TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ጎፋ ዞን አፅድቋል !

ዛሬ የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሳውላ ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም የክልል አደረጃጀትን በተመለከተ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ከሌሎች አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጋር አብሮ ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

በአዲስ የክልል አደረጃጀት በጋራ የሚደራጁ 11 መዋቅሮች ፦
- ወላይታ፣
- ጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ጌዴኦ፣
- ኮንሶ፣
- አማሮ፣
- ደቡብ ኦሞ፣
- ኧሌ፣
- ባስኬቶ፣
- ቡርጂ እና ደራሼ መሆናቸው በምክር ቤቱ ተገልጿል።

#የማዕከል_ጉዳይ ሳይንሳዊ፣ ምክንያታዊ በሆነ እንዲሁም ውይይት ተደርጎበት በህዝብ ድምፅ የሚወሰን መሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#AwaQi

ነፃ የስልጠና እና የተለያዩ እድሎችን እንዲሁም አዝናኝ እና አነቃቂ ቪድዮዎችን በየጊዜው ለማግኘት አዋቂን ይቀላቀሉ https://publielectoral.lat/+fM0ANWxp33Y2ZjM8

@awaqiethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
' 2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ '

ኮማንደር አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል ወቅት የተናገረችው ፦

" ዛሬ ያወደስናቸው የትግራይ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ይሩኑ አይኑሩ ፤ ይብሉ አይብሉ ፣ ይታከሙ አይታከሙ የሚለውን የሚያውቁት ነገር የለም።

ስለዚህ እዚህ ጋር ጥሩ ጎናቸውን ተቀብለን እዛ ጋር ያ ጉድለታቸውን መሙላት ስላለብን እነዚህ አትሌቶች የሚፈለግባቸውን ነገር ሁሉ አድርገዋል መንግስት ደግሞ እንደመንግስት ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመነጋገር የተሻለ ነገር አድርጎ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያገኙ ፣ የትግራይ ህዝብም የተሻለ መሰረታዊ ነገር እንደ ስልክ፣ መብራት፣ ባንክ የመሳሰሉትን ነገሮች እንዲያገኝ ቢያደርረግ ደስ ይለናል።

ምክንያቱም እኛ ለእነዚህ አትሌቶች ቅርብ ነው ያለነው። ቅርብ ስትሆን ትሳቀቃለህ ፣ ከአንዱ አንዱን ስታይ ትሳቀቃለህ ሁለተኛውን ፣ ሶስተኛውን ስታይ ትሳቀቃለህ ብዙ ነገር ነው ያለው እዛ በቅርብ ስናይ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው።

እኛም እስከመቼ ነው የምንጨነቅው ከእነዚህ አትሌቶች ጋር ? ስለዚህ እኔስ ብሆን ፣ እናቴስ ብትሆን፣ አባቴስ ቢሆን፣ ወንድሜስ ቢሆን፣ ልጄስ ቢሆን ብለን ማሰብ አለብን የኢትዮጵያ መንግስት ከአፅንኦት ጋር የማሳስበው ይሄን ነገር ያደርጋል ብዬ ገምታለሁ።

እነዚህ አትሌቶች ልዩነታቸውን ጠብቀው ፣በሀገራቸው ጉዳይ ጠንክረው ፣ ጠንክረን ይሄን ውጤት አምጥተናል ያሉንን ልዩነቶች አጥበን መሰረታዊ ነገሮች አሟልተን እዛ ያሉትን አትሌቶች ረድተን እዚህ ያሉትንም አጠንክረን ሞራል ሰጥተን የተሻለ ዓመት 2015ን እንድንቀበል የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትንም የኢትዮጵያ መንግስትንም እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር ይርዳን።

2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ። ህዝብ ተፈናቀለ፣ ሞተ፣ ተሰደደ፣ ተራበ የሚባለው ነገር ጠፍቶ በአትሌቶቻችን ደስ እንዳለን ሁሉ ኢትዮጵያን ደስ የሚላት ነገር እንዲመጣ ከልቤ ፀልያለሁ፤ ከልቤ እመኛለሁ፤ እኛ ከለመነው እግዚአብሔር ያን ያሳካዋል።

ሁላችንም የጥላቻ ልብ ወደጎን አድርገን የይቅር ባይነት ልብ ካቀረብን ይሆናል። ጥላቻን ባቀረብን ቁጥር ሁለመናችን ወደጥላቻ ይሄዳል፤ ጥላቻን ትተን በጎ ባሰብን ቁጥር ሁሉ ነገር በጎ ይሆናል።

የጥላቻ ልብን እንደምንም አሸንፈነው የይቅር ባይነት ልብ፣ የመረጋጋት ልብ፣ የማስተዋል ልብ ፣ ከጭካኔ የራቀ የርህራሬ ልብ እግዚአብሔር እንዲሰጠን የሁል ጊዜ ፀሎቴ ነው።

ህዝቤ የተሻለ ነገር እንዲያገኝ ከልቤ እመኛለሁ "

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦ " ... በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡ ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓ.ም የ20/80 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡…
#መልስ_ያላገኘው_ጥያቄ

የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ባለፈው ሙሉ በሙሉ የተሰረዘው ዕጣ ሳይወጣ የእነሱ ጉዳይ ላይ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳሰቡ።

የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሰናል ብለው እየቆጠቡ ያሉ ወገኖች አለን ስላሏቸው ጥያቄዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማሳወቃችን አይዘነጋም።

" ዛሬም ድረስ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ የሚሰጠን አጥተናል " ያሉት ነዋሪዎቹ " ከልጆቻችን ምግብ ቀንሰን፣ በቤት ክራይ እየተሰቃየንና እየተማረርን ላለፉት 9 ዓመታት ቆጥበን ስለምን በዕጣው ልንካተት እንዳልቻልን በግልፅ ሊነገረን ይገባል " ብለዋል።

የቀጣዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከመውጣቱ በፊትም መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።

የ2005 ዓ/ም 20/80 ለባለ 3 መኝታ ቆጣቢዎቹ ፤ " #ቤቶቹ_የትገቡ ? ፣ #ተስፋ_አድርገን_ነበር#13ኛው_ዙር_ላይ_97_አልቋል_ብላችሁን_አልነበር?! ፤ #ባለ3_መኝታ_ኦዲት_ይደረግ#ፍትህ_እንሻለን! "በሚሉ እና በሌሎች ሀሽታጎች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ በመሰባሰብ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ዘመቻ እያካሄዱ መሆኑን ገልፀዋል።

https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/72439?single
https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/72244?single
https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/72384?single
https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/72271

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፍትህ ሚኒስቴር የምርመራ ሪፖርት ምን ይላል ? የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር በሚያዚያ ወር ላይ በጎንደር ፣ በወራቤና በጂንካ አካባቢ በተከሰተ ግጭት ተፈፅመዋል ያላቸውን ወንጀሎች የምርመራ ግኝት ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ በሚያዚያ 2014 በጎንደር እና በወራቤ ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ እንዲሁም በጂንካና አካባቢው ማንነትን መሰረት አድርጎ ተከስቷል…
" በሪፖርቱ ላይ ቅሬታ አለን " - የጎንደር እስ/ጉ/ም/ቤት

ከሳምንታት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር ፦ በጎንደር ፣ ወራቤ እንዲሁም ጂንካና አካባቢው ላይ ስላካሄደው ምርመራ ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል።

በተለይ የጎንደርን ሪፖርት በተመለከተ የጎንደር እስ/ጉ/ም/ቤት ቅሬታ እንዳለው ለፍትህ ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ም/ቤቱ ሪፖርቱ በጎ ጎኖች የተካተቱበት ቢሆንም በጎንደር ሙስሊም ማህበረሰብ እና በከተማው የእስ/ጉ/ም/ቤት ዘንድ ቅሬታች የፈጠረው ጉዳይ መኖሩንም አመልክቷል።

አሉ ያላቸውን ቅሬታዎችንም ለፍትህ ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ላይ በዝርዝር አስቀምጧል።

ሪፖርቱ የፈጠረው ቅሬታ ምንድነው ? ከላይ በደብደቤ ተያይዟል።

የፍትህ ሚኒስቴር ያቀረበው ሪፖርት ምን ነበር ? 👉 https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/71944?single

@tikvahethiopia
#Monkeypox

ጎረቤታችን ሱዳን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በምዕራብ ዳርፉር የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያለበት ሰው ማግኘቱን አሳውቋል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣው በብሔራዊ የህዝብ ጤና ቤተሙከራ በተካሄደ ምርመራ በአንድ የ 16 ዓመት ተማሪ ላይ ሀሙስ ዕለት መገኘቱ ተገልጿል።

ወረርሽኙ ከአንድ ሰው ውጭ በሌሎች ላይ አለመገኘቱን ሀገሪቱ አሳውቃለች።

ወረርሽኙ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩት 38 ሰዎች ቢሆኑም በሽታው የተገኘው ግን በአንድ ሰው ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

የዳርፉር ግዛትና የሱዳን የጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸዋል።

መረጃውን የሱዳን ዜና አገልግሎት/ አል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#GERD #ETHIOPIA 🇪🇹

🇪🇹 የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ ፦

" ... ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም፤ ይሄ ግድብ ይሰራል።

ይሄን ግድብ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም። "

🇪🇹 የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ ሀኃይለማርያም ደሳለኝ ፦

" ... በወንዞቻችን ለመጠቀም እና ድህነትን ለማስወገድ የምናደርገው ጥረት እራሳችንን እና ጎረቤቶቻችንን ጭምር ለመጥቀም እንጂ ማንንም ለመጉዳት እንዳልሆነ ለዓባይ ልጆች ሁሉ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ "

🇪🇹 የአሁኑ የሀገራችን ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን። የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው "

#ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ💪

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #Update ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ። ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ…
#ችሎት

የቀድሞው የአ/አ ከተማ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ዛሬ ሰኞ ለ2ኛ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ በሀምሌ 11 በነበረ ቀጠሮ ለተጨማሪ ምርመራ በተሰጠው 14 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ውጤት ለችሎቱ አብራርቷል።

ለተጨማሪ ምርመራ ስራ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

https://telegra.ph/Dr-Muluken-Haftu-08-01

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ።

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው።

ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ በዚህም የ2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ በ8 ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል።

🌊 የትላንቱ አደጋ የደረሰው የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናዱ ነው። ቦታው ከዚህ ቀደም በስጋት ቀጠና ከተለዩት አንዱ ነው።

- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች የንብረት ጎዳትና መሠረት ልማቶች ላይ፤ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ፣ የወንዝ ድጋፍ ግንባታ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና ወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia