TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ጥንቃቄ የተሞላበት የህዝብ የሕይወት ጥበቃ ይደረግ "

ከላይ በፎቶው ላይ የሚታየው ርብ ሞልቶ በመሃል አስፋልት የሚጓዘው ጎርፍ ነው።

የፎገራና የሊቦ አጎራባች ወረዳና ቀበሌዎች የሰው ሕይወት እንዳይጎዳ ጥንቃቄ የተሞላበት ህዝብን ወደ ተራራማ ቦታዎች ማስፈር እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

(ደቡብ ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን)

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል።

የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች፤ በ" ክላስተር" የሚደራጀውን አዲስ ክልል የመቀላቀል ውሳኔን ያጸደቁት በሙሉ ድምጽ መሆኑን ተነግሯራ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚል ስያሜ ያለው አዲስ ዞን ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብም በተመሳሳይ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ተነግሯል።

የ4ቱ ወረዳዎች ም/ቤቶች ዛሬ የወሰኗቸውን ውሳኔዎች ለፌደሬሽን ም/ቤት ያስገባሉ ተብሏል።

የፌዴሬሽን ም/ቤት ወረዳዎች እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች የማሳለፍ ስልጣን አላቸው ወይ ? በሚል ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

የም/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ " ምክር ቤቶቹ ስለ ህዝብ ጥያቄ የመወያየት፤ ተወያይተውም ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን አላቸው፤ ሆኖም ጥያቄው የሚቀርበው #በዞን እና #በክልል ምክር ቤቶች አልፎ ነው " ሲሉ ማስረዳታቸውን #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የጉራጌ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዞኑን ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳ ጋር አንድ ላይ በክልል እንዲደራጅ በመንግስት የቀረበውን ምክረ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎ ነበር።

በምክር ቤቱ ከተገኙ 92 አባላት ውስጥ 40ዎቹ የ " ክላስተር " አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ የደገፉ ቢሆንም 52 አባላት ክላስተርን በመቃወማቸው ነው ምክረ ሀሳቡ ውድቅ የተደረገው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምህርት_ሚኒስቴር " ፈተናው የሚቀር አይደለም " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ * ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ ! የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦ " ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር " የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " ን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል።

በ2015 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው መመሪያው፤ የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ነው ተብሏል።

መመሪያ ቁጥር 919/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ መሰራጨቱ ታውቋል።

አምስት ክፍሎች እና 27 አንቀጾች ያሉት አዲሱ መመሪያ፤ ከነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና እንደሆነ ተደንግጓል።

በመመሪያው ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማንኛውም ሁኔታ የጣሰ፣ እንዲጣስ ያደረገ በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካል ተጠያቂ እንደሚሆን በመመሪያው ተመላክቷል።

More : @tikvahuniversity
#Egypt

በዛሬው ዕለት የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር አድርገዋል።

በዚህ የካቢኔ ሹም ሽር ላይ የውሃና መስኖ ሚንስትሩ ሞሐመድ አብድል አቲን (የታላቁ ግዳሴ ግድብን ድርድር የሚመሩ) ከሥልጣን ተነስተው በሌላ ሰው ተተክተዋል።

ሞሐመድ አብድል አቲን የተከቱት ዶ/ር ሐኒ ስዌይላም የተባሉ ሰው ሲሆኑ ታዋቂ የውሃ ሃብት ተመራማሪ ናቸው ተብሏል። በካይሮ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲም እንደሚያስተምሩ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ሲሲ ሌሎች የካቢኔ ሹም ሽሮችንም ያደረጉ ሲሆን አጠቃላይ የ13 ካቢኔ አባላት ሹም ሽር ነው ያደረጉት።

የጤና፣ የቱሪዝም፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ፣ የሲቪል አቪየሽን፣ የትምህርት እና ሌሎች ሚኒስትሮችንም በአዲስ ተተክተዋል ተብሏል።

አል ሲሲ የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የፋይናነስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እንዳልቀየሩም  ተገልጿል።

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባን ያደረገው የሃገሪቱ ፓርላማም በፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ሹም ሽር በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን አል ዓይን የሀገሪቱን ሚዲያዎች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር ያደረጉት የመንግሥታቸውን የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል እና የግብጻዊያንን ጥያቄ ለመመለስ እንደሆነ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እስካሁን ውጤቱ ያልታወቀው የኬንያ ምርጫ ከምን ደረሰ ?

በኬንያ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከተገኘው ውጤት ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆነው በምርጫ ኮሚሽኑ #የተረጋገጠ ሲሆን ሁለቱ ተፎካካሪ እጩዎች በቅርብ ርቀት በመፎካከር ላይ ናቸው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

እስካሁን በተረጋገጠ ድምጽ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 51 በመቶ ሲመሩ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 48 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ ማክሰኞ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ይፋ ማድረግ በጣም አዝጋሚ መሆኑን አምኗል።

በሁለቱ ዋና ዋና እጩዎች ደጋፊዎች ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎም ውጤቱን የማረጋገጥ ሥራ በተደጋጋሚ ተቋርጧል። 

የራይላ ደጋፊዎች ውጤቱን የማጣራት ሂደቱን በተደጋጋሚ ማስተጓጎላቸው ታውቋል። አንዳንድ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ድምጽ እያጭበረበሩ ነው በማለት ከሰዋል።

እስካሁን ባለስ ከ292 የምርጫ ክልሎች የ141 ቱ ውጤት ተረጋግጧል።

ዛሬም ድረስ የመጨረሻ ውጤቱ የሚታወቅበት ቀን ባይታወቅም የምርጫ ኮሚሽኑ ድምጽ የማጣራት ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

የአሸናፊውን ዕጩ ማንነት የሚያሳውቀው ኮሚሽኑ ይሆናል። 

ምርጫውን ለማሸነፍ ዕጩዎች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የመራጮች ድምጽ ማግኘት እና በ24 ክልሎች ከ25 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። 

ካልሆነ ምርጫው በድጋሚ ጷጉሜ ወር ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን ! በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦ • መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው። • የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ…
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥያቄ !

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ሒደቱ አሁን ምን ይመስላል ?  

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

" በሲቪል ሰርቪስ ባለሙያዎች የሥራ መዘርዝር በድጋሚ ታይቶ ሌላ የደረጃ ምዘና ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ረዳት ምሩቅ ሁለት፣ ረዳት ሌክቸረር፣ ሌክቸረር፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርና ረዳት ፕሮፌሰር ደረጃዎች ተሻሸለዋል፡፡

የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ግን ከነበረበት ደረጃ አልተሻሻለም፡፡ ለፕሮፌሰር ደረጃ ቀድሞም በ2011 ዓ.ም. ላይ ማሻሻያ ሲደረግ ደመወዝ የተጨመረው 233 ብር ገደማ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን በትምህርት ላይ ያሳለፉ፣ እዚህ ለመድረስ ብዙ ጥናት ያሳተሙና ያማከሩ ናቸው፡፡

ውሳኔዎች ሲተላለፉ የአገር አቅም ከግምት ውስጥ የሚገባ ቢሆንም፣ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ሌላ የገቢ ምንጭ የላቸውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ማስተርስ ያላቸው ሆነው በታወቁ ጆርናሎች ላይ ጥናታቸውን ያሳተሙ መምህራን ረዳት ፕሮፌሰር መሆን ይችሉ ነበር፡፡

አሁን በወጣው ደረጃ ግን ረዳት ፕሮፌሰር ለመሆን ሦስተኛ ዲግሪ ስለሚያስፈልግ፣ ማስተርስ ኖሯቸው ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑ መምህራን በአዲሱ ደረጃ የተቀመጠውን የደመወዝ ጭማሪ አያገኙም፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስናነጋግር የሚያነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሰዎች በማስተርስ ደረጃ ረዳት ፕሮፌሰር የሚሆኑ ከሆነ ዶክትሬት ለመማር አይበረታቱም የሚል ነው፡፡

የትምህርት ዕድል ሲሰጣቸው ባለንበት ረዳት ፕሮፌሰር መሆን እንችላለን የሚሉ እንዳሉ ይነገራል፡፡

ይህንንና የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ደረጃ አለመሻሻሉን ጉዳይ ገና እየተወያየንበት ነው፡፡ "

ያንብቡ : telegra.ph/RE-08-14-3

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል። የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል። የማረቆ፣ ቀቤና፣…
የደቡብ ክልል ዕጣፋንታ ምን ይሆን ?

መንግስት ክልሉ በክላስተር ተከፍሎ በአጎራባች ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በመሆን ሁለት አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህን አቅጣጫ ከተትሎም የዞን እና ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች በየም/ቤቶቻቸው በመሰባሰብ በቀረቡላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ ውሳኔያቸውንም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አስገብተዋል።

አዎ! በመንግስት አቅጣጫ መሰረት በአንድ ላይ ሆነን በአዲስ 2 ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ያፀደቁ አጠቃላይ 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ግን በብቸኝነት የጉራጌ ዞን " ክላስተር አልደግፍም ፤ የህዝቡም ፍላጎት አይደለም ፤ እኛ የምንፈልገው በክልል መደራጀት ነው ፤ ይህም በህጋዊ መንገድ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል " ሲል የክላስተር አደረጃጀትን በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህ በኃላ ግን በዛው በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በዞናቸው ም/ ቤት በአብላጫ ድምፅ የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ በመግለፅ " ክላስተር እንደግፋለን " የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

ውሳኔ ያሳለፉ (ትላንት) የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች ሲሆኑ #ዛሬ ደግሞ የቡኢ ከተማ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ እና የሶዶ ወረዳ ምክር ቤቶች "ክላስተር እንደግፋለን " በሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

" ፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ይቀመጣል "

የፌዴሬሽን ም/ቤት በ " ደቡብ ክልል " አደረጃጀት ጉዳይ ላይ ነሃሴ 12 #አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ እና ከክልሉ ጋር ተያይዞ የሚወስናቸው ውሳኔዎች እንደሚኖሩ የም/ቤቱን ህዝብ ግንኙነት ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia