TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ አመሻሽ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ። በመግለጫው ፤ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በውስጥ አሠራር እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙ ይታወቃል። ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ " ብሏል። ይሁንና አሁን የተፈጠረውን አጋጣሚ ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ…
#Update

ዛሬ አመሻሽ የአዲስ አበባ አስተዳደር ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" ... በዛሬው እለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ  አየር ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አዳዲስ የተሾሙ ጳጳሳት እየመጡ ነው ቤተክርስቲያናችንን ሊነጥቁን ነው በሚል፤  ስልክ ተደውሎ ተነግሮናል በሚል ሀሰተኛ መረጃ ውዥንብር በመፍጠርና ሰዎች ወደ ግጭትና ትርምስ ውስጥ እንዲገቡ ሙከራ  ተደርጓል፡፡

ይህም ተግባር በተቀናጀና በተናበበ የሚድያ ዘመቻ ከቤተክርስቲያን ደውል መደወል ጀምሮ በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ጉዳዩን ለማቀጣጠልና ይህንንም በመላው ከተማይቱ በሌሎችም ደብሮች በተመሳሳይ መንገድ  ለመፈፀም  እና ህብረተሰቡን ውዥንብር እና ግጭት ውስጥ ለመክተት ዝግጅት መኖሩን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ከዚያም አልፎ ግጭት ወደ ትምህርት ቤቶችም ለማስፋፋት የተለያዩ ሙከራዎች መኖራቸውም ምልክቶች ታይተዋል፡፡

ስለሆነም አሁናዊ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመው አዳዲስ ጳጳሶች ሹመት  በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትና ደብሮች ውስጥ ያለመሆኑ እየታወቀ ፤ ሆነ ተብሎ ግጭት ለመፍጠር እና የግጭት አውድማውን አዲስ አበባን ለማድረግ የሚደረጉ ጥሪዎች የተሳሳቱ ፤ አግባብነት የሌላቸው ናቸው፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia