TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አደረኩት ባለው ድንገተኛ የሆነ ኢንስፔክሽን ተከትሎ በርካታ ኮሌጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ " ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥሰት " ፈፅመዋል ያላቸውን 18 ኮሌጆች ማገዱን ገልጿል።

ሌሎች 18 የመጨረሻ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 8 ኮሌጆችን የፅሁፍ  ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት በ10 ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍ እና በአካል ሪፖርት ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

(የተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ " የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ " በማለት ከ4 ግለሰቦች ላይ ከ970 ሺ ብር ያታለለን ተጠርጣሪ መያዙን አሳወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡

በስሙ ግን " ታደለ አቤቤ " እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አዘጋጅቷል።

ይኸው ግለሰብ የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የከንቲባዋ ወንድም እንደሆነ እና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃል።

የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺ ብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብራበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉ ግለሰብን በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገውና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

በተመሳሳይ አዳማ ላይ የተዋወቀቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይ የተባሉ ግለሰብን ደግሞ " የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ " ብሎ 10 ሺ ብር ወስዷል።

እንዲሁም ለቤተሰባቸው ' #ፓስፖርት ' ለማውጣት ኢሚግሬሽን ላይ ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡ የተባሉ ግለሰብን " የከንቲባዋ ወንድም ነኝ በተጨማሪም እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ " የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺህ ብር አታሎ ወስዷል።

ፖሊስ ግለሰቡ ከከንቲባ አዳነች ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" 50,000 ብር ተቀጥተዋል " - የአ/አ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ በከተማው በተሰራው የኮሪደር ልማት ለተሽከርካሪ ባልተፈቀደ የእግረኛ መንገድ ላይ " ሆን ብለው በቸልተኝነት " የደንብ መተላለፍ ፈጽመዋል ያለውን ግለሰብ በ50,000 ብር መቀጮ መቅጣቱን አሳውቋል።

ቅጣቱ የተላለፈባቸው በሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 C 03643 አ.አ የተመዘገበ የቤት መኪና ሲያሽከረክሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው።

" ግለሰቡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቀደም ሲል የቀይ ሽብር ሠማዕታት ወይም ሠላም ፓርክ በተሠራ የልማት ኮርደር ላይ ለተሽከርካሪ ባልተፈቀደ የእግረኞች መንገድ  ሆን ብለው በቸልተኝነት በማጥፋት አምልጠው ተሰውረው ነበር " ብሏል ባለልስጣኑ።

ለግዜው ቢሠወሩም ግን በአዲስ አበባ  ትራፊክ ፖሊስ አባላት ክትትል ከነ ተሽከርካሪያቸው በዛሬው ዕለት መያዛቸውን ፤ ባጠፉት ጥፋት መሰረት 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ ብር መቀጣታቸውን አሳውቋል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" ተስፋ ቆርጠናል " - ቆጣቢዎች

በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች " ተስፋ ቆርጠናል " ሲሉ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።

ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች " ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል " ብለዋል።

" የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን " የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ " በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋን።

ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ " ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?

ኮርፖሬሽኑ " አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው " ብሏል።

" ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ " ሲልም ጠይቋል።

ለኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች የት ቦታ ምን እየተሰራ እንደሆነ መግለጽ ከተቻለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እየተሰራ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች ምን ስራዎችን እየከወነ ይገኛል ? በሚል ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ጽ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ሁለት አስርት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀረው ተመዝጋቢ ለሌሎች ዓመታት በትዕግስት እንዲጠብቅ ተገልጾለታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሃዱ ነው።

#AddisAbaba #AhaduRadioFM

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

"መታወቂያ አምጡ" በማለት በመሳሪያ በማስፈራራት ዘርፈዋል የተባሉ ሁለት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ረዳት ሳጅን ሬድዋን ሁሴን እና ኮንስታብል ሳሙኤል ድጉማ ይባላሉ።

ሰዎቹ የፖሊስ አባላት / ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሐርቡ ፖሊስ ጣቢያ አባል ናቸው።

"ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል" ወንጀል  ተከሰው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ሌሊት ላይ ለወንጀል መከላከል ሥራ በተሰማሩበት ቦታ ላይ ግለሰብን አግተው #በሽጉጥ_አስፈራርተው ንብረት ወስደዋል ነው የተባለው።

የክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መርማሪ እንዳለው ፥ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ሌሊት በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ ተመድበው ሲሠሩ መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን አንድ የግል ተበዳይ " መታወቂያ አምጡ " በማለት ፖሊስ ጣቢያ እንደወሚወስዷቸው ገልጸው ግለሰቡ በኪሳቸው የያዙትን ሁለት ዘመናዊ ሞባይሎች በሽጉጥ አስፈራርተው በመደብደብ እንደወሰዱባቸው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከግለሰቡ የተወሰዱትን ስልኮች 2ኛ ተጠርጣሪ በመኖሪያ ቤቱ በሚተኛበት ፍራሽ ውስጥ ደብቆ መገኘቱን ጠቅሷል።

በዚህም መርማሪ " ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል " ወንጀል ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ገልጸው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ምርመራው ሳይጠናቀቅ በዋስ ቢወጡ የግል ተበዳዩን ሊያስፈራሩ ይችላሉ በማለት የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት የ7 ቀን የምርመራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ፈቅዷል።

#AddisAbaba #FBC #JournalistTarikAdugna

@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነዋሪዎች እጅግ እያማረረ ነው።

በርካቶች የኃይል የመቆራረጡ ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ፈተና ሆኖባቸዋል።

" የሚሰሩት የመንገድ ስራዎች እየተጠናቀቂ ሲመጡ የኃይል የመቋራረጥ ነገሩ ይቃለለል ብለን ብናስብም አሁንም ያው ነው " ብለዋል ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች።

በተለያዩ ቦታዎች ላይም የኃይል መቆራረጡ ንብረት እስከማቃጠል የደረሰ ጭምር ነው።

ከኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ባለፈ ውሃም ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

በተለይ ብዙ ነዋሪዎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውሃ አለመኖር የሚፈጥረው ችግር ይታወቃል።

" በየጊዜው ያለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተደጋግሞ ቢነሳም ዛሬም ድረስ ይኸው ጥያቄ ቀጥሏል ፤ ዘላቂ መፍትሄ መቼ እንደሚመጣ ግራ ነው የገባን !! " ብለዋል።

#AddisAbaba #TikvahFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

" ዘንባባውን ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ 347 ሺህ 262 ብር ቀጥተነዋል " - መንግሥት

በአዲስ አበባ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 ቦሌ መንገድ በተለምዶ ' ቦሌ ማተሚያ ' እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሀምሌ 29/2016 ዓ.ም አንድ ተሽከርካሪ ዘንባባ ገጭቷል።

አደጋው እንዴት ? እና በምን ሁኔታ ? እንደተፈጠረ ምንም የምርመራ ውጤት ይፋ አልሆነም።

ነገር ግን " በተሰራው የኮሪደር ልማት ላይ ዘንባባ ገጭቶ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አድርሷል " የተባለው አሽከርካሪ በዛሬው እለት በህግ ጥሰት መቀጣቱን ወረዳው አሳውቋል።

በዚህም፣ አሽከርካሪው በ347 ሺህ 262 ብር እንደተቀጣና ቅጣቱንም በባንክ እንዳስገባ ነው የተገለጸው።

(ገንዘቡ የገባበት እና ለማን እንደገባ የሚያሳይ ደረሰኝ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።

ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#AddisAbaba #TMA

#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia
#AddisAbaba

ከእዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የ '' ቤቲንግ '' ወይም የስፖርት ውርርድ ቤት አይኖርም ሲል የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ማሳወቁን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፤ " በተጠናቀቀው 2016 የበጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ 4,118 የቤቲንግ (የስፖርት ውርርድ) ቤቶችን ዘግተናል፤ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የውርርድ ወይም ቁማር ቤት አይኖርም " ብለዋል፡፡

" የቤቲንግ ቁማር ስራን በዚህ ከተማ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም " አስረድተዋል፡፡

" ልጆቻችን አዕምሯቸው በቁማር ምክንያት እየተበላሸ ነው ፤ እቃም ጭምር ከቤት እየተሰረቀ እየተሸጠ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለትዳር ፊቺ ጭምር መነሻ ሆኗል እየተባለ ቅሬታ ሲነሳ ነበር፤ ምላሽ ተሰጥቶታል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ማሸጉ ግብ አይደለም፤ በዘርፉ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ሌላ ስራ ቀይረው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተላልፏል " ብለዋል።

አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፥ " ቤት አከራይተው የነበሩ አከራዬችም ለሌላ ንግድ ወይም አገልግሎት በማከራየት አንዲጠቀሙ ተደርጓል " ሲሉ መናገራቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሚሰጠውን አስተያየት ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ካርድዎን POS ላይ በማስጠጋት ጊዜ ሳይፈጁ ይክፈሉ።
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://publielectoral.lat/BoAEth

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን