TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #UAE በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት…
" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸውና በዕለቱ ለተማሪዎቹ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ የትምህርት ዕድል መገኘቱን መግለፃቸው ይታወሳል።

ከዚህ የትምህርት እድል ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት እድሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት የተገኘ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎቹ ከመስከረም/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲማሩ መመቻቸቱን ገልጿል።

ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት #የእንግሊዝኛ_ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንዲቆዩ የሚሰራ መሆኑን ገልጿል።

የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎቹም እንዲሁም እንደ አጠቃላይ ለሀገር በጣም ጥሩ እድል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች #እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም ሲል አሳውቋል።

ተማሪዎቹ መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ ?

- የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።

- አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን  የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በዓለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።

- ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ፦ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።

- ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በ1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።

- ዛይድ ዩኒቨርስቲ ፦ በ1998 የተመሰረተና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስመ ጥር የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው።

https://www.topuniversities.com

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አሁን

የኢፌዴሪ ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር የቀድሞ ተዋጊዎችን የመልሶ ማቋቋም ሂደት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በመቐለ እያካሄደ ይገኛል።

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
" አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን " - ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ

ጎረቤት ሀገር ኬንያ በትምህር ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችውን " የተመሳሳይ ጾታ " አጀንዳ ላይ ዘመቻ መጀመሯ ታውቋል።

የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ ፥ " በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል " ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተናግረዋል።

ሚንስትሩ በት/ ቤቶች ውስጥ " የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን " ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።

በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው #መማሪያ እና #አጋዥ_መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህር ሚንስትሩ ገልጸዋል።

ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ " የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል " በማለት በመላው ኬንያ #ጸሎት_እንዲደረግ ካወጁ በኋላ ነው።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል " ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ ፤ " አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ " ብለዋል።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ኬንያ ውስጥ #ሕጋዊ_አይደለም

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው መታየታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል (ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ)

@tikvahethiopia
#TeklehaimanotGeneralHospital

ማርች 8 የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 6 የእርግዝና ክትትል ለሚጀምሩና ለሚወልዱ ነፍሰጡር እናቶች ልዩ ልዩ ስጦታዎችና እስከ ወሊድ ጊዜያቸዉ የሚቆይ የ 25% ቅናሽ በሁሉም አገልግሎታችን ላይ ማድረጋችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ።

ተክለሀይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል

Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral
Telegram: https://publielectoral.lat/teklehaimanothospital
LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../teklehaimanot-general-hospital/
Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: Info@teklehaimanothospital.com
ይኽን አስተውለው ያውቃሉ?

- በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን ይገኛሉ።

- ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የምልክት ቋንቋ ባለቤት ናት፤ ይህ ማለት ይህንን ቋንቋ ሚሊዮኖች ይናገሩታል ማለት ነው።

- ቋንቋ መግባቢያ ሲሆን የምልክት ቋንቋም እንደማንኛውም ቋንቋ ከሰዎች ጋር የምንነጋገርበት፤ የምንግባባበት ነው።

እጆች ይናገራሉ .... አይኖች ያዳምጣሉ ስንል፦

- በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያለው ይኽ ቋንቋ በፖሊሲም ሆነ በአፈጻጸም ትኩረት እንዲሰጠው፤

- መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከሌሎች ዜጎች እኩል የመስራትና የመማር እድል እንዲፈጠርላቸው፥ እንዲሁም በወረቀት የተከበረላቸው ህጎች በተግባር እንዲተገበሩ፤

- መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች በተለይም ለሴቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጥ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ነው።

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia      @RWethiopia
#Afar

15ኛው የአፋር ሱልጣን በዓለሲመት ሰኞ ይከናወናል።

የፊታችን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሱልጣን አህመድ አሊሚራሕ  15ተኛው የአፋር ሱልጣን በመሆን  በዓለሲመታቸው እንደሚከናወን የአፋር ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል።

ለዚሁ በዓለሲመት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ አዲስ አበባ  ገብተዋል። አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ  አመራሮች ተገኝተው  አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tikvahethiopia
#ProfessorSenaitFesha #DrLiyaTadesse

ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሐ ተሸለሙ።

የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በቡፌት ፋውንዴሽን የዓለም ዓቀፍ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰናየት ፍስሐ የዓመቱ ምርጥ የስራ መሪ ተብለው በመመረጥ ተሸለሙ።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሐ በሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ በተካሄደ እና የአፍሪካ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ሲመክር በሰነበተ  ጉባዔ (Africa Health Agenda international Conference- AHAIC 2023) ላይ ነው የዓመቱ ምርጥ የስራ መሪ ተብለው የተመረጡት።

በዚህም መሰረት የዓለም ዓቀፍ የጤና (Global Health Award) ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

በጉባዔው ላይ እንደተገለጸው ሁለቱም ተሸላሚዎች ለሽልማቱ የበቁት  በጤና አገልግሎት ዙሪያ ከፍተኛ የአመራር ብቃት በማሳየታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

#AHAIC2023

ምንጭ፦ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ማህበር ለኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ ለጤና ሚኒስቴር፣ ለጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ግልፅ ደብዳቤ ፅፏል።

ማህበሩ በፃፈው በዚህ ደብዳቤ፤ አስቸኳይ መፍትሔ የሚፈልጉ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በሚል ዘርዝሯል።

ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው የደሞዝ ማሻሻያ ጥያቄ ነው።

መንግስት ለጤና ባለሙያዎች አሁናዊ የኑሮ ሁኔታዉን ባገናዘበ መልኩ አስቸኳይ የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

የህክምና ሙያ አስደሳችም፣ እጅግ አሳዛኝም ሁኔታዎችን የሚያስተናግድ እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ጫና ያለበት የሙያ ዘርፍ መሆኑን የገለፀው ማህበሩ በ2013 ዓ/ም ተግባራዊ የተደረገዉ የነጥብ ስራ ምዘና /JEG/ ግን የጤና ባለሙያዎችን የስራ ጫና ፣ የሙያዉን ክብር ያላገናዘበ ነው ብሏል።

መመሪያዉ ጤና ባለሙያዎችን ያስቀመጠበት ደረጃ ፍፁም ቅቡልነት የሌለዉና ጤና ባለሙያዎችን ያሳዘነ ለከፍተኛ ቅሬታም የዳረገ ጉዳይ መሆኑም ተገልጿል።

መንግስት የሌሎችን ሃገሮች ተሞክሮ በመዉሰድ የጤና ባለሙያዎችን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ደሞዝ በዓለም ጤና ድርጅት(WHO) standard መሰረት በማድረግ ችግሩን መፍታት ስለሚቻል በዚ መልኩ የጤና ባለሙያወችን ደሞዝ እንዲያሻሽል ማህበሩ ጠይቋል።

ሌላኛው ማህበሩ ያነሳው ጉዳይ የቤት ጥያቄ ሲሆን አሁን ባለዉ ተጨባጭ የሃገሪቱ የኑሮ ሁኔታ የጤና ባለሙያዎች ደሞዝ ቤት ለመከራየት እንኳን የማይበቃበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።

ለምሳሌ አዲስ አበባ ዉስጥ ቤት 5000 ብር እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንድ በመጀመርያ ድግሪ ተመርቆ ወደ ስራ የገባ ጤና ባለሙያ የሚከፈለዉ የተጣራ ደሞዝ ከ4,776 ብር ጀምሮ መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።

እንደየአከባቢው የሚለያይ ቢሆንም ይህ የሚያሳየዉ ጤና ባለሙያው የሚከፈለው ደሞዝ በሚያሳዝን ሁኔታ ሌላ መሰረታዊ ፍለጎት አይደልም ቤት ኪራይ እንኳ ለመክፍል አይበቃውም ያለው ማህበሩ አሁን ያለዉን የቤት ኪራይና የኑሮ ዉድነት ግምት ዉስጥ በማስገባት መንግስት ለጤና ባለሙያዎች አፍጣኝ የቤት አበል ጭማሪ እንዲደረግ፣ የጤና ባለሞያዎችን የዘመናት የቤት ጥያቄ በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጠው በአፅንኦት ጠይቋል።

ሌላው ማህበሩ የነፃ ህክምና ጥያቄ አቅርቧል።

"የጤና ባለሙያው ከሚሰራበት ቦታ ጋር ተያይዞ ለተለያዩ በሽታዎች በተለይም ተላላፊ ለሆኑት የመጋለጥ እድሉ እጅግ ከፍ ያለ ነው" ያለው ማህበሩ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጤና ባለሙያዎች ታመው መታከሚያ አጥተው በህዝብ ፊት ሲለመንላቸው ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል፤ ከጤና ውጪ በተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች የሚሰሩ ሰራተኞች የነፃ ህክምና ተጠቃሚ ሲሆኑ ይበልጥ ተጋላጭ የሆነውና የሙያው ባለቤት የሆነዉ ጤና ባለሞያ ግን የነፃ ህክምና ተጠቃሚ አለማድረጉ ጤና ባለሙያዎችን በራሳቸዉ መ/ቤት ያገለለና ጤና ባለሙያዎችንም ለከፍተኛ ወጪና ማህበራዊ ቀዉስ የዳረገ ተግባር ሆኖ ታይቷል" ሲል ገልጿል።

መንግስት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጤና ባለሙያዎች የነፃ ህክምና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ በአስቸኳይ እንዲመቻች ማህበሩ በእፅንዎት ጠይቋል።

ከዚህ ባለፈ ማህበሩ የተጋላጭነት /Risk/፣ የትምህርት ዕድል፣ የስራ እድል፣ የትርፍ ስዓት ክፍያ፣ በጤና ተቋማት የሚታየዉ የግብዓት አጥረትና አስተዳድራዊ ችግሮችን በማንሳት ጥያቄዎች አቅርቧል።

ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ የማይሰጥ ከሆነ ጤና ባለሞያዎች የትኛውም አይነት ህጋዊ መንገድ ተከትለው ጥያቄ የማሰማት መብት አላቸው በዚህም ለሚፈጠረው ችግር ጤና ሚኒስቴር እና የመንግስት ተቋማት ኃላፊነቱን ይወስዳሉ ብሏል።

@tikvahethiopia