TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቦረና

በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖሩት።

በድርቅ ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

(በድብሉቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች)

የ7 ልጆች እናት ወ/ሮ ጂሎ ጉራቻ ፦

" የዘንድሮው ድርቅ የነበሩንን ከብቶች እና ሁሉንም ንብረቶችን ነው ያወደመብን። ባዶ እጃችንን ስንሆን ወደዚህ መጣን ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ በምግብ እና ውሃ እጥረት እየተቸገርን ነው። በተለይም ህፃናት ነፍሰጡር ሴቶች፣ አዛውንቶች በምግብ እጥረት እየተጎዱ ናቸው። እኛ እዚህ ከሰፈርን ከ6 ወር በላይ ሆኖናል። በመጠለያው በጣም ብዙ ቤተሰቦች ነው ያሉት። በቆይታችን አንዴ ብቻ ነው ለተወሰኑ ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ የተሰጠው እንጂ ምንም አላገኘንም። ስለዚህ በጣም ችግር ላይ ውስጥ ነው ያለነው። "

የ6 ልጆች አባት ዳለቻ ዲዳ ፦

" ምንጠጣው ውሃ በጣም የቆሸሸ ነው። እንስሳት ሲሞቱ ከሚጣሉበት ነው ልጆቻችን የሚቀዱልን። በዛ ላይ የመፀዳጃ ቦታም የለንም። እንዲሁ በበሩ ደጃፍ ነው ይህ ሁሉ በዚህ የሰፈረው ህዝብ የሚፀዳዳው ስለዚህ የበሽታ ወረርሽኝ ፍራቻ አለብን። ሌላው የመጠለያ ቦታና ላስቲክ ሰጥተውናል። ይህ ላስቲክ #ብርድ የሚከላከል አይደለም። እናም በጣም ችግር ውስጥ ነን። "

የልጆች እናቷ ትዬ አደንጌ ፦

" #ብርዱ_በጣም_አስቸጋሪ_ነው። ለምግብ ፍለጋ ነው ከእሳት አጠገብ የምንነሳው። በዛ ላይ የምንለብሰው ልብስ የለንም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Borana-08-23 #ገልሞ_ዳዊት

@tikvahethiopia
* ቡልቡሎ

የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ " ቡልቡሎ " ላይ በጎርፍ በመቆረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት እየተዳረገ እንደሚገኝ የወረባቦ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ዙሪያ መልዕክት የላኩ ሲሆን መንገዱ በጎርፍ በመቋረጡ ከፍተኛ የሆነ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።

የወረባቦ ኮሚኬሽን ያናገራቸው የፖወርኮን መንድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት የሀይቅ ቢስቲማ ጭፍራ መንገድ ግንባታ አስተባባሪ አቶ አለሙ አባይነህ ተከታዩን ብለዋል፦

" ድርጅታችን በአጠቃላይ መንገዱን ከመስከረም በኋላ ሙሉ ጥገና ያደርጋል። አሁንም በመንገዱ ላይ የተሰበሩና ለትራንስፖርት መስተጓጉል የሚፈጥሩ ቦታዎች ላይ ጊዜያዊ ጥገና እያደረግን እንገኛለን።

ነገር ግን ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት መንገዶቹ የተቆረጡበት ቦታ የወሰን ማስከበርና የሴሌክት ማቴሪያል እጥረት እያጋጠመ ነው "

የወረባቦ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሰይድ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል፦

" የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ የአስፓልት መንገድ ለመስራት በፌደራል መንግስት ለተቋራጭ የተሰጠ በመሆኑ ወሎ ገጠር መንገድ ከጥገና አገልጎሎቱ ላይ አስወጥቶታል በዚህም መንገዱን እየጠገነ የሚያስተዳድረው ተቋራጭ ድርጅቱ ፖወርኮን ነው።

ፓወርኮን በአሁኑ ሰአት መንገዱን ሙሉ ጥገና ለማድረግ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መጠገን ስለማልችል ሙሉ ጥገና ከመስከረም በኋላ ይደረጋል።

ነገር ግን ዛሬ ላይ ቡልቡሎ አውራጎዶና አካባቢ ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመቆረጡ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት መኪኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የተቆረጠበት ቦታ ከወደፊት አንፃር ለጥገና በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በጋቢዎን መታሰር ይኖርበታል። "

ፎቶ፦ ወረባቦ ኮሚኒኬሽን፣ ABD (ቲክቫህ ቤተሰብ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ! ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። አሁን ላይ 4ተኛ…
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት 4ኛ ዙር በማጠናቀቅ 240 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስቴም ፓወር በቀጣይ አምስተኛ ዙር ሰልጣኞችን መዝገባ በማከናወን ሥልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ሥልጠናው መሰጠት ይጀምራል። በኦላይን ለመሰልጠን ለተመዘገቡም ስለጠናውን እየተሰጠ ይገኛል።

ከ4ኛው ዙር የተመረጡ ምርጥ 4 ፕሮጀክቶች፦

1. ግብርና እና ምግብ ዘርፍ፦

- ዮፍታሔ ሳሙኤል - Mushroom Agro-processing

- ​​ስጦታው አበራ - Punt Flour from Gipto

2. አገልግሎት ዘርፍ፦

- Wujo Digital Iqub

3. ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ:

- መኮንን አስማረ - Agricultural Chemical Spray & Aerial Mapping Drone

በልዩ ዘርፍ፦ ዶ/ር ትዝታ አለሙ - Biruh Hiwot Mental Health Consultancy

#STEMpower #VISA #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

የዘንድሮው ክረምት ተጠንክሮ በመቀጠሉ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ።

በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያላችሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ለማስታወስ እንወዳለን።

የመኪና አሽከርካሪ የሆችሁ ቤተሰቦቻችንም በየአካባቢው እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የራሳችሁን እና የሌሎችንም ወገኖች ደህንነት ልታስጠብቁ ይገባል።

ሌላው ልጆች ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ልጆቻሁን ጠብቁ ፤ በተቻለ መጠን ከባድ ዝናብ ሲጥል ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ በማድረግ ወቅቱን ማሳለፍ ይገባል። እጅግ አስፈላጊ ቦታ የሚሄዱ ከሆነም እንዲጠነቀቁ ማሳሰብ እንዳትዘነጉ።

#መልዕክት : ክረምት ሲመጣ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖቻችን ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ይታወቃል ፤ በግለሰብ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ባንችልም አንዳንድ የሚለበሱ ለብርድ የሚሆኑ አልባሳትን በመስጠት እንደሁል ጊዜው በበጎ ስራችን እንቀጥል።

ቪድዮ : AN ከአዲስ አበባ (አዳዋ ድልድይ) ቲክቫህ ቤተሰብ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE " የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች…
#NationalExam

መስከረም 30 ቀን 2015 መሰጠት የሚጀምረው የ2014 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና " ተሰርቆ ወጥቷል " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆነን  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎተ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከፈተና ስርቆት ጋር በተያያዘ እተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዘንድሮ " ነው ተብሎ የሚሰራጨው ፈተና በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ እንደሆነ አስረድተዋል። እየተሰራጩ ያሉት ፈተናዎች ዓመቱ ኤዲት ተደርጎ መሆኑንም አመልክተዋል።

" ተፈታኝ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩ መሰል መረጃዎችን ከማመናቸው በፊት የአሰራጩን ታማኝነት እንዲያጣሩና ትክክለኛነቱን እንዲመረምሩ " መልዕክታቸውን አስተላፈዋል።

የአገር አቀፍ ፈተናን የተመለከቱ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት " ፖለቲካን ከታዳጊዎች ህይዎት ቢለዩ መልካም ነው " ሲሉ ለ " ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ አጣሪ ድረገፅ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

የ2014 ዓ/ም የሀገር አቀፍ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሁለት ዙር የሚሰጥ ይሆናል።

ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንደሰማነው ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ይገኛል ፤ ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam መስከረም 30 ቀን 2015 መሰጠት የሚጀምረው የ2014 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና " ተሰርቆ ወጥቷል " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆነን  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የአገልግሎተ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከፈተና ስርቆት ጋር በተያያዘ እተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፀዋል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዘንድሮ "…
#Update

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

@tikvahethiopia