TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገታ

ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ የነበሩ 4 የሕዝብ ማመላለሻና 1 የጭነት ተሸከርካሪዎች መታገታቸው ተሰምቷል።

ተሳፋሪዎቹ ከደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ መታገታቸው የተገለፀ ሲሆን እገታው የተፈፀመው በሂደቡአቦቴ ወረዳ ወዘሚ በሚባል መንደር ነው።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ 4 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና 1 የጭነት መኪና መታገታቸውን አረጋግጠዋል።

የመንግስት የጸጥታ ኃይል ወደስፍራው መሄዱን ያነሱት አቶ ውብሸት እስካሁን 230 ሰዎች ከእገታው መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ምን ይህል ሰዎች እንደተሳፈሩ ከጉንዶ መስቀል መረጃ እየሰበሰቡ እንደሆነ ያነሱት ገልፀው፤ የተለቀቁ ቢኖሩም አሁንም የታገቱ እንዳሉ ማወቃቸውን ተናግረዋል።

እገታው የተፈጸመው መንግስት ሸኔ እራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን እንደሆነም ነው የገለፁት። ተሸከርካሪቹ የታገቱበት አካባቢ በብዛት ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት ነው ብለዋል።

አሁን በእገታ ላይ ያሉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል።

የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የታገቱት ሰዎች ጨለንቆ እንደተወሰዱ ገልጸው በስፍራው መንግስት " ሸኔ " እራሱን ደግሞ " የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ብሎ የሚጠራው ቡድን #ማሰልጠኛ እንዳለው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙና በአካባቢው ”ሽፍታ ይንቀሳቀስ ይሆናል” እንጅ ሌላ ችግር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለ8 ወራት ያህል ተዘግቶ የነበረ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቅርቡ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia