#Egypt

በዛሬው ዕለት የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር አድርገዋል።

በዚህ የካቢኔ ሹም ሽር ላይ የውሃና መስኖ ሚንስትሩ ሞሐመድ አብድል አቲን (የታላቁ ግዳሴ ግድብን ድርድር የሚመሩ) ከሥልጣን ተነስተው በሌላ ሰው ተተክተዋል።

ሞሐመድ አብድል አቲን የተከቱት ዶ/ር ሐኒ ስዌይላም የተባሉ ሰው ሲሆኑ ታዋቂ የውሃ ሃብት ተመራማሪ ናቸው ተብሏል። በካይሮ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲም እንደሚያስተምሩ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ሲሲ ሌሎች የካቢኔ ሹም ሽሮችንም ያደረጉ ሲሆን አጠቃላይ የ13 ካቢኔ አባላት ሹም ሽር ነው ያደረጉት።

የጤና፣ የቱሪዝም፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ፣ የሲቪል አቪየሽን፣ የትምህርት እና ሌሎች ሚኒስትሮችንም በአዲስ ተተክተዋል ተብሏል።

አል ሲሲ የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የፋይናነስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እንዳልቀየሩም  ተገልጿል።

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባን ያደረገው የሃገሪቱ ፓርላማም በፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ሹም ሽር በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን አል ዓይን የሀገሪቱን ሚዲያዎች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር ያደረጉት የመንግሥታቸውን የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል እና የግብጻዊያንን ጥያቄ ለመመለስ እንደሆነ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia