TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ሃላፊ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ!

የቀድሞው #የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ #አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ። ሳላህ ጎሽ "በስልጣን ዘመናቸው በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው እንዳለበት አሳማኝ መረጃ በማግኘቴ ነው እገዳውን የጣልኩት" ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ሳላህ ጎሽ የሱዳን የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃላፊ በነበሩበት ጊዜ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ የማሰቃያ ድርጊቶች እጃቸው አለበት። የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ ቤተሰቦችም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ክልከላ ተጥሎባቸዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒኦ ሱዳን ውስጥ በሲቪል አስተዳደር ለሚመራ የሽግግር መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ኦማር ሀሰን አል በሺርን ከስልጣን ያወረደው የሱዳን ጦር የሽግግር ምክር ቤት በማቋቋም ሀገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ወታደራዊ ምክር ቤቱ እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ከ10 ቀናት በፊት ለ3 ዓመት የሽግግር ጊዜ የሚጸናውን የጋራ አስተዳደር ለመመስረት እና ለስልጣን ክፍፍል መፈራረማቸው ይታወሳል።

Via ቢቢሲ/ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሱዳን

አብደላ ሃምዶክ #የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በትናንትናው እለት ተሹመዋል። ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን አዲስ የተቋቋመው የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ በመሆን መሾማቸውን ተከትሎ ነው አብደላ ሃምዶክ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢኮኖሚስት በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አብደላ ሀምዶክ ከሚሰሩበት አዲስ አበባ ወደ ካርቱም በማቅናት በትናንትናው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ምንጭ:- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD #FDREDefenseForce ሀገር መከላከያ ሰራዊት፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል ደመሰስኩኝ አለ። የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ ተልዕኮ ውስደው የተንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ የወሰደባቸው ኃይሎች (የተገደሉ) በቁጥር 50 ሲሆኑ ፤ ከ70 በላይ የሚሆኑት…
ሱዳን ምላሽ ሰጠች...

ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።

ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል መደምሰሱን (50 መግደሉን፤ 70 ደግሞ ማቁሰሉን) ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል-ታሂር አቡ ሀጃ "መሰረተ ቢስ ውንጀላ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

አቡ ሃጃ ፥ "ሱዳን እና ሰራዊቷ በአጎራባች ኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቀ አይገቡም" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፤ "ይህ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥሰቶች በመቀጠላቸው ምክንያት የኢትዮጵያ አገዛዝ የገጠመውን ከባድ እውነታ ያንፀባርቃል” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሱዳን ለአማፅያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገችን እንደሆነ ሲገልፅ ነበር።

በትላንትናው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከገለፀው በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ #የሱዳን_እጅ በጣም ረጅም መሆኑን ገልጿል።

የክልሉ ም/ኮሚሽነር "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፤ በካማሺ ዞን ፤ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች በጅምላ በግፍ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጉ፤ ለጥቃቱ ደግሞ "ጉህዴን"ን ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው። ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - #የሱዳን_ተቃውሞ

የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሱ።

ዛሬ በሱዳን መዲና ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በነበሩ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን ኤኤፍፒ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከካርቱም በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

Video Credit : UoKEN

@tikvahethiopia