TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

የሟቾች ቁጥር ከ45 ሺህ አለፈ።

ባለፈው ሳምንት #ቱርክ እና #ሶሪያን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺህ ማለፉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ምንም እንኳን በአደጋው ሳቢያ መጠለያ አልባ የሆኑ ሰዎች ይፋዊ ቁጥር ባይገለፅም በርካቶች መጠለያ አልባ ሆነው በተለያዩ ቦታዎች ውሎ እና አዳራቸውን ለማድረግ ተገደዋል። ከመጠለያ ባለፈ መሰረታዊ ነገሮችን ለማሟላት ተቸግረው እንደሚገኙ ተነግሯል።

ተጎጂዎችን ለማገዝ ዓለም አቀፍ የሆነ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን በስልክ መግለጣቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

" ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጇን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ ናት። " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ " ባላት ዐቅምም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ አበርክታለች " ብለዋል።

@tikvahethiopia