TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል። @tikvahethiopia
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ መሀመድ (አሊ ቢራ) ማን ነበር ?

- አርቲስት አሊ ቢራ የተወለደው (በ1940 ዓ/ም) እና ያደገርው የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የመተሳሰብ መገለጫ በሆነችው ድሬዳዋ ነው።

- እናት እና አባቱ ያወጡለት ስም አሊ መሀመድ ነው።

- " አሊ ቢራ " የሚለው ስም የመጣው እኤአ 1963 በድሬድዋ ከተማ እራሱን አሊ መሀመድን ጨምሮ የሙዚቃ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ተሰብሰበው በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ለመጫወት በተደራጁበት ወቅት በግሩፑ ውስጥ ሶስት አሊዎች ነበሩ (አሊ ሸቦ፣ አሊ አህመድ አሊ / አሊ ቱቼ ፣ እራሱ አሊ መሀመድ) እነሱን ለመለየት ነው የመጀመሪያ እና እጅግ ተቀባይነት ባገኘው የሙዚቃ ስራው በሆነው " Birraa dha Bairhe " አሊ ቢራ የሚለውም ስም ያገኘው። ከዚህ በኃላ በፓስፖርት፣ መታወቂያ ... አሊ ቢራ እየተባለ መጠራት ጀምረ።

- አርቲስ አሊ ቢራ ፤ የሙዚቃ ስራውን የጀመረው በ14 ዓመቱ በድሬዳዋ " አፍረንቀሎ (አራቱ የቀሎ ልጆች) " የሙዚቃ ቡድን ውስጥ ነው። (በእድሜ ትንንሽ የነበሩት የሙዚቃ ቡድኑ አባላት B ቡድን ውሥጥ ነበሩ አሊ ቢራ በመጀመሪያው ስራ እጅግ ዝናን ስላገኘ ወደ A ቡድን ተቀላቀለ)

- አርቲስት አሊ ቢራ በህይወት በነበረበት ሰዓት ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ስራ ቆይቷል። በርካታ የአልበም ፣ የነጠላ የሙዚቃ ስራዎችን ሰርቷል። በበርክታ የዓለም ሀገራት ተዘዋውሮ ከሙዚቃ ስራዎቹን አቅርቧል።

- አርቲስት አሊ ቢራ በአፋን ኦሮሞ ፣ ሀደርኛ፣ ሶማሊኛ ፣ አማርኛ ፣ አፋርኛ ከውጭ ሀገር ደግሞ በእንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ ቋንቋዎች የመዝፈን ድንቅ ችሎታ ነበረው። የሙዚቃ መሳሪያዎችንም የሚጫወት ሲሆን የዜማ እና የግጥም ደራሲም ነበር። ከአፍረንቀሎ በተጨማሪ በተለዩ በተለያዩ የሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ ሰርቷል።

- ለአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እድገት ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን ኢትዮጵያውያንን በጥበብ ስራዎቹ በማስተሳሰር ፣ በማዋደድ የህዝቡን ስሜት በማንፃባረቅ በመላው የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አንጋፋ ተብለው ከሚጠሩ የጥበብ ሰዎች #ቀዳሚው ነው።

- በህይወት ዘመኑ ላበረከተው በጎ አስተዋፆ ፤ በርካታ ሽልማቶችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ተሸልሟል።  ለአብነት ፦ ከድሬዳዋ እና ከጅማ የክብር ዶክትሬት አግኝቷል፣ በድሬዳዋ ውስጥ ፓርክ በአዳማ ደግሞ መንገድ ተሰይሞለታል ፤ በኦሮሚያ ክልል ልዩ የኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል... ሌሎችም በርካታ እውቅናና ሽልማቶች አግኝቷል።

- ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ከባለቤቱ ጋር በመሆን " Birra Children's Education Fund " የተባለ ምግባረሰናይ ድርጅት አቋቁሞ " ለህፃናት ትምህርት " ድጋፍ ሲሰጥም ነበር።

- የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ትላንት በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

(ስለ አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ለመናገር እና ለመፅሀፍ ጊዜውም ሆነ ቦታውም ባይበቃም በአጭሩ ስለ ህይወቱ ትንሽ የሚያስረዳው ከላይ የቀረበው ፅሁፍ በተለያዩ ጊዜያት ለመገናኛ ብዙሃን ከሰጣቸው ቃለመጠይቆች የተወሰደ እንደሆነ እንገልፃለን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል " - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦ 1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣ 2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ 3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል። ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ…
#Update

ታስረው የነበሩት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ትላንት መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልፀዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ፤ ዳኞቹ ከተፈፀመባቸው የዘፈቀደ እስር መለቀቃቸውን ገልፀው ባለስልጣናት ግን ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎህ የወንጀል ዳኛ የሆኑት ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ፣ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ከሚሰሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ በኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ነበር።

ይህን ጉዳይ ተከትሎ እስሩ ፈፅሞ ህገወጥ እና በዳኝነት ነፃነት ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው ሲል ኢሰመኮ ገልጾ ነበር ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊም የኢሰመኮን ሪፖርት ተከትሎ የዳኞቹ መታሰር በጣም አሳሳቢ መሆኑን ገልፀው ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖባት " ያለመከሰስ ማብታቸው " ከተነሳ በኃላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ " መንግስት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው ተመልሰዋል። "…
#Update

የኢትዮጵያ እና የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ኬንያ፣ ናይሮቢ ላይ ተገናኝተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ጀነራል ታደስ ወረደን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ናቸው እየተነጋገሩ የሚገኙት።

በሰላም ስምምነቱ በ5 ቀናት ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ በሚያዘው መሠረት ነው የአዛዦቹ ውይይት የተጀመረው።

ይህ በተመለከተ አፍሪካ ህብረት (AU) ባወጣው መግለጫ ሁለቱ የጦር አመራሮች በደቡብ አፍሪካ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ነው ምክክር የጀመሩት ብሏል።

ዛሬ የጀመረው ውይይት በትግራይ አስችኳይ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር ተከፍቶ የተቋርጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ምክክር ይደረግብታል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለው ንግግር ለቀጣይ ቀናትም ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Nairobi

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ናይሮቢ ላይ የተናገሩት ፦

" የቴሌኮም፣ የኢነርጂ እና የባንክ አገልግሎቶችን መልሰን ማገናኘት አለብን።

ከዚያ በፊት ግን ሰዎቻችን በቅድሚያ ምግብ እና መድኃኒት ይፈልጋሉ። ይህን ለማፋጠን እየሞከርን ነው።

ክልሎችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች በባለፉ ጉዳዮች ከመዘፈቅ ይልቅ ተስፋ እንዲፈነጥቁ እና መጪውን ጊዜ በጸጋ እንዲቀበሉ መንግስት እያበረታታ ነው። "

አቶ ጌታቸው ረዳ (ከህወሓት) ፦

" በስምምነታችን የተካተቱ ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ።

ከእነዚህ ተግባራት መካከል የአገልግሎቶች መጀመር አንዱ ነው።

የአገልግሎቶቹ ቁጥር ከፍ ሲልም በተደራዳሪ ወገኖች መካከል የሚኖረው መተማመን እና ግንኙነት አብሮ ይጨምራል፤ በሰዎች አዕምሮ ውስጥም ተስፋ ይዘራል ፤ ለማስፈን እየሞከርን ያለውን ሰላም የበለጠ ያጠናክራል።

" ... እኛ የገባነውን ቃል ለማክበር ቁርጠኛ ነን። "

ኡሁሩ ኬንያታ ፦

" በፕሪቶሪያ ጀመርን፣ መንገዳችን እየተጠጋ ፤ አሁን ናይሮቢ ነን ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባችን መቐለ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ ፤ በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ አብረን እናከብራለን። ይህ ጸሎታችን ፣ ተስፋ የምናደርገው እና የምንፈልገው ነው። "

* ቪድዮው እና የኬንያታ ንግግር ከCitizen TV Kenya እንዲሁም የአምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የአቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር በኢትዮጵያ ኢንሳይደር ከቀረበ ዘገባ ላይ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ዋጋ #በጥቅምት_ወር በነበረው እንደሚቀጥል ገልጿል።

የነዳጅ ዋጋው ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ነው።

በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ጀምሮ ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በግብፅ ፣ ሻርም አል-ሼይክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከ100 በላይ የሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ነው።

ዶክተር ዐቢይ ፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን  ከበርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።

ከአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋርም በጋራ የትኩረት  ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ የምትጋራ ሲሆን፣  የመፍትሔዎች አንድ አካል ለመሆን  ቁርጠኛ ናት። " ብለዋል።

@tikvahethiopia
" ... እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ህወሓትን በመወከል በፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ላይ የተሳተፉት እና በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ  ዛሬ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ከኬንያ ሆነው በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" ሰላም ህዝባችን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ነገር ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ "  የሕዝባችንን ጥቅም ለማስጠበቅ የገባውን ቃል ማክበር መቻላችን ጊዜ የሚፈታው ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ፅሁፍ ላይ ፤ " ወደ ጦርነት የገባነው ፈልገነው ሳይሆን እንደ ህዝብ ህልውናችን አደጋ ውስጥ በመግባቱ ነው" ብለው " የሰላም ስምምነት መፈረም የትግራይን ሕዝብ ሕልውና የሚያስጠብቅ ከሆነ ፣ #ለሰላም ለምን ዕድል አንሰጠውም ? " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ በናይሮቢ የተጀማረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የሰላም ንግግር (በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች መካከል) ተሳታፊ ናቸው ይኸው ውይይት ለቀጣይ ቀናት ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቅዳሜ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሰላም ስምምነት በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት " ህወሓት "ን ትጥቅ ስለማስፈታት እና በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫ ተከናውኖ የክልል መንግስት የሚመሰርተው አካል ክልሉን ለመጠበቅ መሳሪያ የመታጠቅ መብቱን በመጠቀም ረገድ ላይ ግርታ ሊኖር እንደማይገባ አስረድተዋል።

አምባሳዳር ሬድዋን በትግራይ በምርጫ ስልጣን የሚይዘው አካል ልክ እንደ ሌሎቹ ክልሎች በቂ የፀጥታ ኃይል እንደሚያደራጅ አረጋግጠዋል። 

መንግስት ህወሓት በሽብርተኝነት የተፈረጀበትን ድንጋጌ መልሶ እንዲመለከተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብም አምባሳደር ሬድዋን ጠቁመዋል። 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በተያያዘ የተናገሩት ፦

" ህወሓትን ትጥቅ ማስፈታት ብለን ስንናገር እና የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይል ያደራጃል ስንል ወዳጆቻችን ግርታ ሊገባቸው ይችላል።

ክልሎች የራሳቸው #የተመጠነ የፀጥታ ኃይል አላቸው ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል ከዚህ ጋር ነው መታየት ያለበት።  አሁንም ደግሜ የምለው ግን ይህ የሚሆነው ለትግራይ ክልላዊ መንግስት እንጂ ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። "

Credit : Journalist Solomon Muchie / ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia