TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ ላይ ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠየቀ። የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊ ሚሼል ባችሌት " በቶሌ መንደር የተፈጸመው የጭካኔ ግድያ እና የነዋሪዎች በጥቃቱ ምክንያት ተገድዶ መፈናቀል ዘግንኖኛል " ብለዋል። ቅዳሜ ዕለት ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት እማኝን ባልደረባቸው እንዳነጋገሩ…
#Update

ከሰሞኑን ጥቃት የተፈፀመበት የምዕራብ ኦሮሚያ ጊምቢ ወረዳ ሁኔታ ምን ይመስላል ? የህብረተሰቡስ ጥያቄ ምንድነው ?

(ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ቲክቫህ አባላት)

- አባሴና ወደ ተባለበት አካባቢ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ ይሰማል።

- በሰኔ 11ዱ ጥቃት የተጎዱ ሪፈር እየተደረጉ ነው።

- እስካሁን (ዛሬ ጥዋት ድረስ) በህይወት ለተረፉ ወገኖች በበቂ ደረጃ አስፈላጊ እርዳታ አልደረሰም።

- በመጠለያ ያሉ ወገኖች ወደ አርጆ ጉደቱ ውስዱን ቢሉም መከላከያ እኛ እያለን ምንም አይፈጠርም ብሏል፤ አሁን የጥቃት ስጋት ባይኖርም መከላከያው ከወጣ ታጣቂዎች ተመልሰው መጥተው ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ህብረተሰቡ መከላከያ በመኖሩ ከስጋት ነፃ ቢሆንም መከላከያው አረጋግቻለሁ ብሎ ከወጣ ሌላ ጥቃት ሊፈፀም ይችላል የሚል ስጋት አለው።

- ማህበረሰቡ ወደበፊት ቦታ ለመመለስ ሌላ ጥቃት እንደማይደርስብን ምን ዋስትና አለን ? በተጨማሪ በባለፈው ሰኔ 11 ጥቃት ያየነው ነገር እንድንመልስ የሚያደርግ አይደለም ብሏል። ገበሬውም ለምንድነው ገብተን የምናርሰው ተመልሰው መጥተው ጥቃት ያደርሱብናል የሚል ስጋት አለው።

- የተጠያቂነትን ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ አካባቢውን ከሚያስተዳድሩት አንዳቸውም በክልል፣ በዞን ፣ በወረዳ፣ ደረጃ መጠየቃቸውን አልሰማንም። የዞን እና የወረዳ አካላት የፀጥታ ችግር እንዳለ ያውቃሉ ፣ ማህበረሰቡም እየፈራ ነበር ወደ ፌደራል ወደላይ አካል ሪፖርት የሚያደርግ አልነበረም። አይደለም ሊጠየቁ ስምምነት ያላቸው ነው የሚመስለን ፤ ለስም መንግስት የሾማቸው ነገር ግን ተገዢነታቸው ለታጣቂዎቹ ነው የሚመስለው።

- ፍትህ ሚወርደው ከታች እስከላይ ያሉ ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አካላት ሲጠየቁ ብቻ ነው። ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ቡድን የሚረዳ አካል አለ ፤ እነሱን መጠየቅ ሳይቻል እንዴት ፍትህ ይሰፍናል ?

- አሁንም ፤ ከነነፍሳቸው #ወደጫካ ይዘዋቸው የሄዱ ህፃናት፣ ወጣቶች ብዙ አሉ። እነዛ እስካሁን በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የሚታወቅ ነገር የለም። አንዳንዶቹ መከላከያ ወደጫካው እየገባ እየተታኮሰ ሲሄድ ሬሳቸው ተገኝቷል።

- አሁን ድረስ ሰፈር ውስጥ ያልተገኙ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እንትና የታለ እየተባለ ሲጠየቅ የሌለው ብዙነው። አስክሬናቸው ያልተገኘ በህይወትም በአካባቢው የሌሉ ፤ ወደጫካ ተተወሰዱ ናቸው።

- ታጣቂዎቹ ከመንግስት የፀጥታ ኃይል በላይ ሆነው አይደለም ፤ ነገር ግን የሚረዳቸው የሚደግፋቸው አካል አለ፤ ይሄ ሁሉ አመት እንዲህ ስቃይ የበዛው ከጀርባ የሚደግፋቸው በመኖሩ ነው። በተለይ ደግሞ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል አንዳችም የሚያደርገው ነገር የለም ፤ መከላከያው ሲመጣ ነው ሁኔታዎች የሚቀየሩት።

- ማህበረሰቡ መጀመሪያም ታጣቂዎች በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ አሳውቆ ነበር። ከቶሌ እስከ ጉተን መስመር ድረስ እየመጡ እየተዝናኑ ወደጫካ ይመለሱ ነበር ፤ አንድ አሸባሪ የተባለ የታጠቀ ኃይል ንፁሃን ያሉበት አልያም አስተዳድራለሁ የምትለው ግዛት ውስጥ ገብቶ እንደፈለገ ሆኖ ሲወጣ እርምጃ ካልወሰድክ ትርጉሙ ሌላ ነው።

- ታጣቂዎች ጥቃት እየፈፀሙ ያሉት በጥላቻ ፣ ባለፈ ታሪክ ተነስቶ በብቀላ መንፈስ ነው፤ እንጂ አንድም የስልጣን ሆነ የፖለቲካ ግብ ያላቸው አይመስልም። ስልጣን ይዞ ለማስተዳደር ከሆነ የሚያስተዳድሩትን ማህበረሰብ አይገድሉም።

- አሁን የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ የተለያዩ ቁጥር መውጣቱ በጫካ የተገደሉትን ፣ አስክሬናቸውን ያልተገኘ በመኖሩ ነው እስካሁን ግን የሰፈሩ ሰው ወደ 600 አካባቢ መቅበሩን ገልጿል። ገና ግን ያልተገኙ አሉ።

- መንግስት በሽብርተኛ ድርጅትነት የፈረጀው " ሸኔ " ያለምንም ድብብቆሽ በግልፅ ነበር ሲኖር የነበረው። ዬሳዲምቱ ላይ እራሱ ካምፕ ነበራቸው በግልፅ ነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ክልሉ ይህ ሁሉ ሲሆን አያውቅም ማለት አይቻልም። የቀበሌ ሊቀመንበር በታጣቂዎች ተይዞ እየተገረፈ ፤ ያሉበትም ሚንቀሳቀሱበትም እያታወቀ መፍትሄ አለመሰጠቱ ድጋፍ እንዳለው ማሳያ ነው።

- አሁን ላይ የተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት ለአብነት እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት አይነት መንግስት ላይ ጫና ካላሳደሩ መፍትሄ ይመጣል ብለን አንጠበቅም ፤ እንዲሁ የሰዎች ሞት እንደተለመደ ያልፋል።

* (ሰኔ 11 ቀን 2014 በምዕራብ ወለጋ በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ንፁሃን አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መገደላቸው ይታወሳል። መንግስት ለግድያው ተጠያቂ ሽብርተኛ ድርጅት ያለውን " ሸኔ " (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) ሲል የታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ ጭራሽ በአካባቢው አልነበርኩም ፤ ጥቃቱን የመንግስት ኃይሎች ናቸው የፈፀሙት ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ ላይ የመንግስት ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ መጠየቁ አይዘነጋም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

እንደ FIAS 777 አይነት ሌሎች ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ስላሉ ገንዘባችሁን እንዳትበሉ አደራ እንላለን።

በተለይ አሁን ያሉብንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ተገን በማድረግ በርካታ ወጣቶችን የሚያጭበረብሩ፤ ትንሽ ሰዎች እየከበሩ ሌሎች ብዙሃኑ ባዷቸውን የሚቀሩበት የማታለል ስራዎች በስፋት እየተስተዋለ ነው።

በትንሽ ብር ብዙ ታተርፋላችሁ፣ ዘመናዊ ስራ ነው፣ ከኢኮኖሚ ችግራችሁ በቶሎ ትላቀቃላችሁ እያሉ ወጣቶች ንብረታቸውን ሽጠው፣ ከሰው ተበድረው ገንዘብ ከከፈሉ በኃላ የውሃ ሽታ እየሆነባቸው ነው።

አንድ የቤተሰባችን አባል ልክ FIAS 777 እንደሚባለው አይነት HDUHDU በሚባል ተመሳሳይ ድርጅት እስከ 70,000 የተበሉ የሚያውቃቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸውን ጠቁሞ እነዚህም አካላት ዛሬ ደብዛቸውን ማጥፋታቸውን ገልጿል።

አንድ ሌላ የቤተሰባችን አባል በዚህ HDUHDU በሚባለው እስከ 93000 ብር ድረስ የተበሉ ብዙ ጓደኞች እንዳሉት ገልጾ በርካታ ወጣቶች ብዙ ለማግኘት ሲሉ ያላቸውን ገንዘብ እና ጊዜያቸውን እያጡነውና ይጠንቀቁ ብሏል።

ሌሎች ከላይ ከተገለፁት ባለፈ ስም እየቀያየሩ በርካቶችን ገንዘብ የሚቀበሉ በሂደቱ ትንሽ ሰው አትርፎ ብዙሃኑ ያለውን የሚያጣበትን ስርዓት የዘረጉ ስላሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዋነኛዋቹ ሰዎች ውጭ ናቸው እየተባለ የሚነገር ሲሆን ገንዘብ የሚሰበሰበው እዚህ ኢትዮጵያ ባሉ ኤጀንቶች ነው።

ሁሌም ወደ ሆነ እንቅስቃሴ ሲገባ ህጋዊ እና ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ ማጣራት ያስፈልጋል ፤ አሁን አሁን እየመጡ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶች የሰዎችን ገንዘብ በመብላት ባለፈ ወዳጆችን እርስ በእርስ እንዲኮራረፉም እያደረገ ነው ፤ ህጋዊ መንገድ ብቻ እንከተል እንላለን።

(ማስረጃዎቻችሁን ለሚመለከታቸው አካላት ለማድረስ እና ምላሽ ካለ ለማሳወቅ እንጥራለን)

@tikvahethiopia
#እገታ

ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ የነበሩ 4 የሕዝብ ማመላለሻና 1 የጭነት ተሸከርካሪዎች መታገታቸው ተሰምቷል።

ተሳፋሪዎቹ ከደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ መታገታቸው የተገለፀ ሲሆን እገታው የተፈፀመው በሂደቡአቦቴ ወረዳ ወዘሚ በሚባል መንደር ነው።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ 4 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና 1 የጭነት መኪና መታገታቸውን አረጋግጠዋል።

የመንግስት የጸጥታ ኃይል ወደስፍራው መሄዱን ያነሱት አቶ ውብሸት እስካሁን 230 ሰዎች ከእገታው መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ምን ይህል ሰዎች እንደተሳፈሩ ከጉንዶ መስቀል መረጃ እየሰበሰቡ እንደሆነ ያነሱት ገልፀው፤ የተለቀቁ ቢኖሩም አሁንም የታገቱ እንዳሉ ማወቃቸውን ተናግረዋል።

እገታው የተፈጸመው መንግስት ሸኔ እራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን እንደሆነም ነው የገለፁት። ተሸከርካሪቹ የታገቱበት አካባቢ በብዛት ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት ነው ብለዋል።

አሁን በእገታ ላይ ያሉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል።

የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የታገቱት ሰዎች ጨለንቆ እንደተወሰዱ ገልጸው በስፍራው መንግስት " ሸኔ " እራሱን ደግሞ " የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ብሎ የሚጠራው ቡድን #ማሰልጠኛ እንዳለው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙና በአካባቢው ”ሽፍታ ይንቀሳቀስ ይሆናል” እንጅ ሌላ ችግር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለ8 ወራት ያህል ተዘግቶ የነበረ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቅርቡ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#WorldBank #Ethiopia

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ600 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት መፈራረሙን አገለፀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፥ ከ600 ሚሊየን ዶላሩ ውስጥ 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ ሲሆን 400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ መሆኑን ገልጿል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ያለውን የስርአተ ምግብ ለማሻሻል እና የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ተራኪ

የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ - ሙሉ የመጽሐፍ ትረካ 🎧

17 ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪኮች ከራሱ ከልብ ጠጋኙ ዶክተር ፈቀደ አግዋር በማስታወሻነት ቀርቦላቿል። ሙሉ የመጽሐፉን ትረካ፤ ተራኪ ላይ ያድምጡ!

ተራኪ - መተግበሪያን ከጉግል ፕሌስቶር እና አፕ ስቶር ላይ ያውርዱ!
⬇️Google Play | ጉግል ፕሌስቶር - bit.ly/3CTALq3
⬇️App Store | አፕ ስቶር - https://apple.co/3AVp0i3
Telegram - https://publielectoral.lat/terakiapp
☎️ አብረውን መስራት ለሚፈለጉ ደራሲያን በ +251920958300 | +251911637874
ፎቶ / ቪድዮ ፦ በኦሮሚያ ክልል ፤ ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ፤ ቶሌ ቀበሌ ላይ ባለፈው ሰኔ 11 /2014 የተፈፀመውን የንፁሃን ግድያ በማውገዝ ሰልፍ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፀጥታ ኃይሎች እንደበተኗቸው ለማወቅ ተችሏል።

ተማሪዎቹ " ሞት ይብቃን፣ አትግደሉን...ያልሞትነው ተራችን ገና ስለሆነ ነው ፣ ዛፉ ከሰው ልጅ ያንሳል እንጂ አይበልጥም ፣ አባይን የምንገድበው ለሰው ፣ ለድሃ እንጂ ለዛፍ ማጠጫ አይደለም እና ሌሎች መስል መልዕክቶችን እያሰሙ ከዩኒቨርሲቲው ተነስተው ወደ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት አቅጣጫ እየተጓዙ ነበር።

የፀጥታ ኃይሎች በሰልፈኞች ላይ የማባረር እና የመደብደብ ድርጊት መፈፀማቸውን በተሰራጩ ቪድዮዎች ለማየት ተችላሏል።

ከዩኒቨርሲቲው አልያም ከፌዴራል ፖሊስ የሚገኝ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።

ፎቶ/ ቪድዮ ፦ BTY (Tikvah Family) & ሶሻል ሚዲያ

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል። ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ…
#Update

በህይወት ያለን ሰው ያቃጠሉት ግለሰቦች ምን ተደረጉ ?

• ካቃጠሉት ውስጥ እስካሁን አራት የሚደርሱ አልተያዙም።

• ወንጀሉን ከፈፀሙት ውስጥ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከድተው ጠፍተዋል፤ 2 የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ለህግ እንዲሰጡ ለክልሉ ፖሊስ አመራሮች ተጠይቋል።

• 3 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው (ሁለት የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት አንድ ሲቪል) ።

የፍትህ ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት በማድረግ ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራው ነው ብሏል።

በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ፥ ውሳኔ ባገኙ ጉዳዮችና በምርመራ ላይ ስላሉ ጉዳዮች ለሚዲያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰውን ልጅ ከእነ ነፍሱ ሲያቃጥሉ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል እስካሁን ድረስ ያልተያዙ መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል።

የሰውን ልጅ ሲያቃጥሉ ከነበሩት መካከል የፀጥታ ኃይሎች እንደነበሩ የሚታወስ ነው ፤ ከነዚህ ውስጥ በወንጀሉ የተሳተፉ 3 ሰዎች (2 የደቡብ ልዩ ኃይል አባላት እና 1 ሲቪል) በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማንነታቸው ቢለይም ወንጀሉን ከፈፀሙ በኃላ ከሰራዊቱ ከድተው በመጥፋታቸው እነሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌዴራል ፖሊስ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ፤ ሁለት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በወንጀሉ ላይ ስለመሳተፋቸው በግልፅ በምስል ማስረጃ ተረጋግጦ ማንነታቸው ተለይቶ ለህግ አካላት እንዲሰጡ የክልሉ የፖሊስ አመራሮች ተጠይቀዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ - https://telegra.ph/ETH-06-24-2

@tikvahethiopia
" ህግ ይከበር ፤ ፍትህ ይሰጠን "

ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ #ህግን_ባልተከተለ መልኩ ቤታችን ፈረሰብን ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

ያሉበት ቦታ ለማስፋፊያ ስራ ይፈለጋል የተባሉ ዜጎች ለማስፋፊያ አንደሚፈለግ ያወቁት ሰኔ 29/2013 ዓ/ም አንደሆነ ከዛ በፊት ስለጉዳዩ ምንም እንደማያቁ / እንዳልተነገራቸው ፤ ጉዳዩን የሚያውቁት ከወረዳው ጀምሮ እስከ መሬት ማናጅመት ድረስ ያሉ አካላቶች እንደነበሩ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ህግን ሳይከተል መኖሪያቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ክረምት ወቅት ዝናብ እየወረደባቸው ውጭ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ያንብቡ ⬇️
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-25
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ_አበባ_፤_ኮሪያ_ሆስፒታል_አካባቢ_ያሉ_ቤቶች_ማስረጃ.pdf
ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ " ህግን ባልተከተለ መልኩ ፤ ፍርድ ቤት ለእኛ ፈርዶልን ቤታችን ፈረሰብን " ያሉ ወገኖች ፍትህ ይሰጠን በማለት ሲጠይቁ።

የ80 ዓመት እድሜ ያለቸው አዛውንት ፦

" ... ለማን አቤት ይባላል ? ለማን አቤት ልበል ? 60 ዓመት የኖርኩበትን ቦታዬን ፣ ቤቴን መንግስት ፈርዶልኝ ፣ አርብ ተፈርዶልኝ ሰኞ ውሳኔ ልቀበል ቅዳሜ ለሊት መጥተው ቤቴን አፈረሱብኝ፣ ንብረቴን አወደሙብኝ።

ልጆቼም ተበተኑ ፣ ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀብኝ ነው። ለማን አቤት ይባላል ? የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድልኝ ፣ ዘመዶቼ ምን ልሁን ? እንዴት እንደምሆን እስኪ ፍረዱኝ፤ የምሆነው ነገር ግራ ገብቶኛል፤ ብቻዬን ነኝ "

🔻

ሌላ እናት የአካባቢው ነዋሪ ፦

" ... በደካሞች ላይ ቤት አፍርሶ ለሌላ መስጠት ለባለሃብት መስጠት ማለት ይከብዳል ያማል።

ለሌላ ትንኮላም አልሄድን ዓመት ሙሉ ስንሟገት አርብ ተወሰነልን ተብሎ ደስታችንን ሳንጨርስ የስራ ሰዓት አዘናግተው በእረፍት ሰዓት መጥተው ቁጭ ባልንበት ነው ያፈረሱብን። ዋና ዋና እቃዎችን እንኳን ማውጣት አልቻልንም ነበር።

... እኔ ልጄን ልያዝ እቃ ልጎትት ? እነሱም ደካማ ናቸው። አባታችንም እራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም ። ጎረቤት ባይደርስልን የተሻለ የምንለውን እቃ ማውጣት አንችልም ነበር።

መንግስትን በጣም ነበር የምንደግፈው ለውጥ አየን ብለን ግን አሁን ላይ በሰው የምናየው ስናዝን የነበረው ነገር በራሳችን ላይ ስለተፈፀመ እግዚአብሔር ፍትህ ይስጠን።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ለፍትህ ነው የምቆመው ብሏል ፍትህ ይስጠን ፤ ልጅ ይዘን ነው እየኖርን ያለነው። "

@tikvahethiopia