TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል። አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ " ትላንት ምሽት የመንግስት የጋራ ግብረኃይል የሰጠውን የ " ሰልፍ ክልከላ መግለጫ " እንደማይቀበለው አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የትላንቱ የመንግስት መግለጫ " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ " ትላንት ምሽት የመንግስት የጋራ ግብረኃይል የሰጠውን የ " ሰልፍ ክልከላ መግለጫ " እንደማይቀበለው አስገንዝቧል። ቅዱስ ሲኖዶስ የትላንቱ የመንግስት መግለጫ " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል። (ሙሉ መግለጫ…
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል።

" መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ፦

- ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር

- በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣

- ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣

- ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

- በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ ጠይቋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት #በዚሁ_አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት 5/2015 ዓ/ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ " ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊ እና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም ሲል አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስቱ የተደነገገ መሰረታዊ መብት መሆኑን ገልጾ ቤተክርስቲያን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን ብሏል። 

ሙሉ መግለጫ : https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/76397?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያመጡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ያበቃል።                         በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡና በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየት/ ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እንዲያስተካክሉ በትምህርት…
#ተራዝሟል

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓም. መራዘሙን አሳውቋል።

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ገልጾ ይህም የሚሆነው ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ ተማሪዎች የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ግንዛቤ አንዲወሰድ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል። " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል "…
" ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ መላው ምዕመን ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቹን ድምጽ ብቻ እንዲሰማ አሳስቧል።

" ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ " እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፋለን " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሊደረግ የታሰበውን ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈ ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

" ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን " ያለው  ቅዱስ ሲኖዶስ " እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን " ብሏል።

@tikvahethiopia
#Update

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ አመሻሽ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ።

በመግለጫው ፤ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በውስጥ አሠራር እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙ ይታወቃል። ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ " ብሏል።

ይሁንና አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላት እየተገለጡ ናቸው ያለው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን " ይህንንም መንግሥት በልዩ ልዩ መንገዶች አረጋግጧል " ብሏል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" ... ' የመሥዋዕትነት ሰልፍ አዘጋጅ ' በሚል ከባለ ሀብቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከመንፈሳውያን የወጣት አደረጃጀቶች የተውጣጣ ቡድን ከማዕከል እስከ ታች መዋቀሩን መንግሥት ደርሶባታል።

አጋጣሚውን #በትጥቅ_በተደገፈ_ሁከት መንግሥትን የመነቅነቅ ፍላጎት ያለው ይህ ቡድን ወጣቶችን እየመለመለ ማሠማራት መጀመሩን፣ ለዓላማው በልዩ ልዩ መንገዶች ገንዘብ በመሰብሰብ እያሠራጨ መሆኑንና በሕገ ወጥ መንገድ ከታጠቁ ኃይሎች ጋርም ግንኙነት እየፈጠረ መሆኑን መንግሥት አረጋግጧል።

ለዚሁ እኩይ ዓላማ አስቀድሞ አስቦበት ያደራጁት የሚዲያ ቡድን ሥራውን መጀመሩም ተረጋግጧል፡፡

በዚህ የክትትል ሂደት ድምጽ ያላቸውና የሌላቸው መሣሪያዎች ይዘው ሁከት የሚፈጥሩ አካላት በሥምሪት ላይ እያሉ ተይዘዋል።

የቤተ ክርስቲያንን ደወል ላልተገባ ዓላማ በመጠቀም ሕዝብን ለብጥብጥ የሚዳርጉ ቡድኖችም ታይተዋል።

በየአካባቢው ወጣቶችን ለግጭት የሚመለምሉና የሚያሠማሩ አካላት ተደርሶባቸዋል። የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም የሚሞክሩ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ አመሻሽ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ። በመግለጫው ፤ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በውስጥ አሠራር እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙ ይታወቃል። ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ " ብሏል። ይሁንና አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ…
#Update

ዛሬ አመሻሽ የአዲስ አበባ አስተዳደር ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" ... በዛሬው እለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ  አየር ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አዳዲስ የተሾሙ ጳጳሳት እየመጡ ነው ቤተክርስቲያናችንን ሊነጥቁን ነው በሚል፤  ስልክ ተደውሎ ተነግሮናል በሚል ሀሰተኛ መረጃ ውዥንብር በመፍጠርና ሰዎች ወደ ግጭትና ትርምስ ውስጥ እንዲገቡ ሙከራ  ተደርጓል፡፡

ይህም ተግባር በተቀናጀና በተናበበ የሚድያ ዘመቻ ከቤተክርስቲያን ደውል መደወል ጀምሮ በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ጉዳዩን ለማቀጣጠልና ይህንንም በመላው ከተማይቱ በሌሎችም ደብሮች በተመሳሳይ መንገድ  ለመፈፀም  እና ህብረተሰቡን ውዥንብር እና ግጭት ውስጥ ለመክተት ዝግጅት መኖሩን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ከዚያም አልፎ ግጭት ወደ ትምህርት ቤቶችም ለማስፋፋት የተለያዩ ሙከራዎች መኖራቸውም ምልክቶች ታይተዋል፡፡

ስለሆነም አሁናዊ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመው አዳዲስ ጳጳሶች ሹመት  በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትና ደብሮች ውስጥ ያለመሆኑ እየታወቀ ፤ ሆነ ተብሎ ግጭት ለመፍጠር እና የግጭት አውድማውን አዲስ አበባን ለማድረግ የሚደረጉ ጥሪዎች የተሳሳቱ ፤ አግባብነት የሌላቸው ናቸው፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ  እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል።

አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል።

ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ ሆነ ማቆም የሌለ ሲሆን አገልግሎት እንዲገደበ የተደረገው በዚሁ በሀገር ውስጥ መንግስት በወሰደው እርምጃ  እንደሆነ አያጠራጥርም።

እስካሁን ስለጉዳዩ በቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎቹም ሆነ በየትኛውም የመንግስት አካል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል ፤ ኔትብሎክስ የተባለው የኢንተርኔት ጉዳዮች ተከታታይ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር ፣ ቲክቶክ፣ እና ቴሌግራም የመሳሰሉ የማህበራዊ መገናኛዎች መገደባቸውን አመልክቷል። ድርጅቱ ገደቡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ ሊደረግ ከታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር የተገናኘ እንደሆነ አመልክቷል።

ምንም እንኳን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ገደብ ቢደረግባቸውም በVPN / Psiphon አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ !

ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል።

እስካሁን ድረስ መግለጫቸውን ለህዝብ ያሰራጩት ፦

- የሶማሌ ክልል
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል
- የደቡብ ክልል
- የሐረሪ ክልል
- የጋምቤላ ክልል መንግስታት ሲሆኑ በመግለጫቸው " በተገቢው አካል ያልተፈቀደ እና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ሰላማዊ ሰልፍ " የተከለከለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫ ፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና መሰረት ባደረገ ውስጠ ደንብ / ውስጣዊ አሰራር ሊፈታ ይገባል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከሃይማኖት ጉዳይነት አልፎ እየተወሳሰበና በርካታ እኩይ ዓላማ ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የፓለቲካ ኃይሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ለማዳከም ርብርብ እያደረጉ ናቸው " ያሉት የየክልሉ መንግስታት " ይህንንም በመረጃና በማስረጃ አረጋግጠናል ብለዋል።

በዚህም " ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሀገርና የህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም እንቅሳቃሴ እንቃወማለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገቢው አካል ያልተፈቀደና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግም ተገቢነት ያለው ጉዳይ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫቸው ፤ ህገ መንግስቱንና የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ውሳኔን መሰረት በማድረግ ማንኛውንም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በመከላከልና በመቆጣጠር ህግ የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ አስገንዝበዋል።

(መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሰበር_መረጃ

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች 72 ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት ፤ ቀኖናና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ይፋዊ ጥሪ ማስተላለፏን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ለሕዝቡ የሚያመጣው መፍትሔ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አሳውቋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia