TIKVAH-ETHIOPIA
#UN የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ ላይ ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠየቀ። የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊ ሚሼል ባችሌት " በቶሌ መንደር የተፈጸመው የጭካኔ ግድያ እና የነዋሪዎች በጥቃቱ ምክንያት ተገድዶ መፈናቀል ዘግንኖኛል " ብለዋል። ቅዳሜ ዕለት ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት እማኝን ባልደረባቸው እንዳነጋገሩ…
#Update

ከሰሞኑን ጥቃት የተፈፀመበት የምዕራብ ኦሮሚያ ጊምቢ ወረዳ ሁኔታ ምን ይመስላል ? የህብረተሰቡስ ጥያቄ ምንድነው ?

(ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ቲክቫህ አባላት)

- አባሴና ወደ ተባለበት አካባቢ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ ይሰማል።

- በሰኔ 11ዱ ጥቃት የተጎዱ ሪፈር እየተደረጉ ነው።

- እስካሁን (ዛሬ ጥዋት ድረስ) በህይወት ለተረፉ ወገኖች በበቂ ደረጃ አስፈላጊ እርዳታ አልደረሰም።

- በመጠለያ ያሉ ወገኖች ወደ አርጆ ጉደቱ ውስዱን ቢሉም መከላከያ እኛ እያለን ምንም አይፈጠርም ብሏል፤ አሁን የጥቃት ስጋት ባይኖርም መከላከያው ከወጣ ታጣቂዎች ተመልሰው መጥተው ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ህብረተሰቡ መከላከያ በመኖሩ ከስጋት ነፃ ቢሆንም መከላከያው አረጋግቻለሁ ብሎ ከወጣ ሌላ ጥቃት ሊፈፀም ይችላል የሚል ስጋት አለው።

- ማህበረሰቡ ወደበፊት ቦታ ለመመለስ ሌላ ጥቃት እንደማይደርስብን ምን ዋስትና አለን ? በተጨማሪ በባለፈው ሰኔ 11 ጥቃት ያየነው ነገር እንድንመልስ የሚያደርግ አይደለም ብሏል። ገበሬውም ለምንድነው ገብተን የምናርሰው ተመልሰው መጥተው ጥቃት ያደርሱብናል የሚል ስጋት አለው።

- የተጠያቂነትን ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ አካባቢውን ከሚያስተዳድሩት አንዳቸውም በክልል፣ በዞን ፣ በወረዳ፣ ደረጃ መጠየቃቸውን አልሰማንም። የዞን እና የወረዳ አካላት የፀጥታ ችግር እንዳለ ያውቃሉ ፣ ማህበረሰቡም እየፈራ ነበር ወደ ፌደራል ወደላይ አካል ሪፖርት የሚያደርግ አልነበረም። አይደለም ሊጠየቁ ስምምነት ያላቸው ነው የሚመስለን ፤ ለስም መንግስት የሾማቸው ነገር ግን ተገዢነታቸው ለታጣቂዎቹ ነው የሚመስለው።

- ፍትህ ሚወርደው ከታች እስከላይ ያሉ ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አካላት ሲጠየቁ ብቻ ነው። ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ቡድን የሚረዳ አካል አለ ፤ እነሱን መጠየቅ ሳይቻል እንዴት ፍትህ ይሰፍናል ?

- አሁንም ፤ ከነነፍሳቸው #ወደጫካ ይዘዋቸው የሄዱ ህፃናት፣ ወጣቶች ብዙ አሉ። እነዛ እስካሁን በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የሚታወቅ ነገር የለም። አንዳንዶቹ መከላከያ ወደጫካው እየገባ እየተታኮሰ ሲሄድ ሬሳቸው ተገኝቷል።

- አሁን ድረስ ሰፈር ውስጥ ያልተገኙ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እንትና የታለ እየተባለ ሲጠየቅ የሌለው ብዙነው። አስክሬናቸው ያልተገኘ በህይወትም በአካባቢው የሌሉ ፤ ወደጫካ ተተወሰዱ ናቸው።

- ታጣቂዎቹ ከመንግስት የፀጥታ ኃይል በላይ ሆነው አይደለም ፤ ነገር ግን የሚረዳቸው የሚደግፋቸው አካል አለ፤ ይሄ ሁሉ አመት እንዲህ ስቃይ የበዛው ከጀርባ የሚደግፋቸው በመኖሩ ነው። በተለይ ደግሞ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል አንዳችም የሚያደርገው ነገር የለም ፤ መከላከያው ሲመጣ ነው ሁኔታዎች የሚቀየሩት።

- ማህበረሰቡ መጀመሪያም ታጣቂዎች በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ አሳውቆ ነበር። ከቶሌ እስከ ጉተን መስመር ድረስ እየመጡ እየተዝናኑ ወደጫካ ይመለሱ ነበር ፤ አንድ አሸባሪ የተባለ የታጠቀ ኃይል ንፁሃን ያሉበት አልያም አስተዳድራለሁ የምትለው ግዛት ውስጥ ገብቶ እንደፈለገ ሆኖ ሲወጣ እርምጃ ካልወሰድክ ትርጉሙ ሌላ ነው።

- ታጣቂዎች ጥቃት እየፈፀሙ ያሉት በጥላቻ ፣ ባለፈ ታሪክ ተነስቶ በብቀላ መንፈስ ነው፤ እንጂ አንድም የስልጣን ሆነ የፖለቲካ ግብ ያላቸው አይመስልም። ስልጣን ይዞ ለማስተዳደር ከሆነ የሚያስተዳድሩትን ማህበረሰብ አይገድሉም።

- አሁን የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ የተለያዩ ቁጥር መውጣቱ በጫካ የተገደሉትን ፣ አስክሬናቸውን ያልተገኘ በመኖሩ ነው እስካሁን ግን የሰፈሩ ሰው ወደ 600 አካባቢ መቅበሩን ገልጿል። ገና ግን ያልተገኙ አሉ።

- መንግስት በሽብርተኛ ድርጅትነት የፈረጀው " ሸኔ " ያለምንም ድብብቆሽ በግልፅ ነበር ሲኖር የነበረው። ዬሳዲምቱ ላይ እራሱ ካምፕ ነበራቸው በግልፅ ነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ክልሉ ይህ ሁሉ ሲሆን አያውቅም ማለት አይቻልም። የቀበሌ ሊቀመንበር በታጣቂዎች ተይዞ እየተገረፈ ፤ ያሉበትም ሚንቀሳቀሱበትም እያታወቀ መፍትሄ አለመሰጠቱ ድጋፍ እንዳለው ማሳያ ነው።

- አሁን ላይ የተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት ለአብነት እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት አይነት መንግስት ላይ ጫና ካላሳደሩ መፍትሄ ይመጣል ብለን አንጠበቅም ፤ እንዲሁ የሰዎች ሞት እንደተለመደ ያልፋል።

* (ሰኔ 11 ቀን 2014 በምዕራብ ወለጋ በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ንፁሃን አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መገደላቸው ይታወሳል። መንግስት ለግድያው ተጠያቂ ሽብርተኛ ድርጅት ያለውን " ሸኔ " (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) ሲል የታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ ጭራሽ በአካባቢው አልነበርኩም ፤ ጥቃቱን የመንግስት ኃይሎች ናቸው የፈፀሙት ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ ላይ የመንግስት ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ መጠየቁ አይዘነጋም)

@tikvahethiopia