TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እንደ የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መረጃ ፦ - በአዲስ አበባ ከተማ 1,558 የግል ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1,257 ወይም 80.6 በመቶው የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል " አቅርበዋል። - ባለስልጣን መ/ቤቱ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ " ፕሮፖዛል" ካቀረቡት ውስጥ 1,031 ያህሉ ከተማሪ " ወላጆች ጋር ተስማምተዋል"…
#Update

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፥ የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ከተማሪ ወላጆች መጠየቅ እንደማይችሉ አስታውቋል።

በከተማዋ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ 1 ሺህ 253 የግል ት/ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

የግል ትምህርት ቤቶች ዋጋ የሚጨምሩባቸው ምክንያቶች ፦
- ግብዓቶችን ለማሟላት፣
- ለአስተዳደራዊ ወጭዎች እና የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለማስቀጠል ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ሲል አመልክቷል።

የዋጋ ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው ግን ወላጆች እና ትምህርት ቤቶች ተወያይተው ሲስማሙ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ትምህርት ቤቶች የወላጆችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ክፍያ እንዲያቀርቡ እና ወላጆችም ሁኔታውን አይተው ተግባብተው ሰላማዊና ስኬታማ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ባለስልጣን መ/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በዓይነትም በገንዘብም ግብዓቶችን ለማሟላትና ለተለያዩ ጉዳዮች ተጨማሪ እንደሚጠይቁ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ምንም አይነት ተጨማሪ ጥያቄ ማቅረብ እንደማይቻል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚያወጣው ጊዜ #ከሐምሌ ወር በኋላ መሆኑን ማመልከቱን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia