TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቱ ዩኒቨርስቲ👆

"የመቱ ዩንቨርስቲ መምህራን በዩኒቨርሲቲው የተንሰራፋውን #የመልካም_አስተዳደር እጦት ይታወቅልን በማለት #ሰልፍ ወጥተዋል።"

√Save Mettu University
√ያለ ፕሬዘዳንት እስከ መቼ?
√የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ያነጋግሩን
√ፋይናስ አስተዳደር ለስራችን እንቅፋት መሆን አይገባም
√ለመምህራን ማህበር የሚገባው እውቅና ይሰጠው
√የትምህርት ቁሣቁሦች ይሟሉልን
√ወጥ የሆን የክፍያ አሰራር ይኑር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የመምህራን_ቅሬታ #ምላሽ

ለ487 ' የአዲአርቃይ ወረዳ ' መምህራን የ22 ወራት የደረጃ ዕድገት ደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ማሳደሩን የሰሜን ጎንደር ዞን መምህራን ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፤ " በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን "  የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።

የሰሜን ጎንደር ዞን የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሀብታሙ አቸነፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- የመምህራንን #የመልካም_አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ የሆነ የፖለቲካ የመንግሥት አመራር ባለመፈጠሩ ምክንያት 487 የአዲአርቃይ ወረዳ መምህራን ከጥር 1/2014 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ በጊዜ ቆይታ የደረጃ እድገት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ይህ በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የቅሬታ ምንጭ ሆኖብናል።

- ለመምህራን ከጥር 01/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የደረጃ እድገታቸው እንደሚያድግና ለእድገታቸው የሚሆን በጀት ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሥማቸው ተይዞ ነበር። ይህንን በጀት ' አዘዋውረን ለሰላም ማስከበር አውለነዋል' ነው የሚለው የአስተዳደር ምክር ቤቱ።

- ጥያቄያችንን #በተደጋጋሚ አቅርበን ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት አካል አላገኘንም።

- ባለፈው ዓመት በወረዳው ላይ በነበረ አንድ ጉባኤ ' የመምህራን ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፣ በአዲሱ በጀት ዓመት ጥያቄውን እመልሳለሁ ' የሚል ምላሽን ሰጠ #አስተዳዳሪው። በዚህ ዓመት ደግሞ ፦
* ሀምሌ፣
* መስከረም፣
* ጥቅምት ወራት ላይ ተጠየቀ አሁን የመጨረሻው ውሳኔ ' እኔ በጀቱን አላውቅም ፣ በወቅቱ የነበረውን አስተዳዳሪ በጠየቃችሁ ፣ እኔ አሁን የምከፍልበት ኮንዲሽን የለም ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው ፤ በዚህ መምህራን በጣም #ተበሳጭተው ነው ያሉት።

- መምህራን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለመጠየቅ ሲሄዱ 'እናስራችኋለን፣ እንመታችኋለን' የሚል ተፅእኖ አለ።

- በወቅቱ የነበረው ችግር የሁላችንም ችግር ቢሆንም ደመወዝ ቀጥታ ተከፋይን አንስቶ ' ለሰላም ማስከበር ' በሚል ላለአስፈላጊ ጥቅም ማዋል ተገቢ አይደለም። ላለአስፈላጊ ጥቅም ነው የዋለበት ያልኩት ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኮማንድ ፖስት የትዕዛዝ አቅጣጫ ተሰጥቶ የነበረው ሁሉም ደመወዝ ለሰላም ማስከበር ይሆናል የሚል ሳይሆን፣ 'የሥራ ማስኬጃ 40%ን ተጠቀሙ' የሚል ስለነበር ነው።

- እንደ 'ሰሜን ጎንደር ዞን' ብዙ ወረዳዎች ተሳትፈዋል በጦርነቱ። ጠለምት ተሳትፏል፣ ዳባት ተሳትፏል ነገር ግን አንድም ከበጀት ጋር የተያያዘ ደመወዝ የተነሳበት ወረዳ የለም። በዞናችን አሥር ወረዳዎች አሉ ሙሉ በሙሉ የደረጃ ዕድገታቸውን እየከፈሉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። #አዲአርቃይ ግን እንዲህ አይነት ችግር ገጥሞናል።

- ያልተከፈለውን የደረጃ እድገት ምን ያህል እንደሆነ አላሰላሁትም፣ ግን ቢያንስ ለ487 መምህራን ዝቅተኛ 800፣ ከፍተኛ እስከ 2,000 ብር የደረጃ እድገት ያገኛሉ። ነገር ግን ይኸው እንግዲህ አሁን ጥር ወር ሲገባ 2 ዓመታት ሊሆነው ነው ሳይከፈል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ " የመምህራኑን #የደረጃ_እድገት ደመወዝ ለምን እስካሁን ድረስ አልተከፈለም ? " ሲል የአዲአርቃይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ ጆርጌ ጠይቋል።

አቶ አረቡ ጆርጌ " አሁን ያለበት ሁኔታ በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " መምህራኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እንዳልተከፈላቸው፣ በመጨረሻም በጀቱ ለሌላ ጥቅም እንደዋለ " እንደገለፁለት ለኃላፊው #በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪ ፦

* ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለምን ገንዘቡን አልከፈላችሁም ?

* አሁን ለመክፈልስ ምን የታሰበ ነገር አለ ? ብለን ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው " ኦሬዲ ጠይቀዋል በጀት ተይዞ እንደሚከፈል ብቻ ነው የነገርናቸው እንጂ ለዚህ የተመደበ #ለሌላ ጥቅም የዋለ ገንዘብ የለም " ብለዋል።

" መከፈሉ ግዴታ ነው፣ እንደ ተቋም እንደ አስተዳደር ምክር ቤትም ' አይከፈልም ' የሚል ማስተባበያ አይኖረንም ምክንያቱም ደመወዝ ስለሆነ " ያሉት ኃላፊው፣ " ለሁለት ዓመታት ያክል የገቢ መሰብሰብ ችግር ስለነበር በጦርነቱ ምክንያት በጀቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነው ያሳደረው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስለዚህ እኛም አሁን የያዝነው ፕሮግራም ሙሉውን እንኳ ባይከፈል እየተከፈለ (የአመቱን ወደ 6 ወራት፣ የ6 ወራቱን ወደ ሦስት ወራት እየተደረገ በጀት እየያዝን እንከፍላለን እንጂ አይከፈልም የሚል አቋም የለም። ተገቢነትም የለውም " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia