TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHO_SUDAN

ኢትዮጵያ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን ገለፀች።


ጎረቤት ሃገር ሱዳን በኢትዮጵያ ጦር 7 ወታደሮቿ እና 1 ሲቪል እንደተገደለባት ክስ አሰምታለች። ግድያው በዚህ ወር አጋማሽ የተፈፀመ ነው ብላለች።

በዚህም ለተመድ ፀጥታ ም/ቤትና ለሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋም ክስ አቅርባለሁ ብላለች።

በተጨማሪ ቁጣዋን ለመግለፅ በአዲስ አበባ የሚገኙትን መልዕክተኛዋን ወደ  ካርቱም ጠርታለች፣ በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደርም ጠርታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ብላለች።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ ግጭት የተከሰተው በህወሓት ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች መሆኑን ገልጿል።

በሱዳን ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው በዚህ ግጭት በጠፋው ህይወት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያዝን ገልጾ ምርመራ እንደሚደረግም አመልክቷል።

ክስተቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን በማመልከት፣ የሱዳን መንግሥትም ሁኔታውን የበለጠ ከሚያባብስ እርምጃ እንደሚቆጠብ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሱዳኖቹ በአማራ ክልል ምእራብ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ “ገላል ውሀ” የተባለ አካባቢን በከባድ መሳሪያ ሲደበድቡ ውለዋል።

ጥቃቱ ካለፈው ሰኔ 15 ጀምሮ አልፎ አልፎ የነበረ ሲሆን ታጣቂዎቹ ተመትተው ከአካባቢው ከተባረሩ በኋላ እንደገና ዛሬ ከጠዋቱ ከ2 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የከፋ ጉዳት ባይደርስም ጥቃት መሰንዘራቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ ዶቼቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሮይተርስ፣ ዴቼቨለ እና ቢቢሲ ናቸው።

@tikvahethiopia