TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ነው ያለውና ቤተክርስቲያንን ያሳዘነው ፤ ምዕመኑንም ያስደናገጠው የ " ጳጳሳት " ሹሙት ምንድነበር ?

ትላንት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት ተፈፅሞ ጳጳሳትን የመሾም ተግባር መከናወኑን መግለጿ ይታወሳል።

ይኸው ሲመተ ጳጳሳት ፤ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ እውቅና ውጭ #በሕገወጥ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ነው ቤተክርስቲያን ያሳወቀችው።

ድርጊቱ በርካታ ምእመናንንም ያስደነገጠ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት በተፈፀመበት መልኩ ተከናውኗል ያለችውን ሹመት ማነው ያካሄደው ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-23-2
#ECSOC

ዛሬ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምከር ቤት የአገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ከጉዞው ዋነኛ ዓላማዎች ወስጥ ፦

• በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንበታ እና መልሶ-ማቋቋም ፈተናዎች እና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማት እና ለመረዳት፤

• የሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈናቃዮች በተሻለ ሁኔታ ለማድረስ፤ የምልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማስጀመር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ፤ በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ጋር ለመነጋገር እና ለመወያየት መሆኑን ታውቋል።

ፕሮግራሙ የተዘጋጀው ከትግራይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ተቋም ጋር በመተባባር መሆኑን ለመረዳት የቻልን ሲሆን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከስፍራው ተጨማሪ መረጃዎችን ይልካሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ECSOC ዛሬ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምከር ቤት የአገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ከጉዞው ዋነኛ ዓላማዎች ወስጥ ፦ • በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንበታ እና መልሶ-ማቋቋም ፈተናዎች እና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማት እና ለመረዳት፤ • የሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈናቃዮች…
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሀገር በቀልና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር 60 ልዑካንን በመያዝ መቐለ ገብቷል።

የጉዞው ወነኛ አላማዎች በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ፈተናዎችና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማትና ለመረዳት ነው።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በስፍራው ስለሚገኙ ሂደቱን እየተከታተሉ ያሳውቁናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሀገር በቀልና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር 60 ልዑካንን በመያዝ መቐለ ገብቷል። የጉዞው ወነኛ አላማዎች በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ፈተናዎችና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማትና ለመረዳት ነው። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በስፍራው ስለሚገኙ ሂደቱን እየተከታተሉ ያሳውቁናል።…
#አሁን

አሁን በመቐለ ከተማ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ልዑክ ከትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።

የትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት / ACSOT የቦርድ ሊቀመንበር እና የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ተስፋይ ገብረ እግዚያብሔር ውይይቱን ሲከፍቱ ከተናገሩት ፦

" ስለደርሰብን ስብራት ኣብዝተን በማውራት የምንቀይረው ብዙ ኣይኖርም።

በትንሹ ከተግባባን፣ በብዙ ከሰራን በመከራ ላይ ላለው ህዝባችን ልንደርስለት እንችላለን።

ሁኔታው ልትገነዘቡ የመጣቹህ እንግዶች፣ ትላንት ዕዱልን ኣጥታቹህ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታቹ ሳትወጡ ለቀራቹህ ሁሉ፣ ዛሬም ህዝባችን ስቃይ ኣለበቃም እና፣ ድምፃቹህ፣ እውቀታቹህ፣ ጉልበታቹህ ያስፈልገዋል እና

✓ መጠልያ ውስጥ ያሉት ወደ ቀያቸው፣ የተሰድዱትም ወደ ኣገራቸው

✓ ተማሪዎች ወደ ናፈቃቸው ትምህርታቸው፣ ሰራቶኞችም ወደ ስራቸው፣

✓ ህመምተኞች የሚፈልጉት መድሃኔት እንዲያገኙ፣ የተማላ የምግብ ኣቅርቦት እንዲኖር፤

✓ ነፃ የዜጎችና የሸቀጦች እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የባንክ ኣገልግሎት እንዲጀመር በፍፁም ቅንነት ድምፃቹ እንድታሰሙ፣ የምትችሉትን ሁሉ እንድትሰሩ በታላቅ ትህትና እጠይቃቸዋለሁኝ፣ ትችላላቹም። "

(ሙሉ ንግግራቸው ከላይ ተያይዟል)

Photo : Tikvah Family (Mekelle)

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።

ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።

በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።

ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ…
ፎቶ ፦ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከስልጣናቸው በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ አግኝተው ማናጋገራቸና ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ከሰሞኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰላሞን አረዳ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በምትካቸው አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

Photo Credit : PMOEthiopia

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና " ላልተገደበ ጊዜ " እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያገኙት ፈተናውን ወስደው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ተብሏል።

ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው መውሰድ የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሀመድ ለኢፕድ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየስድስት ወሩ ፈተናውን የሚወስዱበት ዕድል እንዳለ ኃላፊው ጠቁመዋል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ የፈተና ወጪያቸው እንደሚሸፈንላቸው ገልጸዋል።

በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ የሚሰጡ ከ300 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉ ያነሱት ኃላፊው፤ በየትምህርት መስኩ እየተደረገ በአስር ዙር ፈተናው ለመስጠት ታቅዷል።

#ኢፕድ

More : @tikvahuniversity