TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#KENYA

የጎረቤታችን ኬንያ ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አማፂያንን ለመዋጋት እና የቀጠናውን ሰላም ለማስከበር ወደ ምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ይሰማራሉ።

የሰራዊቱ አባላት ዛሬ ተሸኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከቀጠናው ጦር ጋር የሚቀላቀሉትን የኬንያ መከላከያ ሰራዊት አባለትን ስንብት ስነ ስርዓት ያካሄዱ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ የሰንደቅ አላማ የመስቀል ስነስርዓት ተካሂዷል።

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚሰማራው የኬንያ ጦር የምስራቅ አፍሪካ ማህብረሰብ አካል በመሆን የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጦር በአገሪቱ ግጭትና ሁከትን ለማስቆም የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል።

" የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሃገራት " በያዝነው አውሮፓውያኑ ዓመት መጀመሪያ ላይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ አማጽያንን ለመዋጋት ወታደሮችን የማሰማራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የኬንያ ጦር ሰራዊት የመጀመሪያ ተልዕኮ በሰኔ ወር በM 23 አማፂያን ቁጥጥር ስር ያለችውን የድንበር ከተማ ቡናጋናን መልሶ ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዘመቻ ማገዝ እንደሚሆን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" መግለጫው ዘግይቷል ፤ ነገር ግን ወደ በኃላ ይሰጣል "

ዛሬ ከሰዓት ላይ ሊሰጥ የነበረው የአፍሪካ ህብረት መግለጫ #መዘግየቱን ነገር ግን መግለጫው ወደ በኃላ #እንደሚሰጥ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።

መግለጫው ለምን ሊዘገይ እንደቻለ የተሰጠ ማብራሪያ የለም። ወደ በኃላ ይባል እንጂ ትክክለኛ ሰዓቱም አልተገለፀም።

በደ/አፍሪካ ፕሪቶሪያ እየተካሄደ ካለው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት " የሰላም ንግግር " ጋር በተያያዘ እስካሁን ስላለው ሂደት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሚሰጡት በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕ/ት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ናቸው።

በርካቶች እየጠበቁት ያለው መግለጫ  በደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት #የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ እንደሚተላለፍ  መ/ቤቱ ገልጿል👇
https://www.facebook.com/DIRCOza

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከሀገር ውጭ (በጂቡቲ) በኩል በሚያልፉ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ #በመጠባበቂያ_መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

በዚህ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል የገለፀው ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ባለሙያዎቹ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጿል።

እስከዚያው ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁት በትህትና ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት የቆየችው ላሊበላ ከተማ ዛሬ እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኘች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል። ከላሊበላ ከተማ በተጨማሪ ላስታ ወረዳና ሙጃ ከተማ ኤሌክትሪክ እንዳገኙ ተገልጿል። እነዚህን አካባቢዎች መልሰው ኃይል ያገኙት በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኬ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ…
#Update

" የሁመራና ወልቃይት ከተሞች #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ። " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የሁመራ - ወልቃይት - ሽሬ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ገልጿል።

በጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ስራዎቹን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ህብረተሰቡ #ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

#የሁመራ - #ወልቃይት - #ሽረ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና የማከፋፈያ ጣቢያ የፍተሻና የጥገና ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፀው ተቋሙ " ከሁመራ እስከ ሽሬ ባለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በተደረገው የፍተሻና ጥገና ሥራ 67 ቦታዎች ላይ የኮንዳክተር እንዲሁም 3 ቦታዎች ላይ የፋይበር ኦፕቲክስ መቆራረጥ አጋጥሟል። " ብሏል።

የሁመራና ወልቃይት ከተሞች እና አካባቢያቸው ለረጅም ጊዜ ያህል ኃይል ተቋርጦ የቆየ በመሆኑ #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ሲል አክሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
#LIVE

በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ ሲደረግ ከነበረው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስላለው ሂደት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በደቡብ አፍሪካ ፤ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ መከታተል ይቻላል👇
https://www.facebook.com/DIRCOza

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#LIVE በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ ሲደረግ ከነበረው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስላለው ሂደት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ መግለጫ እየሰጡ ነው። በደቡብ አፍሪካ ፤ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ መከታተል ይቻላል👇 https://www.facebook.com/DIRCOza @tikvahethiopia
#BREAKING

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህ የተገለጸው በደቡብ አፍሪካ ሲያደረግ የነበረው የሰላም ንግግር ውጤት በተገለጸበት ወቅት ነው።

የፌደራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ይዘት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እየገለጹ ነው።

@tikahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰላም ስምምነት ዛሬ በፕሪቶሪያ ይፈረማል። ነገር ግን የስምምነቱ ትግበራ " ወሳኝ ይሆናል " ሲሉ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ አሁን ተናግረዋል። @tikvahethiopia
#ሰላም #Peace

" ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ "

በአፍሪካ ህብረት መሪነት በዛሬው ዕለት በፕሪቶሪያ በተደረሰው "  የሰላም 🕊 ስምምነት " መሰረት ፦

- በዘላቂነት ግጭት ለማቆም ፣
- ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ
- የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነትን ለማረጋጋጥ
- #አገልግሎቶችን_ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ከስምምነት ላይ ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል በስርዓት የሚመራ እና ተከታታይ የትጥቅ መፍታት አንዱ ነው። በአጠቃላይ ፤ ዛሬ የተደረሱትን ስምምነቶች የአፍሪካ ህብረት ቡድን ይከታተላል። @tikvahethiopia
#Update

የሰላም ስምምነቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈራርመዋል።

ከተፈራረሙ በኃላም እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።

በአጠቃላይ የተደረሱትን የስምምነት ነጥቦችን የያዘው እና በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል (አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ) የተፈረመበት ወረቀት እንደደረሰን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰላም ስምምነቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈራርመዋል። ከተፈራረሙ በኃላም እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል። በአጠቃላይ የተደረሱትን የስምምነት ነጥቦችን የያዘው እና በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል (አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ) የተፈረመበት ወረቀት እንደደረሰን የምንልክላችሁ ይሆናል። @tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ የወጣው የጋራ መግለጫ 12 ነጥብ የያዘ ነው።

ከዚህም ስምምነት መካከል ፦

- የህወሓት ቡድን #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል።

- የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል።

- ኢትዮጵያ #አንድ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ብቻ አላት በሚለው ስምምነት ተፈርሟል።

- በመሬት ላይ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ተዋጊዎችን ከሠራዊቱ እንዲወጡ ለማድረግ እና መልሶ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቀላቀል ስምምንት ላይ ተደርሷል።

- #የጥይት_ድምጽ_በዘላቂነት_እንዳይሰማ  በመስማማት፣ ጦርነቱ እንዲያበቃ የሚያስችል ዘላቂ የግጭት ማስወገድ ስምምነት ተፈርሟል።

-  በትግራይ ክልል ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እና የሽግግር እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈርሟል።

- የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለማቆም ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስምምነት ተፈፅሟል።

@tikvahethiopia