TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰሞነኛው የግብፅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዙሪያ :

#Djibouti

• የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡

- የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

- የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር የውይይቱ ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል።

 - የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሀሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል፡፡

#Kenya

• ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

- በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው።

- ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2021 በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ነው፡፡

- ከኬንያ በተጨማሪ ከሱዳን ፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋር ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡

#Sudan

• ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ ፣ የናይል ጠባቂዎች (Nile Protectors/ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#አልአይን

@tikvahethiopia
#Shebelle

ሸበሌ የምትሰኝ የኢትዮጵያ መርከብ ከ11 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ስኳርና ሩዝ ይዛ በርበራ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።

መርከቧ ከህንድ ሀገር የጫነችውን ስኳርና ሩዝ ይዛ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ድርሻ ባላት የበርበራ ወደበ እያራገፈች ነው።

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ታሪክ የኢትዮጵያ መርከቦች ወደ በርበራ ወደብ ጉዞ ሲያደርጉ ከ20 ዓመታት በኋላ ሸበሌ መርከብ ሁለተኛ ናት።

ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ ከ20 ዓመታት በኋላ ጊቤ መርከብ በበርበራ ወደብ የመጀመሪያ ጉዞ አድርጋ ነበር፤ በዚህ ጉዞም 11 ሺ 200 ሜትሪክ ቶን የፍጆታ ዕቃ ለሶማሌላንድ ገበያ አጓጉዛ ነበር።

NB : በበርበራ ወደብ፤ ዲ ፒ ወርልድ 51 በመቶ፣ ሶማሌላንድ 30 በመቶ እና ኢትዮጵያ ደግሞ 19 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል ።

#አልአይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ የኢትዮጵያ ተወካይ ምን አሉ ?

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፤ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለምክር ቤቱ ያብራሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሰት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ተኩስ አቁም አውጆ መውጣቱ በአካባቢው ለሰብአዊ እንቅቃሴ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ህወሓት ወደ ተኩስ አቁም የመምጣት ፍላጎት የላቸውም፤ ይባስ ብሎም ህጻናትን ወደ ውትድርና እያስገቡ ነው፤ ወላጆች ልጆቻውን ለውትድርና እንዲሰጡ እርዳታ እህልን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።

ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀለቸውን እንዲሁም በህወሓት ተግባር ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የግብርና ስራ መስራ እንዳልቻሉም አስረድተዋል።

ቡድኑ የእርዳታ እህሎች እንቅስቃሴን እያስተጓጎለ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ግብ ሰላም ነው፤ ነገር ግን ህወሓት በኢትዮጵያና በሰላም መካከል እንቅፋት ሆኖ ቆሟል ሲሉም ተናግረዋል።

ሁሉም አካል የህወሓት ቡድን ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ ያቀረቡት አማባሳደር ታዬ ፤ ሁሉም የም/ቤቱ አባላት እውነታ ላይ የተመሰረተ መረጃ ብቻ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በልዩነት ውስጥ አንደነትን መፍጠር የቻለች ሀገር ነች፤ አሁን በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ለውጥም መድሎን ሳይሆን አንድነትን ማጠናከር ላይ የሚሰራ ነው ብለዋል።

#አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO ➡️ የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አን ሊንዴ ሀገራቸው የNATO አባል እንድትሆን ማመልከቻ መፈራረማቸው ተነግሯል። ሚኒስትሯ የፈረመት የአባልነት ጥያቄ ማማልከቻ ከፊንላንድ የNATO ማመልከቻ ጋር አብሮ ይቀርባል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ➡️ ዛሬ የፊንላንድ ፓርላማ የNATO ወታደራዊ ጥምረት አባል ለመሆን የቀረበውን ሀሳብ በ188 ድምጽ…
#Update

#ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን NATOን ለመቀላቀል በይፋ የማመልከቻ ደብዳቤያቸውን ለNATO አስገብተዋል።

➡️ የNATO ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ፊንላንድ እና ስዊድን የዓለም ትልቁን ወታደራዊ ህብረት ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል። ዋና ፀሀፊው 2ቱ ሀገራት የNATO አባል ለመሆን ያቀረቡትን ጥያቄ በከፍተኛ ደስታ መቀበላቸውን ገልፀዋል።

➡️ ፊንላንድ እና ስዊድን የNATO ጥምረት አባል ለመሆን ያቀረቡት ማመልከቻ በ30ዎቹ አባል አገራት የሚታይ ሲሆን ሂደቱ ሁለት ሳምንታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተነግሯል። ቱርክ ሀገራቱን የአሸባሪዎች ማረፊያ ናቸው በማለት NATOን ለመቀላቀል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ደጋግማ መቃወሟ ይታወቃል።

➡️ ነገ ሀሙስ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የስውዲን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንት በዋይትሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፤ የ2ቱ ሀገራት መሪዎች NATOን ለመቀለቀል እያደረጉት ስለለው ሂደት ከባይደን ጋር ይወያያሉ ተብሏል። አሜሪካ ሀገረቱ የNATO አባል እንዲሆኑ ከፍተኛ ድጋፍን እየሰጠች ከምትገኝ ሀገር አንዷ ናት።

➡️ NATOን መቀላቀል በማሰቧ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሩስያ አሁንም ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን እያካሄደች ነው። ሩስያ
በዶኔትስክ እና ሉሃንስክ የምድር ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች መቀጠሏ ተነግሯል።

➡️ ሩስያ፤ ፊንላንድና ስዊድን NATO የሚቀላቀሉ ከሆነ አፀፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ እየዛተች ነው ይህን ተከትሎ ፊንላንዳውያን በገፍ ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየወሰዱ ነው። እንደ ዩክሬን ልንወረር እንችላል በሚል የሃገሪቱን ጦር በመቀላቀል በፈቃደኝነት ወታደራዊ ስልጠናዎች እየወሰዱ ይገኛሉ።

#አልጀዚራ #አፒ #አልአይን #ቲአርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

➡️ ፈረንሳይ ፣ ጣልያን እና ስፔን 85 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ዲፕሎማቶቹ ሀገራቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ተከሰው ሲሆን፤ ሩስያ ክሱ ሀሰት ነው ብላለች፤ የዩክሬን ጦርነት ከጀምረ ጊዜ አንስቶ 300 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከተለያዩ ሀገራት ተባረዋል።

➡️ ሩስያ ዛሬ የስፔን እና የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባረረች። እስካሁን 27 የስፔን፣ 34 የፈረንሳይ ያባረረች ሲሆን 24 የጣልያን ዲፕሎማቶችን ልታባርር እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የNATO አባላት ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ህብረቱ አባልነት እንዳይገቡ ያደረባትን ስጋት እንዲያከብሩ ጠየቀዋል። ኤርዶጋን ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ሀገር እንዲሆኑ ሀገራቸው ድጋፏን እንደማትሰጥ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

➡️ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ቆሟል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድሩ መደናቀፍ አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ነው።

➡️ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የፊንላንድ እና ስዊድን ለNATO አባልነት ያቀረሹትን ታሪካዊ ያሉትን ማመልከቻ ባደስታ እንደሚቀበሉትና አጥብቀው እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ባወጡት ተግለጫ ከUS ኮንግረስ እና ከNATO አጋሮች ጋር በመሆን በፍጥነት ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ጠንካራው የመከላከያ ህብረት (NATO) ለማምጣት እሰራለሁ ብለዋል።

➡️ ፊንላንድ NATO ለመቀላቀል ባሳለፈችው ውሳኔ ላይ የሩሲያ ምላሽ ድንገተኛ ቢሆንም እርምጃዎቹ ግን ወታደራዊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

#አልጀዚራ #ኤኤፍፒ #ዘኪየቭ_ኢንዲፔንደንት #አልአይን

@tikvahethiopia
" የማህበራዊ ሚዲያው ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል " - ቮልከር ተርክ

ነገ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 የዓለም አቀፍ የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን ይከበራል።

ቀኑን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የጥላቻ ንግግርና አደገኛ መልዕክቶችን " ሰፊ ስርጭት " መከላከልን ጨምሮ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ቀኑን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቮልከር ተርክ ፦

" ትልቅ ግብዓት ያለው ጥረት ዓለምን ከመከራ ሊያጸዳው ይችላል።

የጥላቻ መስፋፋት መለያየትን ለመዝራት፣ ለማፍረስ እና ከትክክለኛ ጉዳዮች ለማዘናጋት በሚፈልጉ አካላት እንደሚሰራጭ እናውቃለን።

የማህበራዊ ሚዲያው በተለይም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል።

ጥላቻ ትምክህተኝነትን ፣ አድልዎንና አመጽን ያነሳሳል፤ ዓለማችንን ከጥላቻ የሚያጸዳው ጥይት፣ ማብሪያ ማጥፊያ የለውም።ነገር ግን የታለሙ እርምጃዎች ላይ ቢሰራ የጥላቻ ንግግሮችን ስርጭት መገደብ እና የሚያሰራጩትን ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል።

በተጨማሪ ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ለሚሰሩት እና ላልሰሩ ነገር ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ጥላቻን የሚያቋርጡ አውታረ መረቦችን መገንባት እና ድምጾችን ማጉላት አለብን። ለአብነትም የኃይማኖት መሪዎች ለጥላቻ እና ለአመጽ ማነሳሳት ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ አንዱ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ በጋዜጠኞች እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ያለአግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉት ከጥላቻ ንግግር ጋር የተገናኙ ህጎች መስፋፋታቸውም የጥላቻ ንግግርን ከማስፋፋት ባልተናነሰ ጉዳት ያለው ነው። "

Credit : #አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

- " ችግሩ የተከሰተው አንድ ሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስህተት በመፈጠሩ ነው። የተፈጠረው ስህተት ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቶ ነበር። "

- " የሲስተም ማሻሻያው የተተገበረው አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር። ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ችግር እንዳለ ሊለይ ችሏል። ይህን ተከትሎም አንዳንድ የተጠረጠሩ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ይህም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ችግሩ ስላልቆመ ሁሉም የዲጂታል ባንክ ስርዓቶች እንዲቋረጡ ተደርጎ ነበር። "

- " ባንኩ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተካሂዷን። ሌሊቱን ሙሉ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበረባቸው የባንክ ሂሳቦች በሙሉ እስኪጣራ ድረስ #እንዲታገድ ተደርጓል። "

- " በቀጣይ ከፍተኛ እና ያልተገባ ግብይት የፈጸሙ አካላትን እየለየን ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራል። "

- " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንጀሉ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸው አሳዝኖናል። በየአካባቢው ያሉ የዲስትሪክት ኃፊዎች በየአካባው ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ #እንዲመልሱ እየተደረገ ነው። "

- " ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው። የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ እና ያስከተለውን ጉዳትም ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል። "

- " ባንኩ ላይ የደረሰው ጉዳት ባንኩ ካለው ሀበት እና አቅም አንጻር የጎላ ተጽእኖ የለውም፤ ከደንበኞች ሂሳብ ጋርም አይገናኝም። " #አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል። ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል። 4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። የሩሲያ…
#ሩስያ

" ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትላንትና የሽብር ጥቃት በኃላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ነገ መጋቢት 15 በመላው ሩሲያ የሀዘን ቀን እንደሚሆን ተናግረዋል። " የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይዘከሩበታል " ብለዋል።

አሁን ላይ በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ሌላ የጅምላ ግድያ እንዳይፈጸም የጸጥታ ኃሎች ሰፊ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

" በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፈ እና ያገዛቸው የትኛውም አካል ለህግ ይቅርባል " ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ 4 ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሊያመልጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

" አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዩክሬን በኩል ሽብርተኞች ለማስመለጥ የሚያስችል መንገድ በድንበር በኩል ተዘጋጅቶ እንደነበረ ነው "  ብለዋል።

" ሩሲያ በዚህ የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት ለይታ ትቀጣለች " ያሉት ፑቲን፤ " ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው፤ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ እና ተስፋ የላቸውም " ሲሉ ዝተዋል። #አልአይን

@tikvahethiopia