TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን እንየተስተዋለ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህን አስመልክቶም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎችም የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

በተለይም ፦ አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው (ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።

ሊደረጉ የሚገባቸው የጥንቃቄ ተግባራት ፦

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፣

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፣

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፣

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፣

5. አመጋገብዎን ማስተካከል (ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፣

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፣

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፣

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፣

9. የተለያየ ህመም ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ያድርጉ ፡ የታዘዘሎትን መድሃኒትም በትዕዛዙ መሰረት ይውሰዱ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ፤ ከሙቀቱ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ የጤና ችግሮችና ድንገተኛ ህልፈት ነዋሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#CBE

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ከደንበኞች የማይንቀሳቀስ ሂሳብ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ስለመውሰዱ የሚያስረዳ ማስረጃ የተገኘበት ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የባንኩ ሰራተኞችም በዚሁ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

➡️ 1ኛ ተከሳሽ አቶ እስጢፋኖስ ሙሉጌታ ገቢሳ (የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን)

➡️ 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አስኩዋል ወልደአብዝጊ ߹

➡️ 3ኛ ተከሳሽ በቀለ ሽፌ

➡️ 4ኛ ተከሳሽ ይልቃል አዳነ ናቸው የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ የመሰረተባቸው።

አንደኛ ተከሳሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ " ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ " ተቀዳሚ ባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን የሥራ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በባንኩ ደንበኛ ከሆኑ ግለሰቦች ሳይንቀሳቀስ በመቆየታቸው ምክንያት የማይንቀሳቀሱ ሂሳብ (Inactive) የነበሩ የቁጠባ ሂሳቦች ሃላፊነቱን በመጠቀም ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Active) በመቀየር ደንበኞች ከሂሳባቸው ጋር ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያስተሳሰሩትን ስልክ ቁጥር ሲስተም ላይ የተቀየረውን በማፅደቅ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ በተለያዩ ጊዚያት በራሱ ሥም በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች በአጠቃላይ ብር 2,535,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺ) ብር በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ ወስዷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Ministry-Of-Justice-05-19

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጠበቃ አቶ ሸጋው አለበል ምን አሉ ? (ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃል) ፦

" ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች የመኪና መንገድ ዘግተው ከከበቧቸው በኋላ በርከት ብለው አስገድደው ተሽከርካሪ ውስጥ እንዳስገቧቸው ነግረውኛል።

ተሽከርካሪ ውስጥ ግባ አልገባም በሚል ኃይል እንደተጠቀሙና መጠነኛ ቢሆንም የእጅ ነገር እንዳረፈባቸውም ነግረውኛል።

ከተያዙበት እለት ጀምሮም ለሁለት ቀናት ምድር ቤት በጨለማ ውስጥ ብቻቸውን እንዳደሩ እና ይህ ትክክል እንዳልሆነ ፤ ቀጥሎ በተሽከርካሪ ወደ ቢሾፍቱ ተወስደው ከዚያም በሄሊኮፕተር ወደ ባህርዳር መወሰዳቸውንና ለእሳቸው ተብሎ ሄሊኮፕተር ተመድቦ መወሰዳቸው የመንግሥትን ሀብት ማባከን መሆኑን እንደሚያምኑ ገልፀውልኛል።

ባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ማንኛውም እስረኛ በሚጠየቅበት ሁኔታ መብታቸውን እንዲገለገሉ ተደርገዋል።

ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ወንጀል እንዳልፈፀሙ ነግረውኛል፤ የመናገር ነፃነታቸውን ተጠቅመው ሚዲያ ላይ በዋለ ጉዳይ እንዲሁም ቅሬታ ያላቸው አካላት አስረውኝ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው አስረድተውኛል።

ከተያዙ ጀምሮ ቃል አልሰጡም፤ የተጠረጠሩበት አልተነገራቸውም፤ ፍርድ ቤትም አልቀረቡ። እነዚህ ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸው በመጣሳቸው ቅሬታ እንዳላቸው ገልፀውልኛል።

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ በማረሚያ ቤት ውስጥ በተረጋጋ ሁኔታ ይገኛሉ። የዋስትና ጥያቄ አቅርበናል የዋስትና ጉዳያቸው ቀጠሮ ነገ ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ/ም ነው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ለመጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል። በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ተከሳሹ ብሩክ በላይነህ፤ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል። ማክሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት የቀረበው ተከሳሹ፤ "የሚፈልጋቸው ምስክሮቹ በአካባቢው…
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ ለውሳኔ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ተቀጥሯል።

ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ራሱን ሲከላከል ቆይቷል።

ፍርድ ቤት የቀረቡ ምስክሮች "ሟች እና ተከሳሾች ጓደኛሞች እንደነበሩ እንደሚያውቁና ከዚያ ውጪ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ" ገልጸዋል።

በሕግ ጥላ ስር ሚገኘው ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ላይ የፍርድ ማቅለያ እና ማክበጃ መቅረቡን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ለ @tikvahuniversity ተናግረዋል።

ተከሳሹ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።

ፍርድ ቤቱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ተለወጫ ቀጠሮ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ሰጥቷል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

More : @tikvahuniversity
#SEMU

የስሙ ኦዲዮ ቡክስ እና ፖድካስት መተግበሪያን ከጎግልና አፕል ማከማቻ በማውረድ በደንበኝነት ምዝገባ (Subscription) ወይም በአንድ ጊዜ ክፍያ (à la carte) ከመቶ በላይ ድምፀ-መጻሕፍት እና ፖድካስቶችንም ያግኙ።

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገጽቻችንን ይከታተሉ እና የቴሌግራም ቻነላችን @SemuAudiobook ቤተሰብ ይሁኑ።

መተረክ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎን ከ5 ደቂቃ ያነሰ ናሙናዎን በቴሌግራም +251 911 926725 ላይ ይላኩልን።

ጉግል ማከማቻ ፡ https://bit.ly/SemuGooglePlay
አፕል ማከማቻ፡https://apple.co/3gzblVH
ድረ-ገፅ፡ https://www.semuaudiobooks.com/
(ቁጥራዊ መረጃ)

ከIDMC የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ፦

➡️ በ2021 በመላው ዓለም 59.1 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል ፤ ይህ ቁጥር በታሪክ ከፍተኛው ነው። ከ59.1 ሚሊዮኑ መካከል 53.2 ሚሊዮን በግጭት እና ሁከት ፤ 5.9 ሚሊዮን በተፈጥሯ አደጋዎች የተፈናቀሉ ናቸው።

#ኢትዮጵያ

➡️ በ2021 በኢትዮጵያ ግጭት እና ሁከት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይህ ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ3 እጥፍ ይበልጣል።

➡️ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የተፈናቃዮች ቁጥር በአንድ አገር ውስጥ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ሁሉ የሚበልጥ ሲሆን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአመቱ የአገሪቱን ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል ከፍተኛውን ቦታ ይዟል። በሌሎች ክልሎች የተከሰቱ የርስ በርስ ግጭቶችም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

በIDMC ሪፖርት መሠረት ፦

⮕ በትግራይ ክልል 1.8 ሚሊዮን፣
⮕ በአማራ ክልል 1.7 ሚሊዮን፣
⮕ በኦሮሚያ ክልል 643 ሺ ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል።

➡️ በ2021 መጨረሻ በመላው ኢትዮጵያ 3.6 ሚሊዮን ዜጎች ሕይወታቸውን በተፈናቃይነት ለመግፋት ተገደዋል፤ ከእነዚህ መካከል 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት የትምህርት ዕድል የሌላለቸው ናቸው።

➡️ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች በሚገኙ አገራት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ14 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።

➡️ በተፈናቃዮች ቁጥር ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ያሉት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ቡርኪና ፋሶ ናቸው (ከሰሀራ በታች)።

ሙሉ ሪፖርት : https://www.internal-displacement.org/global-report/grid2022/

@tikvahethiopia
የሚሊዮኖች የሳቅ ምንጭ የነበረው ኮሜዲየን ወንደሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሜዲ ዘርፍ ከታዩ እጅግ ተወዳጅ እና ምርጥ ኮሜዲያኖች እንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ ( #ዶክሌ ) በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየቱ ተሰምቷል።

ኮሜዲያኑ ላለፉት ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ሀገር አድርጎ የነበረ ሲሆን ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የኮሜዲያን ወንደሰን (ዶክሌ) አጫጭር የኮሜዲ ስራዎች እጅግ በርካታ ሲሆኑ በተለያዩ ረጃጅም ፊልሞች ላይም በትወና ሰርቷል ፤ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በዚሁ ሞያ ውስጥ ቆይቷል።

ኮሜዲያኑ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትኩረት📣

በሲዳማ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም የፀጥታ ችግር እና ግጭት ማገርሸቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከበንሳ ጠቁመዋል።

የዳዬ አጠቃላይ ሆስፒታል የቲክቫህ አባላት በሲዳማ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በአካባቢዎች ላይ ባገረሸው ግጭት #የሰዎች_ህይወት_ማለፉን እና ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።

ችግሩ ይፈታ ዘንድና አሁን ካለው ሁኔታ ይበልጥ እንዳይከፋ እንዲሁም አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ በሚመለከተው አካል ሁሉ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አስገዝበዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ ነዋሪዎችም ፤ የሚታየው ነገር በአካባቢው ላይ ያለን መልካም ግንኙነት በእጅጉ የሚያደፈርስ በመሆኑ ከሁለቱም ክልል የሚመለከተው አካል የህዝቡን ደህንነት እንዲያስጠብቅና ግጭቱን እንዲቆም መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትም ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የራሱን ድርሻ እንዲጫወት ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

ፎቶ ፦ ከዳዬ አጠቃላይ ሆስፒታል ቲክቫህ አባላት

#ትኩረት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አብዱልዋሀብ መሐድ ከአሶሳ ማረሚያ ቤት አመለጠ። የቤንሻጉል ሕዝቦች ነጻ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) የቀድሞ ሠራዊት መሪ አብዱልዋሀብ መሐድ ታሥሮ ከነበረበት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት ማምለጡን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንደነገሩት አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነበበ። የ9 ዓመት ዕሥር የተፈረደበት አብዱልዋሀብ ያመለጠው ታኅሣሥ 18/2014 መሆኑ ተገልጿል። ግለሰቡ ከዚህ በፊትም እንዲሁ…
" ተጠርጣሪዎቹ ያመለጡት ቆጠራ እየተከናወነ ባለበት ሰዓት ሮጠው በአጥር ዘልለው ነው " - ኮማንደር ጠይባ መሐመድ

ትላንት ሀሙስ አመሻሽ ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ስር ከሚገኘው የአሶሳ ማረሚያ ቤት 17 ተጠርጣሪዎች ማምለጣቸውን የዞኑ ማረሚያ ቤት መምሪያ አሳውቋል።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ጠይባ መሐመድ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል ፤ ካመለጡት ተጠርጣሪዎች ጋር አብረው ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉ 2 እስረኞች መያዛቸውን ገልፀዋል።

ከማረሚያ ቤቱ ያመለጡት ግለሰቦች " በወቅታዊ ሁኔታ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት " ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።

ካመለጡት ውስጥ የተወሰኑት ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ኮማንደር ጠይባ ተጠርጣሪዎቹ ያመለጡት " ቆጠራ እየተከናወነ ባለበት ሰዓት ሮጠው በአጥር ዘልለው " ነው ያሉ ሲሆን ታሳሪዎቹን ለመያዝ የሞከረ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ጉዳት እንደደረሰበት ገልፀዋል።

" ተከትሏቸው የሮጠ አባል በዱላ ተመትቶ ሲወድቅ፤ መሳሪያው ተነጥቆ አንድ መሳሪያ ይዘው ሄደዋል” ሲሉ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አስረድተወል።

በወቅቱ ተጠርጣሪዎቹን ለማስቆም የሞከረው የማረሚያ ቤቱ አባል በስለት ሶስት ቦታዎች ላይ መዋጋቱን እና አሁን በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ኮማንደር ጠይባ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የዞኑ ማረሚያ ቤት ክትትል እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

ከዚሁ ማረሚያ ቤት ከሶስት ወር በፊት የቀድሞው የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ መሪ አቶ አብዱልዋሀብ መሀዲ በተመሳሳይ ሁኔታ ማምለጡ ይታወሳል።

የአሁኑ የእስረኞች ማምለጥ ከአቶ አብዱልዋሀብ ጋር ግንኙነት "ይኑረው አይኑረው እንደማይታወቅ" ኮማንደር ጠይባ መሐመድ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia
#ብርሃን

ብርሃን ሞባይል ባንኪንግ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ምቾታቸው ሳይጓደል በስማርት ወይም በመደበኛ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው *881# ላይ በመደወል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ነው፡፡

Follow us on
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ያግዛል የተባለ ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ የተባለ ተቋም ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ማስፋፊያ (FSD Ethiopia) ለመንግሥት እና ለግሉ ፋይናንስ ዘርፍ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣል ተብሏል።

ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ተደራሽነት ያላቸው፣ አካታች እና ዘላቂ የሆኑ የፋይናንስ ገበያዎችን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት የሚሠራ የልማት ኤጀንሲ ነው፡፡

አዲሱ ተቋሙ መንግሥት የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት አካታች መሆኑን ለማረጋገጥ እና የዕድገት ግቦችን ለማስተባር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች የሚደግፍ ወሳኝ አጋር መሆኑን የኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ሽግግር አስተዋጽኦ ይኖረዋል ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ፤ መንግስት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የፋይናንስ አካታችነት፣ የካፒታል ገበያ ዕድገት እና የተቋማት አቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጥምረት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽንና በእንግሊዙ የውጭ የጋራ ብልጽግና አገሮች የልማት ቢሮ በገንዘብ የሚደገፈው ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ፤ የገበያ ሥርዓት ዘዴዎችን በመጠቀም የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopia