከት የነበሩትን ችግሮች መነሻ በማድረግ ፦

ሀ/ በክልል ትግራይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የትግራይ አባቶችና አባላቱን በአካል ለማነጋገር በቋሚ ሲኖዶስ የተመረጠውን ኮሚቴ ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ የጀመረውን ሥራ እንዲቀጥል ወስኗል።

በተጨማሪም ፦

👉 ተቋርጦ የነበረው በጀት እንዲለቀቅ፤

👉 የማጽናኛ መርሐ ግብር እንዲካሄድና በተቻለ መጠን አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ በጉባኤው ተወስኗል።

ለ/ በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የተከሰተውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በተመለከተ ሰፊ ውይይት ከተደረገ እና ወደ መግባቢያ ሐሳቦች መደረሱ ተገልጿል።

በስድስት አኅጉረ ስብከቶች ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየተሰጠ አለመሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ
የማያዳግም የመፍትሔ ለመስጠት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ከሦስቱ ብፁዓን አባቶች ጋር አራት ብፁዓን አባቶችን ተጨማሪ በማድረግ
በቀጥታ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉንና ከአንድ ሲኖዶስ ውጪ ሌላ አለመኖሩን ለመንግሥት አካላት በጋራ ሔደው የተደረሰበትን ስምምነት ተገቢውን መረጃ እንዲሰጡ ፦
- ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስን
- ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልን
- ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን
- ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን
- ብፁፅ አቡነ ሳዊሮስን
- ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን እና ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስን
በመመደብ እነዚህ ሰባት ብፁዓን አባቶች በአንድ ላይ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ፍጹም በሆነ የመግባባት ስምምነት መፈጠሩን ገልጸው ከእንግዲህ በኋላ የተከፋፈለ ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ የሆነ መሆኑን በአንድነት ለመንግሥት እንዲያሳውቁ መወከላቸው ተገልጿል።

ብፁዕነታቸው " በቀጣይ ያሉንን የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች በዚህ መልኩ በመግባባትና በመተማመን በመፍታት በሀገርና በቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነትን በማያዳግም ሁኔታ የሚያውጅ ቆይታ ይሆን ዘንድ መላው ሕዝበ ክርስቲያን በጸሎት አስቡን " ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውንና ቡራኬአቸውን ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ጊዜ ገና ብዙ ያሳየናል !

አፖሎን ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርገው የጣት አሻራዎን በመጠቀም የባንክ ሒሳብዎን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ ማስቻሉ ነው።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
ዘማሪት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ዘማሪት ሂሩት ዘማሪ ከመሆኗ በፊት በህዝብ ዘንድ ዛሬም ድረስ የሚደመጡና የሚወደዱ እጅግ በርካታ የዘፈን ስራዎች ነበሯት።

ከዘፈን ዓለም ወጥታ ወደ መንፈሳዊ ዓለም ከገባች በኃላ የተለያዩ የመዝሙር አልበሞችን ሰርታ ለአድማጭ አቅርባለች።

ዘማሪ ሂሩት ዛሬ በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች ሲሆን ፤ የ7 ልጆች እናት ፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

@tikvahethiopia