TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።…
#Update

የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።

ሕጉ ምን ይዟል ?

- ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል።

- በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ #የረጅም_ጊዜ_እስር ይጠብቀዋል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል።

- በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው።

ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ ለፓርላማ የቀረበው ይህ ሕግ በከፍተኛ ድምጽ ነው ትናንት ማክሰኞ የጸደቀው።

ከዚህ በኋላ ሕጉን የመሻር ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሲሆኑ ሕጉ ላይ በፈረሙ ቅጽበት ተፈጻሚነቱ ይረጋገጣል።

ከቀናት በፊት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው " ሲሉ አሳስበው ነበር።

#BBC

@tikvahethiopia