TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SUDAN

"...ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ በዘንድሮው ክረምት የደረሰብኝ የጎርፍ አደጋ የለም" - ሱዳን

የሱዳን የመስኖ እና ውሃ ሃብት ሚኒስትር ያሲር አባስ (ፕ/ር) ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ዘንድሮ ያጋጠማት የጎርፍ አደጋ እንደሌለ አስታወቁ፡፡

ፕ/ር ያሲር አባስ ኢትዮጵያ ግድብ እየገነባች ካለችበት የዓባይ ውሃ ይልቅ ዘንድሮ ነጭ ዓባይ ሱዳንን ለጎርፍ አደጋ አጋልጧታል ብለዋል፡፡

ይህ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት ታይቶ አይታወቅም ነው አባስ ያሉት፡፡

ክረምት በመጣ ጊዜ በቀን ወደ ሱዳን ይገባ የነበረው ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር መጠን ያለው የነጭ ዓባይ ውሃ ዘንድሮ በቀን ከ120-130 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

ሆኖም በተያዘው ክረምት ሊያጋጥም ይችል የነበረውን የጎርፍ አደጋ በሮዜሪዬስ እና ሜሮዔ ግድቦች የተያዘውን ውሃ በአግባቡ በመልቀቅ ለመቆጣጠር መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡን 2ኛ ዙር ሙሌት በተናጠል ከማከናወኗ ውጭ ክረምቱን ተከትሎ በሱዳን ካጋጠሙ የጎርፍ አደጋዎች ጋር የተያያዘ ተጽዕኖ እንደሌለው ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ከሙሌቱ በፊት መረጃን በወጉ ለመለዋወጥ አለመቻሉ ለቅድመ መከላከል ተግባራት ከፍተኛ ወጪ፣ ለተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ተጽዕኖዎች ዳርጎናልም ነው ፕ/ር ያሲር አባስ ያሉት፡፡

አባስ አል ፋው እና አል-ራሃድ በተሰኙ ከተሞች በእርሻ መሬቶች ጭምር የደረሰውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ የቀረቡ ሪፖርቶችን ገምግመናል፤ ተወያይተናልም ብለዋል፡፡

ሱዳን ከሙሌቱ በፊት የመረጃ ልውውጥ አልነበረም ትበል እንጂ ኢትዮጵያ ግን ሙሌቱን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎችን ልኬያለሁ ስትል ከአሁን ቀደም ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡

የመረጃ ባለቤት ፡ #አል_አይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው !

የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል።

ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡

ጉብኝቱ ሱዳን ፤ "ምርኮኛ ወታደሮቼ በኢትዮጵያ ጦር ተገደሉብኝ " ማለቷን ተከትሎ የተካሄደ ነው፡፡ " የአጸፋ ምላሽንማ ሳንሰጥ አንቀርም " ስትልም ዝታ ነበር።

ጄነራል አልቡርሃን ፤ በጉብኝታቸው ጦሩ የሃገሩን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ ስለመሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ለሃገራቸው ሲሉ መስዋዕትነትን የሚከፍሉ የጦሩ አባላት ደም "በከንቱ ፈስሶ" አይቀርም ሲሉም ዝተዋል። ሁኔታው ተጨባጭ መልስ እንደሚያገኝ ቃል በመግባት ከሰሞኑ በአል ዑስራ ያጋጠመው ፈጽሞ አይደገምም ብለዋል፡፡

በሱዳን መሬቶች ላይ ሚደረግ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሲሉም ትዕዛዝን አስተላልፈዋል፡፡

አል ፋሽቃ፤ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሱበት ሰፊና ለም መሬት ሲሆን ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ መሆኗን ተከትሎ ወደ አካባቢው ዘልቆ የገባው የሱዳን ጦር መሬቱን ይዞ ለቅቄ አልወጣም ብሏል።

ከዚህ አልፋ ሀገሪቱ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ጥረት እያደረገች መሆኑን #አል_አይን_ኒውስ ዘግቧል።

ከሰሞኑን ፤ ሱዳን ሞቱብኝ ያለቻቸው ወታደሮች ፤ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው የገቡና (ጠብ አጫሪዎች እራሳቸው ናቸው) ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር ግጭት የፈጠሩ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ሲሆኑ ኢትዮጵያም በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን መግለጿ ይታወቃል።

@tikvahethiopia