TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጿል። ቦርዱ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ብሏል። @tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች ፦
- በኮንሶ፣
- በደቡብ ኦሞ፣
- በወላይታ፣
- በጋሞ፣
- በጌዴኦ፣
- በጎፋ እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦
• በቡርጂ፣
• በባስኬቶ፣
• በአሌ፣
• በአማሮ፣
• በዲራሼ ላይ ያካሄደውን የሕዝበ ውሣኔ ጊዜያዊ ውጤት የማዳመር ሥራ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ አጠናቆ በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ መደረጉን አስታውሷል።

ቦርዱ የመጨረሻውን ውጤት የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የሕዝበ ውሣኔው ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ቀደም ሲል ቦርዱ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ የመጨረሻውን በቦርድ የተረጋገጠ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ እንደሚያደርግ የገለፀ ቢሆንም በርከት ያሉ ግድፈቶችና የምርጫ ህግ ጥሰቶች በቦርዱ የምርጫ ክትትል ቡድን እንዲሁም በምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት በመቅረቡ የማጣራት እና ውጤት የማረጋገጥ ስራን በታቀደበት ግዜ ለማጠናቀቅ አልተቻለም ብሏል።

በዚህም የውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ ስራ ፦

የዲራሼ፣
አሌ፣
ደቡብ ኦሞ፣
ባስኬቶ፣
ኮንሶ
ቡርጂ ውጤቶችን የማጣራትና የማረጋገጥ ስራ ተጠናቆ ውጤታቸው በቦርዱ #ፀድቋል

በቀጣይም በቀሪዎቹ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦
በአማሮ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ እና የጎፋ ግዜያዊ ውጤቶች የማጣራትና የማረጋገጥ ሂደት እንደተጠናቀቀ ቦርዱ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በቦርዱ የፀደቀውን ውጤት ከላይ ተያይዟል በተጨማሪ በዚህ ማግኘት ይቻላል : https://nebe.org.et/am/Referendum_Result

#NEBE

@tikvahethiopia
" ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ እስረኞች ተፈተዋል "

በሸገር ከተማ (በቀድሞ ፊንፊኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን) በፉሪ ክ/ከተማ 04 ፓሊስ ጣቢያ ታስረው ከነበሩ እስረኞች መካከል ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑት መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሸገር ከተማ በፉሪ ክ/ከተማ 04 ፖሊስ ጣብያ የሚገኙ እስረኞችን፣ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በእስር ቤቱ በመገኘት ከጠየቁና ካጽናኑ በኋላ ከሚመለከታ ቸው የአቃቤ ሕግና የፖሊስ ጣቢያው ኋላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ከውይይቱ በኋላም ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ እስረኞች መፈታታቸውን ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ከአቃቤ ሕግና ከፓሊስ ኃላፊዎች ለተደረገላቸው ግሩም የሆነ መስተንግዶና አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አቅርበዋል።

አሁንም የቀሩትና በፓሊስ ጣቢያው ውስጥ የሚገኙ እስረኞችም በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚፈቱ ከአቃቤ ሕጉና ከፓሊስ ኃላፊዎቹ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው ብፁዕነታቸው ገልጸዋል።

በዛሬው እለትም ተጨማሪ እስር ቤቶችን እንደሚጎበኙና እስረኞችን እንደሚያጽናኑ አሳውቀዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በወልቂጤ ምን ሆነ ? ዛሬ ረቡዕ በወልቂጤ ከተማ ውስጥ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ 7 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል።  በከተማው ነዋሪዎችን ካማረረ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለማቅረብ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ  ወስደዋል። በዚህ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃም 2 ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች እና የጤና…
" 3 ሰዎች ጭንቅላታቸውና ደረታቸው ላይ በጥይት ተመተው መገደላቸውን አረጋግጫለሁ " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የካቲት 8/2015 ዓ.ም በደቡብ ክልል፤ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች የቧንቧ ውሃ አቅርቦት ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ላጋጠማቸው የውሃ ችግር መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለማቅረብ ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በፖሊስ በተወሰደ #የኃይል_እርምጃ በነዋሪዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ የዐይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችንና የጤና ባለሙያዎችን በማነጋገር ባሰባሰበው መረጃ እና ማስረጃ መሠረት 3 ሰዎች ጭንቅላታቸውና ደረታቸው ላይ በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆኑን ቢያንስ በ30 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱን #እንዳረጋገጠ ገልጿል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት ለደረሰው ጉዳት ምክንያት የሆነው ከሰልፈኞች ውስጥ የተወሰኑት ሰዎች የከተማው የውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ላይ ድንጋይ መወርወራቸውንና የመኪና መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ በክልሉ ፖሊስ በተወሰደ የኃይል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የተወሰደው የኃይል እርምጃ ከነገሩ ሁኔታ አንጻር ሲታይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ነው ብለዋል።

"አንገብጋቢ በሆነ የውሃ አቅርቦት ጥያቄ ሰልፍ ወጥተው ድንጋይ በወረወሩና መንገድ በዘጉ ሰዎች ላይ ሕይወት የሚያጠፋ መሣሪያ ተጠቅሞና ጥይት ተተኩሶ ነዋሪዎች መገደላቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እርምጃ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና የተጎዱ ሰዎችም ተገቢውን ካሳ ሊያገኙ ይገባል" ሲሉ አስገንዝበዋል።

(ከኢሰመኮ የተላከ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

የሟቾች ቁጥር ከ45 ሺህ አለፈ።

ባለፈው ሳምንት #ቱርክ እና #ሶሪያን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺህ ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ምንም እንኳን በአደጋው ሳቢያ መጠለያ አልባ የሆኑ ሰዎች ይፋዊ ቁጥር ባይገለፅም በርካቶች መጠለያ አልባ ሆነው በተለያዩ ቦታዎች ውሎ እና አዳራቸውን ለማድረግ ተገደዋል። ከመጠለያ ባለፈ መሰረታዊ ነገሮችን ለማሟላት ተቸግረው እንደሚገኙ ተነግሯል።

ተጎጂዎችን ለማገዝ ዓለም አቀፍ የሆነ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን በስልክ መግለጣቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

" ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጇን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ ናት። " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ " ባላት ዐቅምም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ አበርክታለች " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AU

ኮሞሮስ የ2023 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን #ከሴኔጋል በይፋ ተረክባለች።

36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ መርሐግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሴኔጋል ለኮሞሮስ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች።

የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ከፕሬዜዳንት ማኪ ሳል የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡ ሲሆን 2023ን የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ያገለግላሉ።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀናት በፊት ስምምነት ላይ የደረሱት አባቶች ስምምነቱን እንዲሁም ቀኖናውን ደግመው መጣሳቸውን አሳወቀች። ይህንን በተመለከተ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ፅህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተከታዩን ብለዋል ፦ " ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች…
#Update

ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማሙባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን መስጠታቸው ተገልጿል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia