TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

" የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል " - ገዢው ብልፅግና ፓርቲ

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ከጥር 13 እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የሥራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህንን ስብሰባ ተከትሎ ፓርቲው መግለጫ አውጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሙሉ መግለጫውን ከላይ ያያዘ ሲሆን አንኳር ያላቸውን ጉዳዮች ከታች አቅርቧል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በ2017 የበጀት ዓመት #ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል።

የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡን አሳውቋል።

" በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ፤ ዓላማቸው በነፍጥ ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ ደግሞ፣ ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድ " ሲል ፓርቲው ውሳኔ አሳልፏል።

ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኢኮኖሚና የባህል ትሥሥር ያላትን አቋም የሚያሳይ መሆኑ መታየቱና በቀጣይም የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ #ተግባራዊ_ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ፓርቲው ውሳኔ አሳልፏል።

ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ፣ የሽግግር ፍትሕና የቀድሞ ታጣቂዎች የተሐድሶ ፕሮግራሞች በተገቢው መንገድ ተከናውነው ለውጤት እንዲበቁ፣ ፓርቲው መንግሥትን እንደሚመራ ፓርቲ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ገልጿል።

በፕሪቶርያው ስምምነት የተገኙ የሰላም ፍሬዎችን በመንከባከብ፣ የጎደሉ ክፍተቶችን በመሙላት፣ ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር ፓርቲው የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia