TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢውም ክፍያ አልተከፈለንም " ያሉ በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራ ካቆሙ ቀናት አልፈዋል። እነዚህ አውቶብሶች በከተማይቱ ያለውን የትራንስፖርት ችግር እንዲያቀሉ ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ከአመት በላይ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ ግን " ከሁለት እና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢ…
#Update

በአዲስ አበባ የ " ሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች " ውል ለተጨማሪ 6 ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ውሉ ከመጋቢት 4/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ወራት እስከ መስከረም 2/2015 ዓ.ም መራዘሙ ነው የተገለፀው።

ቢሮው በሁሉም አውቶቡሶች GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር ስራው የተጠናከረ እና አገልግሎት አሰጣጡ የተሻሻለ እንዲሆን በትኩረት ይከናወናል ተብሏል።

በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደ ስራ ከገቡ በኋላ በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም " ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢውም ክፍያ አልተከፈለንም " ያሉ በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራ አቁመው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር እየተካሄደ ያለው ምንድን ነው ? በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት የሰጡት ቃል ፦ - የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ድብደባው ለቀናት የዘለቀ ነው። እስከ ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሲደበድቡ ነበር። - ነዋሪዎች ግጭቱ…
#ETHIOPIA #SUDAN

አፍሪካ ህብረት (AU) እና ኢጋድ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረው ወታደራዊ ውጥረት እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ሀገራቱ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ወታደራዊ ውጥረት ያሳስበኛል ያለ ሲሆን ሀገራቱ ከወታደራዊ እርምጃ እንዲታቀቡ ጠይቋል፤ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ውይይትን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርቧል።

የድንበር ውዝግቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተከሰቱ ያሉ የውስጥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ዲፐሎማሲያዊ ጥረቶችን ማደናቀፍ እንደሌለበት ህብረቱ አስገንዝቧል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በሀገራቱ መካከል ያለው የድንበር ውዝግብን ምክንያት ያደረገ ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቅርቧል።

ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ውጥረቱን የበለጠ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ኢጋድ በጉዳዩ ዙሪያ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን እንዲከተሉ ጠይቋል።

[ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና በኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የተሰጡት መግለጫዎች ከላይ ተያይዘዋል ]

@tikvahethiopia
#Wollega #Tole

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ድጋፍ ይዞ ወለጋ ቶሌ እና አርጆ ጊዳ መድረሱን ገልጿል።

ማህበሩ ዜጎች በ9400 ላይ OK ብለው በመላክ ሰብዓዊነትን እንዲደግፉ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ) ለቀይ መስቀል ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የባንክ አካውንቶች ፦
👉 ንግድ ባንክ - 907
👉 አዋሽ - 907
👉 COOP - 907
👉 አቢሲንያ - 907 ናቸው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመላው ሀገሪቱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን እየደገፈ ይገኛል።

ማህበሩ በ1947 ከተቋቋመ አንስቶ በሀገራችን እጅግ በርካቶችን አግዟል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

71 ሺ 832 ተማሪዎች የሚፈተኑበት የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ሰኔ 27 ይጀምራል።

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በፈተናው አሰጣጥ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በከተማዋ በ 792 ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ለዚህም 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል ።

አቶ ዳኘው አክለውም አጠቃላይ በከተማዋ 71 ሺህ 832 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ነው የተናገሩት።

ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እስካሁን ያለውን የፈተናው ዝግጅት ሂደት የገመገመ ሲሆን ፈተናው ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ሂደት ላይ ነውም ተብሏል።

ሰኔ 24 ቀንም ለሁሉም ፈተናውን ለሚመለከት የትምህርት ማህበረሰብ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

(አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia #Sudan

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለማጋጨት የሚፈልጉ መንግስታት ወይም #ሌሎች_ወገኖች ቢኖሩም እነዚህ አካላት ከሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ግጭት የሚያተርፉት አይኖርም ሲሉ አስረድተዋል።

#በውጭ_ሀይል_ግፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ውዝግብ ሊኖር እንደማይግባ ገልፀው ራሳችንን ልንቆጣጠር እና ከግጭት ልንቆጠብ ይግባል ብለዋል።

" በመካከላችን የጠላትነት መንፈስ ሊኖር አይግባም ፤ ይልቁንም በልማት ልንተባበር እና አብረን ልናድግ ይገባናል " ሲሉ ገልፀዋል።

ለሱዳን ህዝብ ክብር አለን ያሉት ዶ/ር ዐቢይ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ያጋጠማቸውን ችግር በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፋታህ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ጋር ካርቱም ውስጥ ተወያይተው ነበር ፤ በዚህም ወቅት ቡርሃን " ከኢትዮጶያ ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን " ማለታቸውን ሱና ዘግቧል።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለማርገብ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለአንድ ዓመት ጊዜ ዝግጅት ተደርጎበታል የተባለው የመጀመሪያው የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሰኔ 22 ይካሄዳል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ሰኔ 22 በሚካሄደው መጀመሪያው ዙር የሽልማት መርሐግብር አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ጀምሮ እስከ ዓመት ከስምንት ወር ያሉ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን ለመሸለም የታቀደ መሆኑን ባለቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው ተናግረዋል። ሰኔ…
ፎቶ፦ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2014 የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የመጀመሪያ አዋርድ እየተካሄደ ይገኛል።

በስነስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቹን ጨምሮ የውድድሩ እጩዎች እንዲሁም በርካታ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ስነስርዓቱ የተጀመረው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በማሰብ ሲሆን ቤተሰቦቹን ጨምሮ በአዳራሹ የተገኙ እንግዶች በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ሲያለቅሱ ተስተውሏል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሁሌ በየዓመቱ ሰኔ 22 የሚቀጥል ሲሆን በሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን በኩል የሚዘጋጅ ነው።

(Tikvah Family)

Tikvah Ethiopia AFAAN OROMOO
https://publielectoral.lat/+UTMftkYHBuOGaQ23

@tikvahethiopia