TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ አመሻሽ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ።

በመግለጫው ፤ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በውስጥ አሠራር እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙ ይታወቃል። ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ " ብሏል።

ይሁንና አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላት እየተገለጡ ናቸው ያለው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን " ይህንንም መንግሥት በልዩ ልዩ መንገዶች አረጋግጧል " ብሏል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" ... ' የመሥዋዕትነት ሰልፍ አዘጋጅ ' በሚል ከባለ ሀብቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከመንፈሳውያን የወጣት አደረጃጀቶች የተውጣጣ ቡድን ከማዕከል እስከ ታች መዋቀሩን መንግሥት ደርሶባታል።

አጋጣሚውን #በትጥቅ_በተደገፈ_ሁከት መንግሥትን የመነቅነቅ ፍላጎት ያለው ይህ ቡድን ወጣቶችን እየመለመለ ማሠማራት መጀመሩን፣ ለዓላማው በልዩ ልዩ መንገዶች ገንዘብ በመሰብሰብ እያሠራጨ መሆኑንና በሕገ ወጥ መንገድ ከታጠቁ ኃይሎች ጋርም ግንኙነት እየፈጠረ መሆኑን መንግሥት አረጋግጧል።

ለዚሁ እኩይ ዓላማ አስቀድሞ አስቦበት ያደራጁት የሚዲያ ቡድን ሥራውን መጀመሩም ተረጋግጧል፡፡

በዚህ የክትትል ሂደት ድምጽ ያላቸውና የሌላቸው መሣሪያዎች ይዘው ሁከት የሚፈጥሩ አካላት በሥምሪት ላይ እያሉ ተይዘዋል።

የቤተ ክርስቲያንን ደወል ላልተገባ ዓላማ በመጠቀም ሕዝብን ለብጥብጥ የሚዳርጉ ቡድኖችም ታይተዋል።

በየአካባቢው ወጣቶችን ለግጭት የሚመለምሉና የሚያሠማሩ አካላት ተደርሶባቸዋል። የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም የሚሞክሩ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia