TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሀገር በቀልና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር 60 ልዑካንን በመያዝ መቐለ ገብቷል። የጉዞው ወነኛ አላማዎች በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ፈተናዎችና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማትና ለመረዳት ነው። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በስፍራው ስለሚገኙ ሂደቱን እየተከታተሉ ያሳውቁናል።…
#አሁን

አሁን በመቐለ ከተማ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ልዑክ ከትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።

የትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት / ACSOT የቦርድ ሊቀመንበር እና የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ተስፋይ ገብረ እግዚያብሔር ውይይቱን ሲከፍቱ ከተናገሩት ፦

" ስለደርሰብን ስብራት ኣብዝተን በማውራት የምንቀይረው ብዙ ኣይኖርም።

በትንሹ ከተግባባን፣ በብዙ ከሰራን በመከራ ላይ ላለው ህዝባችን ልንደርስለት እንችላለን።

ሁኔታው ልትገነዘቡ የመጣቹህ እንግዶች፣ ትላንት ዕዱልን ኣጥታቹህ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታቹ ሳትወጡ ለቀራቹህ ሁሉ፣ ዛሬም ህዝባችን ስቃይ ኣለበቃም እና፣ ድምፃቹህ፣ እውቀታቹህ፣ ጉልበታቹህ ያስፈልገዋል እና

✓ መጠልያ ውስጥ ያሉት ወደ ቀያቸው፣ የተሰድዱትም ወደ ኣገራቸው

✓ ተማሪዎች ወደ ናፈቃቸው ትምህርታቸው፣ ሰራቶኞችም ወደ ስራቸው፣

✓ ህመምተኞች የሚፈልጉት መድሃኔት እንዲያገኙ፣ የተማላ የምግብ ኣቅርቦት እንዲኖር፤

✓ ነፃ የዜጎችና የሸቀጦች እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የባንክ ኣገልግሎት እንዲጀመር በፍፁም ቅንነት ድምፃቹ እንድታሰሙ፣ የምትችሉትን ሁሉ እንድትሰሩ በታላቅ ትህትና እጠይቃቸዋለሁኝ፣ ትችላላቹም። "

(ሙሉ ንግግራቸው ከላይ ተያይዟል)

Photo : Tikvah Family (Mekelle)

@tikvahethiopia