TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥረው በቀረቡ ግለሰቦች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን #ፎቶ_በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ፍርድ ቤቱ በድብቅ በመግባት ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሲያሰራጩ ነበር ተብለው #የተጠረጠሩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው በአሁን ወቅት ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን፥ በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፍጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ምስክርነት በመስጠት በፍርድ ቤት ቅድመ መርመራ ላይ እያሉ ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ #በማሰራጨት ስጋት ለመፍጠርና እንዲሸሹ ለማደረረግ መሞከራቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስም በአሁኑ ወቅት የምስክሮችን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር በቂ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተመለከተው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ጎንደር የታገቱ ሰዎች #መለቀቃቸውን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጅዓለም በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ታጋቾቹ መለቀቃቸውን አረጋግጠዋል። ኃላፊው «የታገቱ ሰዎች ነበሩ ሙሉ በሙሉ ተለቅቀዋል» ሲሉ አረጋግጠዋል።
ከጎንደር ወደ ገንዳውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞች በምዕራብ ጎንደር ዞን መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ የታገቱት ባለፈው የካቲት 12 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. ነበር። የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰዉ «በአጠቃላይ የታገቱ ሰዎች ከሰባት እስከ ስምንት ሊሆኑ ይችላሉ» ብለው ነበር። የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጅዓለም በዛሬው መግለጫቸው አጋቾቹን #በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር‼️

የ14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ #አዳነች_አቤቤ በሰጡት መግለጫ የህዝብን ሀብት በመበዝበር እና የታክስ ማጭበርበር በመፈፀም የተለዩ 135 ድርጅቶች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በታክስ ስወራው ከተጠረጠሩት 105 ግለሰቦች መካከል 64 የሚሆኑት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሯ በመግለጫቸው 9 ቢሊየን ብሩ 100 ቀናቱ የተለዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ቀሪው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጥርና የካቲት ወር የተለየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ በዋነኝነት ተሳታፊ ሆነው የተገኙት አከፋፋዮች እና አስመጪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 30 በመቶዎቹ ብቻ ቸርቻሪ መሆናቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ በታክስ #ስወራና #ማጭበርበር የተለየውን 14 ቢሊየን ብር ድርጅቶቹ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሚኒስትሯ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ሶዶ ውሎ‼️

በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ የተባሉ ቤቶች #መፍረሳቸውን ተከትሎ በከተማይቱ ዛሬ ግርግር እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተማይቱ #የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርም የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል።

አቶ ዳንኤል ዓለሙ የተባሉ የከተማይቱ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በከተማይቱ #ግርግር የተቀሰቀሰው ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ ነበር። የግርግሩ መነሻም በተለምዶ “የጨረቃ ቤቶች” ተብለው የሚጠሩ በከተማይቱ ዙሪያ ከተገነቡ መኖሪያ ቤቶች መፍረስ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ገልጸዋል። “በጣም ግርግር ነበር። የተወሰነ ጥይት ተኩሰዋል። ሰው ሩጫ ላይ ነበር” ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የከተማይቱ ነዋሪም ከቀኑ ስድስት በኋላ ጥይት ይሰማ እንደነበር አረጋግጠዋል። የቤቶችን መፍረስ በመቃወም መንገድ ዘግተው የነበሩ ሰዎችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንም የዓይን እማኙ ገልጸዋል። ግርግሩን የፈሩ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ተዘግተው መዋላቸውን የሚናገሩት እኚሁ ነዋሪ ወደ 10 ሰዓት ገደማ ግን ከተማይቱ “ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሳለች” ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ህገወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች እየፈረሱ የሚገኙት ቀድሞ የገጠር ቀበሌዎች የነበሩ ነገር ግን ከአንድ ዓመት ወዲህ በከተማይቱ ክልል ስር በተካተቱ ሶስት አካባቢዎች እንደሆነ ነዋሪዎች ለDW አስረድተዋል። ላሬና፣ ኦፎሳሬ እና ቆንቶ በተባሉት በእነዚህ ቦታዎች የእየፈረሱ ያሉት ቤቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መንግስቱ ቶራ ዛሬ በከተማይቱ የተፈጠረው ግርግር “የህገ ወጥ ግንባታን ለመከላከል እየተደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል። “ሰባት ሰዓት አካባቢ ጎማ በመቃጠሉ ሰዉ አመጽ ሊቀሰቀስ ነው በሚል ሰግቶ፣ ፈርቶ ነበር። ግን ምንም ነገር የለም። ተረጋግቷል” ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

የከተማይቱ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ካለፈው ከትላንት ጀምሮ የሶዶ ከተማ አስተዳደር እና በዙሪያ ያለው ወረዳ ህገወጥ ግንባታ የመከላከል እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቋል። በህገወጥ ግንባታ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች “ስራውን ለማስተጓጎልና የከተማውን ጸጥታ ለማወክ” መሞከራቸውንም ጠቁሟል። “መንገድ በመዝጋት፣ ደን የማቃጠል ሙከራ በማድረግ እና ሌሎች ችግሮችን ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” ያላቸው ግለሰቦችም “#በቁጥጥር ስር ውለዋል” ብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 #ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ #በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ህገወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው ትናንት ለሊት #በቡራዩ_ከተማ ነው፡፡ የጦር መሳሪያው በአይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ ተጭኖ #ከጋምቤላ ወደ #አማራ_ክልል ሊጓጓዙ የነበረ ነው ተብሏል፡፡ የተያዘው የጦር መሳሪያ 42 ታጣፊና 63 ባለሰደፍ በድምሩ 105 ክላሽንኮቮች፣ 95 #የክላሽንኮቭ_መጋዝኖች እና 5 ጥይት ነው፡፡ ከአይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት #ተሽከርካሪው ፊት በመሄድ ሁኔታዎችን #ሲያመቻች የነበረ አንድ ዶልፊን ሚኒባስም ተይዟል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 28 ክላሽንኮቭ፣ 459 ሽጉጦች እና በመቶ ሺህዎች የሚቁጠሩ የአሜሪካ ዶላር #በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል #ከሁለት_ክልሎች በረቀቀ መንገድ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ መሃል ከተማ የገባ 25 ታጣፊ እና 3 ባለ ሰደፍ በድምሩ 28 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳትም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በተመሳሳይ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቴል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ በኮሮላ የቤት ተሽከርካሪ ውስጥ 459 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና 2 የዝሆን ጥረስ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የካቲት 29 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤቴል ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ከ700 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
(ትኩረት‼️)

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየተዘረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ በጫኝና አውራጆች መካከል በተነሳ ግጭት የተጀመረው አለመረጋጋት ወደተለያዩ አካባቢዎች #መስፋፋቱን ነው ነዋሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አስተያዬታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹እረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ከብቶቻችንም እየተነዱ እየተወሰዱ ነው፡፡ ትናንት ገበያ መውጣት አልቻልንም፤ ዛሬም #በዓሉን ለማክበር ተቸግረን ፍርሃት ውስጥ ነን›› ብለዋል፡፡

ማምቡክ መንደር 49 አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ገበያ ነበር፤ ገና ከመቆሙ በጠዋቱ ተበትኗል፡፡ በጫካው ውስጥ ተኩስና ቀስት ማስወንጨፍ አለ፡፡ ከዳንጉር አካባቢ ነው የግጭቱ መሠረት ያለው፤ መንግሥት በፍጥነት ሊደርስልን ይገባል፡፡ ሰዎች በየጫካው እየሞቱ ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በበኩሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር አንጻራዊ #መረጋጋት ላይ መሆኑን ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በአሽከርካሪ እና ጫኝና አውራጅ ሥራ በተሠማሩ ወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ላይ ችግሩን የፈጠሩ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን እና ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት #እንዳይጠፋ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት መነኩሴ፦

በምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የእነጋትራ ሐና ገዳም አስተዳዳሪ መነኩሴ ከስድስት ክላሽንኮቭና ከአንድ ሽጉጥ ጋር #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

መነኩሴው ከስድስት ክላሽንኮቭና ከአንድ ሽጉጥ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ግጭት መፍጠራቸውን ተከትሎ መሆኑን የወረዳው አስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ይሄነው አበባው ለኢዜአ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋሉት አባ ገብረ ስላሴ ሳሙኤል የተባሉ ተጠርጣሪ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በምትገኘው ጥንታዊቷ የእነጋትራ ሐና ገዳምን ከ28 ዓመታት በላይ አስተዳድረዋል።

ተጠርጣሪው መነኩሴ ከሃይማኖታዊ አገልግሎትና የገዳም መሬት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለረጂም ጊዜ የቆየ አለመግባባት ነበራቸው። ህብረተሰቡም በአስተዳዳሪው ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታ ለሚመለከተው አካል ሲያቀርብ መቆየቱን አቶ ይሄነው አስታውሰዋል።

በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ግን አባ ገብረ ስላሴ ጭቅጭቅ በሚነሳበት መሬት ላይ እርሻ ማረስ ሲጀምሩ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ግጭት መቀስቀሱን ነው የተናገሩት።

በግጭቱም አስር ክፍሎች ያሉት ቤት መቃጠሉን፣ በገዳሙ አስተዳዳሪ ግብረ አበሮቻቸው በተተኮሰ ጥይት በአንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድብረ ማርቆስ👆

#በደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ተማሪ ሞት ምክንያት የሆነውን ድርጊት የከተማው ነዋሪዎች እና የክልሉ መንግስት አወገዙ።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች #ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለጸጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎች #በቁጥጥር _ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ የተገለፀው።

ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንዳይደርስባቸው ከጎናቸዉ እንደሚሆኑ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እሁድ ግንቦት 18/2011 ዓ.ም የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፋ ሶስት ተማሪዎች ቆስለዉ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። የችግሩ መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀም ነው ማብራሪያ የተሰጠው።

የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ከማዘን ባሻገር ድርጊቱን አጥብቀው እንደሚያወግዙት ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብም ነው ያስታወቀው። ለሟች ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብም መጽናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ በፀጥታ ችግር ቀያቸውን #ትተው የሄዱ ሰዎችን #ንብረት የፀጥታ አካላት ሲዘርፉ #በቁጥጥር_ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BGU-07-10
TIKVAH-ETHIOPIA
ቅሬታ ! የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች የስም ዝርዝር ይፋ ባለመደረጉ ቅሬታ እንዳላቸው ገለፁ። የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ዓርብ ቢወጣም እስካሁን የቤት ዕጣ የደረሳቸው ሰዎች ስም ዝርዝር በይፋ አልተገለፀም። ይህም የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆን ለማወቅ እየተጠባበቁ ባሉ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት…
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦

" ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል።

በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር #በቁጥጥር_ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል። "

@tikvahethiopia
#WKU

" አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል።

ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው።

ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል።

በየጊዜው እንዲህ ያለ ነገርም እንሰማለን ነው ያሉት።

ከጠቆሙት አንዱ ጉዳይ በመምህሯ የተደፈረችን ተማሪ የሚመለከት ነው።

በተማሪዎች ስለሚነሳው ጉዳይ ተቋሙ ምን ይላል ? በማለት ጥያቄ አቅርበናል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው አመራር የመምህሩ ጉዳይ #ከ2_ወራት_በፊት መከሰቱን እና ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ በቅርብ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን ገልጸዋል።

" ወንጀሉን ከ2 ወራት በፊት እንደፈጸሙ የተጠረጠሩት መምህር በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ ?

በወቅቱ አንድ የሂሳብ መምህር በክፍል ውስጥ ሆነው ከተማሪዎቻቸው አሳይንመንት በመቀበል ላይ ነበሩ። የአንደኛዋን ተማሪያቸውን ወረቀት ግን ሳይቀበሉ ነበር የወጡት።

ይሁንና " #አልቀበልሽም " የተባለችው ተማሪም ምን አድርጌ / ምንስ አጥፍቼ ነው ? ብላ በምትጨነቅበት ሰአት ከክፍሉ ተጠሪ ያገኙትን ስልክ ተጠቅመው የደወሉላት መምህር  " አሳይመንትሽን ቤቴ መጥተሽ ማስረከብ ትችያለሽ " ይሏታል።

ተማሪዋም በተሰጣት አድራሻ ተመርታ ወደተባለችው ቦታ ትሄዳለች። የጠበቃት ግን አሳይመንቱን መቀበል ሳይሆን ሌላ ነበር።

ተማሪዋ እያነባች ጓደኛዋን ይዛ ወደሆስፒታል ካመራች በኃላ በሆስፒታል ህክምና አግኝታለች።

የሆስፒታል ማስረጃዋን ይዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሂዳ አመልክታቸለች።

በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዋ አቤቱታና በቀረበዉ የህክምና ማስረጃ  መሰረት ጉዳዩን ወደ #ዲስፕሊን በመዉሰድ በፍጥነት መምህሩን ከስራ ሊያግድ ችሏል።

መምህሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ #ራሱን_ደብቆ እና ስልኩን አጥፍቶ ቆይቷል ተብሏል።

የዩኒቨርስቲው አስተዳደር #የስራ_እግድ ማሳለፉንም ተከትሎ ከተደበቀበት በመዉጣት ሲመለስ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው በመረከብ ይዞ መምህሩን ሲያፈላልግ የነበረው ፖሊስ #በቁጥጥር_ስር ሊያውለው ችሏል።

አሁን ላይ የምርመራ ሂደቱ አልቆ ፍርዱን እየተጠባበቀ ሲሆን ወደፊት የፍርድ ሂደቱ የሚገለጽ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከሰሞኑ በዚሁ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት ተማሪና አንድ መምህር መጉዳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል👉 https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/88025

@tikvahethiopia