TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
ኤርትራ የምርመራ ሪፖርቱን አልቀበልም አለች።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተመድ የጋራ የምርመራ ቡድን ዛሬ ይፋ ያደረጉትን ሪፖርት ኤርትራ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

ዛሬ ከሰዓት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ኤርትራ በምርመራው ላይ የተሳተፉ አካላትን ገለልተኛነት ጉዳይ ያነሳች ሲሆን ምርመራው አካሄድና ትክክለኛነት እንዲሁም ህጋዊነት ላይ ጥያቄዎችን አንስታለች፡፡

ሪፖርቱ ላይ ኤርትራን የተመለከቱ መረጃዎች ተዛብተው መቅረባቸውን ኤርትራ የገለፀች ሲሆን ምርመራው ከምስክሮች ተዓማኒነት፣ ከተደረገበት ጊዜ እና ከሸፈናቸው ቦታዎች አንጻር ውስንነቶች ያሉበት ነው ብላለች።

የኤርትራን ጦር መዳኘትም ሆነ ለተጎጂዎች ፍትህ መስጠት ከተፈለገ የሚቻለ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሌሎች በኤርትራ ህግ መሰረት ገለልተኛ እና እውነተኛ ምርመራን ለማድረግ በሚችሉ አካላት ነው ብላለች።

ኤርትራ ምንም ዐይነት ማረጋገጫና ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ያለቻቸውን የአክሱም ጭፍጨፋና ሌሎች ጾታዊና በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ጥቃቶችንም አንስታለች።

በእዚህም ጣምራ ሪፖርቱ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃ ፤ ኤርትራ ፈርማ ህግ ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ማክበሯን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። እነዚህን ህጎች በሚጥሱ የሰራዊት አባላት ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂ እንደምታደርግ ኤርትራ ገልፃለች።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#አልዓይን
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
#ETHIOPIA

አሜሪካን ጨምሮ 16 የዓለማችን ሀገራት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተካሄደውን ጥምር ምርመራ ሪፖርት እንደሚቀበሉት በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የጣምራ ሪፖርቱን እንደሚቀበሉ ያሳወቁት፦
• አሜሪካ
• አውስትራሊያ
• ቤልጂየም
• ካናዳ
• ዴንማርክ
• ፊንላንድ
• ፈረንሳይ
• ጀርመን
• አይስላንድ
• አየርላንድ
• ሉግዘንበርግ
• ኔዘርላንድ
• ኒውዝላንድ
• ኖርዌይ
• ስዊድን እና እንግሊዝ ናቸው።

ሀገራቱ በመግለጫቸው ሁለቱ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ዙሪያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ያወጡት ሪፖርት ገለልተኛ እና ተጠያቂነትን ሊያሰፍን የሚችል መሆኑን አስታውቀዋል።

በሪፖርቱ መሰረት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁሉም አካላት መሳተፋቸው በመረጋገጡ ሁሉም ተሳታፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ሀገራቱ አሳስበዋል።

በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት በሪፖርቱ ግኝቶች መሰረት ወደ መፍትሄ እንዲመጡም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል 16ቱ አገራት የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነቱ ለተጎዱ አካላት እያደረገ ያለው ድጋፍ፣ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በተጠረጠሩ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምርመራ መጀመሩ ና እያደረጋቸው ላለው ሌሎች ጥረቶች እውቅና እንሰጣለን ብለዋል።

መንግስት የጀመረውን ጥረት እንዲቀጥልበት የጠየቁ ሲሆን በተለይ ለተጎጂዎች ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ፣ በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱና ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም ብሄራዊ ውይይት እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ሰላሟና መረጋጋቷ እንድትመለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉና የግዛት አንድነቷን እንደሚያከብሩም አሳውቀዋል።

https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-07

#አልዓይን

@tikvahethiopia
" ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነትም፣ ንግግርም፣ ድርድርም አንፈልግም "- አቶ ሙሳ አደም

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ንግግርና ድርድር ማድረግ እንደማይፈልግ አስታወቀ።

የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ሙሳ አደም ለአል ዐይን በሰጡት ቃል፤ አሁን ላይ በሕዝብ ላይ ትንኮሳና ጥቃት እያደረሰ ካለው የህወሃት ቡድን ጋር እንደ ፓርቲ መነጋገርም ሆነ መደራደር እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

አቶ ሙሳ ህወሃት ትናንትና ከሰዓት በኋላ በሰሜን አፋር በኩል አዲስ ጥቃት መክፈቱን ተናግረዋል።

ህወሓት በመጀመሪያ በአፋር ክልል በራህሌ ጥቃት ሰንዝሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

አቶ ሙሳ፥ ህወሃት የአብአላ ከተማን ለመቆጣጠር 3 እና 4 ጊዜ ሙከራ ማድረጉን ገልጸው በአካባቢው ያለው የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት ይህንን ጥቃት እየመከተ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከስር መሰረቱ የተቋቋመው ህወሃት በሕዝብ ላይ ሲፈጽመው የነበረውን የረጅም ዘመናት ግፍና መከራን ለመታገል ነው ያሉት አቶ ሙሳ ፓርቲያቸው ከሕወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኑነትም፣ ንግግርም፣ድርድርም እንደማይፈልግ ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ፤ እንደፓርቲ ከህወሃት ጋር ድሮም ምንም ንግግር አልነበረንም ያሉ ሲሆን፤ ወደፊትም ንግግር ሊኖር አይችልም ሲሉ ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ፥ “ህወሃት የአፋርን ሕዝብ ብዙ መከራ አብልቷል” ያሉ ሲሆን የፓርቲውን አመራሮች አሸባሪ ብሎ ፈርጆ እንደነበር አስታውሰዋል።

እንደፓርቲ ከህወሃት ጋር መነጋገር እንደማይፈልጉ የተናገሩት አቶ ሙሳ እንደሀገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጋግሮ ችግሮቹን በጠረንጴዛ ዙሪያ መፍታት ከቻለ “እኛም እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም የምናገኝበት አጋጣሚ ሊኖር ስለሚችል የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወስነውን አብረን የምንወስን ይሆናል” ብለዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#MinistryFinance

በሀገሪቱ 🇪🇹 ኢኮኖሚ ላይ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እና ዜጎች ለማቋቋም የሚውል አዲስ በጀት ሊያጸድቅ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ በጠ/ሚ ጽ/ቤት በተዘጋጀው " የአዲስ ወግ " መርሃ ግብር ላይ መስሪያ ቤታቸው በጦርነት ምክንያት የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለማካካስ ብሎም መልሶ ለመገንባት ተጨማሪ በጀት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

የሚያስፈልገው ገንዘብን በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ተሰርቶ ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን አስታውቋል።

አቶ አህመድ ሽዴ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም የገለፁ ሲሆን ከጸደቀ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ መናገራቸድን አል ዓይን ድረገፅ አስነብቧል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#Sudan

በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል።

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው።

ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው።

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት ኮሚቴ፤ ከህላፋያና ሶባ ድልድዮች ውጪ በ3 አቅጣጫዎች ወደ ከተማይቱ የሚያስገቡ ድልድዮችን ከትናንት ምሽት ጀምሮ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ተቋማት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ያሳሰበው ኮሚቴው፤ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በመብት ቢሆንም፤ አመጽ እና ሁከት መቀስቀስን ግን እንደማይታገስ አስታውቋል።

በካርቱም የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን በመከተል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡንም አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፥ ካናዳ ሞንትሪያ በሚገኘው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩትን አቶ ጌታቸው መንግስቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

አቶ መንግስቱ ንጉሴን ደግሞ የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸው መንግስቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ረዘም ላለ ጊዜ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛውን በመተካት ነው።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን አሁን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪውን ዳታ ሴንተሩን አስመልክቶ ለሚዲያዎች ገለፃ ያደርጋል። በስፍራው የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገለፃውን ተከታትለው ዝርዝር መረጃው ይልኩላችኃል። @tikvahethiopia
#Update

ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መግለጫ ፦

• ከፊታችን ሚያዝያ 1ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀምራል። ከሚጀመሩ አገልግሎቶች መካከል ፦
- የጽሁፍ አገልግሎት፣
- የዳታ፣
- የድምጽ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ የቴሎኮም አገልግሎቶች ናቸው።

• ከሰኔ በኋላ ሁሉንም የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀመራል።

• አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ ደሴ ኮምቦልቻ ፣ ሀረር ፣ ድሬዳዋና ጅግጅጋ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸው።

• በ07 መነሻ ኮድ አገልግሎት ይሰጣል።

• የኢትዮ ቴሌኮምን የቴሌኮሙንኬሽን መሰረተ ልማቶች ለመጠቀም ድርድሮች እየተደረጉ ነው።

• በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ውስጥ 2 ተጨማሪ የመረጃ ማዕከላት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች ይገነባል።

• በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ውስጥ ለግማሹ ህዝብ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እቅድ አለው። በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ 98% ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን አገልግሎት የመስጠት እቅድ ተይዟል።

#አልዓይን

ፎቶ ፦ ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት

@tikvahethiopia
#Russia

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዙ፡፡

ፑቲን ከገቡበት የዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንዲሆን ያዘዙት፡፡

ዛሬ ከከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል የሆኑ ሃገራት ጠንከር ያለ መግለጫ እያወጡ መሆኑን እና ማዕቀቦችን እየጣሉ በመሆኑ ጸረ ኑክሌር ኃይሉ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዋል፡፡

ትዕዛዙ ለሃገሪቱ ጦር አመራሮች የተሰጠ ነው፡፡

ይህ ሁኔታውን የበለጠ እንዳያባብሰውና ወዳልተፈለገ አስከፊ #የኑክሌር_ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡

የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎችንም እርምጃዎችን በሚወስዱ እና ጣልቃ በሚገቡ ሃገራት ላይ ጠንከር ያለ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲያስጠነቅቁ ነበር።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው ! ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል። የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል። ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ…
#Update

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ትምህርት ቤት ወንዝ ውስጥ የገባው ማርኮን ይገረም አለመገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ ።

ኮሚሽኑ ለአል ዐይን ኒውስ አማርኛ በሰጠው ቃል ፤ የኮሚሽኑ ሰራተኞች አሁንም ፍለጋ ላይ ናቸው።

ህጻኑ ከጠፋ አምስት ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን አለመገኘቱ ተገልጿል። በጎርፍ የተወሰደውን ማርኮን ይገረም አካል ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል ተብሏል።

ህጻኑ ረቡዕ ዕለት ወንዝ ውስጥ የገባው።

ዘንድሮ ትምህርትን " ሀ " ብሎ ሊጀምር በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት የገባው የ4 ዓመቱ ማርኮን ይገረም ባለፈው ረቡዕ ከት/ ቤት ሲወጣ ከት/ ቤቱ አጥር ውጭ ያለው ትቦ ውስጥ በመግባቱ በትቦ ውስጥ የነበረው የጎርፍ ውሃ ይዞት ሄዷል።

በትምህርት ቤቱ አካባቢ ካሉ ወንዞች ጀምሮ የአፍንጮ በር በቀበና በአቃቂ በአባ ሳሙኤልም ባሉ ወንዞች ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ፍለጋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

#አልዓይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" አሁንም 10 ሰዎች ታግተዋል ፤ አጋቾቹ ብር ይፈልጋሉ " - አቶ ውብሸት አበራ

ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ከታገቱ ዜጎች መካከል እስካሁን 360ዎቹ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ስራ መለቀቃቸውን የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ገለፁ።

አጋቾቹ በራሳቸው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት መልቀቃቸውን ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

አሁንም 10 ሰዎች መታገታቸውን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አጋቾቹ ብር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ትናንት በስፍራው ከታገቱት ዜጎች ውስጥ ሁለት የደራ ባለሀብቶች እንዳሉበት ተገልጿል። ዋና አስተዳዳሪው የታጋቾችን ብዛት እና ማንነት በተመለከተ መረጃው የተገኘው አምልጠው እና ተለቀው ከመጡ ሰዎች መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዲስ አበባ ፍቼ ደራ መስመር የፌዴራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራ ተጠይቋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መስመር ላለፉት ስምንት ወራት ተዘግቶ መቆየቱን አስታውሰዋል። የመኪና መንገዱ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም ትናንት ሰዎች ግን መታገታቸውን ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ በአካባቢው እንዲሰማራ ጠይቀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው የፌዴራል ሰራዊት እንዲሰማራ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሰላም ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ምላሽ እንዳላገኙ ገልፀዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU2022Summit ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ መሆኑን ገለፁ። ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " አሁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሻሻልበት እና አፍሪካም በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ…
#UNGA  

አሜሪካ የተመድ የፀጥታ ም/ቤት ሁሉን አካታች እንዲሆን ለማድረግ #ሪፎርም እንዲደረግበት ጥሪ አቀረበች።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ፦
- #የአፍሪካ
- ላቲን አሜሪካ
- ካሪቢያን ሀገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ለዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት የተሻለ ብቃት እንዲኖረውና ሁሉንም አካታች እንዲሆን ለማድረግ ሪፎርም እንዲደረግበትም ባይደን ጥሪ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ አሁን ላይ 5 ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ በድምሩ 15 መቀመጫዎቸ ያሉት ሲሆን ይህ የመቀመጫ ቁጥር እንዲጨምር ጠይቀዋል።

በአፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካና ካሪቢያን ውስጥ የሚገኙ ሀገራት በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲያገኙ የጠየቁት ባይደን አሜሪካ ይህንን አቋም ለረጅም ጊዜ ስትደግፍ ቆይታለች ብለዋል።

በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ያላቸው ሀገራት በእነሱ ላይ ወይም በአጋሮቻቸው ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመሻር መብት አላቸው።

ባይደን አሜሪካን ጨምሮ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ያላቸው ሀገራት ምክር ቤቱ ተዓማኒነት ያለውና ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ከአቅም በላይ ከሆኑ ያልተለመዱ ሁኔታዎች ውጪ ድምጽን በድምጽ መሻር መብታቸውን ከመጠቀም እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

አፍሪካ በፀጥታው ም/ ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ለማስቻል የተለያዩ ዘመቻዎች ሲካሄዱ እንደነበር ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከዚህ ቀደም ይህንን የአፍሪካ ሀገራት በተመድ የጸጥታው ጥበቃ ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ማግኘት አለባት የሚለውን ሃሳብ መቀላቀላቸውን ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል። 10ኛው የ " ጣና ፎረም " ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ፦ - የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን…
#TanaForum

በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።

ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር።

በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ ዌበር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የተመድ የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር ሀና ቴተህ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ነበር።

በወቅቱም ኬኒያዊው የህግና ፖለቲካ ተንታኙ ፕ/ር ፓትሪክ ሉሙምባን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካዊያን ምሁራን ለሐመር ጥያቄ አቅርበዋል።

ምሁራኑ ለአምባሳደር ሐመር ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? የሚል ሲሆን አሜሪካ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው፤ ቻይና ለአፍሪካ ከአሜሪካ በተሻለ መንገድ እየሰራች ነው የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ፦

" አፍሪካ በራሷ ችግሯን መፍታት ትችላለች ?  እንደዛ ማድረግ የምትችል አይመስለኝም።

እኔ ባህርዳር የተገኘሁት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለመንገር አይደለም። አፍሪካም ሆነች አሜሪካ ችግራቸውን ለመፍታት በጋራ መስራት ግን አለባቸው።

በአፍሪካ እንደ አሜሪካ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረገ ሀገር ወይም ተቋም የለም፣ የአፍሪካዊያንን ህይወት በመታደግ ከአሜሪካ በላይ የሰራ ሀገር የለም፣ ፍጹም ላንሆን እንችላለን።

አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ሀላፊነት ታውቃለች ነገር ግን በብዙ መንገድ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን። " ሲሉ መልሰዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#Amaharic #Russia

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በሞስኮ የሚገኙ ት/ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀምራሉ ተባለ።

በዚህም የአማርኛ ቋንቋ አንዱ ሆኖ ይሰጣል።

የሞስኮ ትምህርትና ሳይንስ ክፍልን ዋቢ በማድረግ ስፑትኒክ እንደዘገበው ፤ ሩሲያ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ #አማርኛ እና #ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ት/ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ባሳወቀችው መሰረት ትምህርቱ መሰጠት ይጀምራል።

እንደ ዘገባው ከሆነ " 1517 " የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል።

" 1522 " የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።

ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።

ሩሲያ በቀጣይ በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።

በመቀጥልም #ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።

ሌላኛዋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር ከዚህ ቀደም መግለጿ ይታወቃል።

አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣል ተብሏል።

መረጃው የ #አልዓይን (ስፑትኒክ) ነው።

ስፑትኒክ አፍሪካ ፦ https://www.facebook.com/100091796831512/posts/pfbid02Zf2NYdkBuBFDA8UDxBbtf5ZBGbRVPjYGUWzgeLVL365qBrKQgthGS622GJqo2PNul/?app=fbl

@tikvahethiopia