TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ🔝

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ “በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ተግዳሮቶች እድሎችና መሰናክሎች” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ በንግግራቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ #መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡

ጥያቄው “ይህንን ለውጥ እንደ ወርቃማ እድል ተጠቅመን እንጓዛለን ወይስ በለውጡ የተመዘገቡ ውጤቶችን እንቀለብሳለን?” የሚለው ነው ብለዋል ጠ/ሚ ዐቢይ፡፡

በመቀጠልም አሁን የምንገኝበት ዘመን የተለያዩ የፖለቲካ ሀሳቦችን የምናንሸራሽርበት ሲሆን አዲሱ የፓለቲካ ባህላችንም ሰጥቶ መቀበልን
እንድንለምድ ግድ ይለናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- ጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳፋሪኮም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው። በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች…
#DireDawa #SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል።

ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦
- በአማርኛ
- በአፋን ኦሮሞ
- በሱማሊኛ
- በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን " 700 "  ላይ በመደወል ማናገር ይችላሉ።

* ማስታወሻ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት ናቸው። የሽያጭ ማዕከሎቹ የሚገኙት ፦
- #ከዚራ
- #መስቀለኛ
- #ኮርኔል ነው።

#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa

@tikvahethiopia