TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" መግለጫውን አልቀበለውም " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ያወጣውን ወቅታዊ መግለጫ በተመለከተ መግለጫውን እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

" በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ " በሚል ከመንግስት የተሰራጨው መግለጫ ያስቀመጣቸው ነጥቦች የቤተክርስቲያኗን ክብር፤ ታሪክ፤ እና እውነታ ቸል በማለት በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ የሌላቸው ወገኖች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል መግለጫ በመሆኑ እንደማትቀበለው ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ቤተክርስቲያኗ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው መግለጫ ፤ ብቸኛ ሕጋዊ ሰውነት ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በቀኖናው መሠረት አውግዞ የለያቸውን ግለሰቦች አሁንም ሕጋዊ አካላት እንደኾኑ እና እውቅናም እንደሚሰጣቸው የሚያስረዳ መግለጫ ሆኖ እንዳገኘችው አስረድታለች።

ይህም ተገቢነት የሌለው ነው ብላ እንደምታምን በመግለፅ በመንግሥት ኮምዩኒኬሽን የተሰጠውን መግለጫ " አልቀበለውም " ስትል ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

(የቤተክርስቲያኗ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

የመንግሥት መግለጫ በዚህ ይገኛል : https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/76283?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መግለጫውን አልቀበለውም " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ያወጣውን ወቅታዊ መግለጫ በተመለከተ መግለጫውን እንደማትቀበለው አሳውቃለች። " በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ " በሚል ከመንግስት የተሰራጨው መግለጫ ያስቀመጣቸው ነጥቦች የቤተክርስቲያኗን ክብር፤ ታሪክ፤…
#Update

ቤተክርስቲያኗ መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት እንዲሁም ህገወጥ ናቸው ስትል የፈረጀቻቸው አካላት እየፈፀሙት ነው ላለችው ህገወጥ ድርጊት እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትላንትናው ዕለት መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

ቤተክርስቲያኗ ትላንት መንግስት መግለጫውን ሲያወጣ ፤ " በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑን አንስታ ይህም " የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል " ብላለች።

" መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እናሳስባለን " ያለችው ቤተክርስቲያኗ ፤ " ሕገ ወጡ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ ያቁም " ስትል አሳስባለች።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በሮም፤ ጣሊያን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ሴርጂዮ ማታሬላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።

Photo ፦ PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዛሬም እስር እና ማንገላታት ቀጥሎ መዋሉን ገለፁ።

ተሚማ የተሰኘው ሚዲያ ፤ በዛሬው ዕለት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ መታሰራቸውን ገልጿል።

ሚዲያው ፤ " ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል " ሲል ነው ያስረዳው።

በሌላ በኩል በሀገረ ስብከቱ ያሉ 13 ወጣቶችም በዛሬው ዕለት መታሠራቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል በቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ዛሬ የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥቁር ለብሰው የዋሉ ሲሆን ጥቁር ልብስ የለበሱ ምእመናን በኮልፌ ፊሊዶሮ ልደታ፣ በቀራንዮ መድኃኔዓለምና በወይብላ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ፖሊስ ድብደባ መፈፀሙን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሌላ በኩል በአንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጥቁር እንዳይለብሱ ፤ የቤተክርስቲያኗን ትዕዛዝ እንዳይፈፅሙ የማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ ምዕመናን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ጸሎትና ምሕላ እንዲያቀርቡ በቤተክርስቲያኗ የቀረበው ጥሪ በቀጣይ ቀናትም ተግባራዊ ሆኖ ይቀጥላል።

ፎቶ፦ የጾመ ነነዌ የፀሎት ስነስርዓት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዛሬም እስር እና ማንገላታት ቀጥሎ መዋሉን ገለፁ። ተሚማ የተሰኘው ሚዲያ ፤ በዛሬው ዕለት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ መታሰራቸውን ገልጿል። ሚዲያው ፤ " ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል…
#Update

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው አሳውቋል።

የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸው ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖናና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ጉባኤው ገልጿል።

የጉባኤው ባለ 5 ነጥብ መግለጫ ፦

- ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማኞች በተጨማሪ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪ በመመለስ ጸሎት ወይም ዱዓ እንዲያደርግ ብሏል።

- የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ከማክበር ጎን ለጎን የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ተገንዝበው ውይይትን፣ ይቅርታንና እርምትን እንዲያስቀድሙ በፈጣሪ ስም በማሳሰብ ይህም ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አስቀድሞ እንድትከላከሉ ብሏል።

- የፌዴራልና የክልሎች መንግሥታት በቤተክርስቲያኒቱ  ውስጥ የተፈጠረው ችግር በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ቀኖና እና ሥርዓት ብቻ ተመሥርቶ እንዲፈታ ኃላፊነታቻውን በአግባቡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 መሠረት እንዲወጡ አሳስቧል።

- ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አመራሮችና አባላት፤ የማኅበረሰብ አንቂዎች ወቅታዊ የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግር ከማባባስ እንዲታቀቡ አሳስቧል።

- የመገናኛ ብዙኋን ባለሙያዎች፣ ዘጋቢዎችና ተንታኞች የሚያስተላልፏቸው መልእክቶችና ንግግሮች ችግርን የሚያባብሱና ሌላ ግጭትና ሁከት የሚቀሰቅሱ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ቪድዮ ፦ ቱርክ እና ሶሪያ በሚወሰኑበት የድንበር አካባቢ ባጋጠመው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት አሳወቁ።

ዛሬ ሰኞ ጠዋት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ አስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ እንዲሁም በሶሪያ በኩል ደግሞ ወደ 800 የሚደርሱ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።

ቱርክ ከሶሪያ ጋር በምትዋሰንባት በደቡብ ምሥራቋ ጋዚያንቴፕ ግዛት ውስጥ ባጋጠመው በዚህ አደጋ በአጠቃላይ በሁለቱ አገራት ወደ ሁለት ሺህ እየተጠጉ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

የነፍስ አድን ሠራተኞች በፍርስራሾች ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ፈልጎ የማውጣት ሥራ እያከናወኑ ሲሆን፣ በዚህም የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቪድዮ ፦ Ahmit Sahu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ መንግሥት በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገለፀ።

መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ፤ በደቡባዊ ተርኪዬ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም  ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

መንግስት ጉዳት የደረሰባቸው በቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ገልጾ ፤ " በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርኪዬ መንግሥት እና ህዝብ ጎን የምትቆም መሆኗን እንገልፃለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፖሊስ ዛሬ ስለነበረው ሁኔታ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጠዋት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰላማዊ እንቅስቃሴን የማወክ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተስተውለዋል ብሏል።

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ክልል ውስጥ በምትገኘው ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን  የተሰበሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ገብተው " የታሰሩብን ሰዎች ይፈቱልን " በሚል ምክንያት በድንጋይ መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር እንዲከሰት ለማድረግ ሞክረዋል ሲል ገልጿል።

ፖሊስ ፤ " ምንም አይነት የታሰረም ሆነ የተያዘ ሰው እንደሌለ በመግለፅ የተዘጋው መንገድ እንዲከፈት ቢያሳስባቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም " ሲል አስረድቷል።

ከፖሊስ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ወጣቶች የታሰረ ሰው አለመኖሩን በማስረዳት መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ አካሉን እያገዙ በምክር እና በተግሳፅ የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም የተሰበሰቡት ሰዎች ከቦታው ለመንቀሳቀስ እና መንገዱ እንዲከፈት ፍላጎት አልነበራቸውም ብሏል።

ፖሊስ በመግለጫው፤ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወቅቱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ እንዲከፈትና ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል የማድረግ ስራ ሰርቷል ብሏል።

በዚህ ወቅት ግጭቱ እንዲፈጠር በግልፅም ሆነ በስውር ሲቀሰቅሱና በተባባሪነት ሲሳተፉ በነበሩ ሃይሎች በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል አሳውቋል።

(የፖሊስ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

@tikvahethiopia @tikvahuniversity