TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ፤ ይህም ይቀጥላል " - የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት

የብሔራዉ የደኅንነት ምክር ቤት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባጋጠመ ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዳሉ ገልጿል።

" እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው " ብሏል።

" የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " ሲልም ገልጿል።

" በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል፤ #በራያ እና #አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው " ሲል አመልክቷል።

በዚህ ሂደት " የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል " ብሏል።

ም/ቤቱ እነዚህ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልጽ በስም ጠርቶ ባይገልጽም " ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ " ብሏል።

" አንዳንዴም #በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። " ሲል ገልጿል።

" መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል " ሲል አሳውቋል።

https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/87168?single

@tikvahethiopia