TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ? የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦ " ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት። ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም። ስርዓተ…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔውም በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ ተወያይቷል።

በዚህም ፤ ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የሕዝብ ( #የተማሪ_ወላጆችን_ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው ዕለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ  (ሁለተኛ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው  ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ፤

4ኛ:-  ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች #አረብኛና #ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፤

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን፤

6ኛ:-  በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የሥራ እና ቴክኒክ ትምህርት  በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ በሚያስቀምጠዉ መስረትና ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና  በተጠናው ጥናት  መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ፤

7ኛ:-  የግል ትምህርይ ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ  250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia