TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ብርጋዴር_ጄነራል_ተፈራ_ማሞ

የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከትላንት ጀምሮ የት እና በምን ሁኔታ እንዳሉ ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ ስለነበራቸው ነበር ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው አልተመለሱም።

ተደጋግሞ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደወልም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ያሉበትንም ፤ ሆነ በማን እንደተወሰዱ ማረጋገጥ አልተቻለም።

የብርጋዴር ጄነራሉ ያሉበት አለመታወቅን ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በየአካባቢው የታፈኑ እና የታሰሩ የፋኖ አባላት በአስቸኳይ ይልቀቁ ሲሉ ፅፈዋል።

ዶ/ር ደሳለኝ ፤ የዜጎች እስር እገታ፣ መሰወር እጅግ አሳሳቢ እና በአስቸኳይ መቆም ያለበት ድርጊት ነው ሲሉ አሳስበዋል።

@Tikvahethiopia
#AmharaRegion #እንድታውቁት

ከዛሬ ግንቦት 9 ጀምሮ በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ይካሄዳል።

ይኸው የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በክልሉ ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው ባሉ የምዝገባ ማዕከላት መሳሪያውን ማስመዝገብ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምዝገባው የአማራን ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ዛሬ የዓለም የደም ግፊት ሕመም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው፡፡

በሽታው ምንም አይነት የህመም #ምልክት_ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል።

በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ብዛትድምጽ አልባው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል።

የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል።

ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ሆኖም ህሙማኑ በአብዛኛው የሚከተሉት ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል፡፡
➡️ የራስ ምታት
➡️ የአይን ብዥታ
➡️ ራስ ማዞር
➡️ ደረት ላይ የሚሰማ ህመም

መልዕክቱን አዘጋጅቶ ያሰራጨው ፦ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ነው።

#የደም_ግፊትዎን_በየጊዜው_ይለኩ !

#worldhypertensionday17may #hypertension
#WorldHypertensionDay

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌ ምን አሉ ?

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአዲስ አበባ ከቤታቸው እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም።

ይህን ተከትሎ ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠቱ ቃል የሚከተለውን ብለዋል ፦

" ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ/ም ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጣው ከጓደኛው (አቶ ዮሐንስ ቧያለው) ጋር ቀጠሮ እንደነበረው ገልጾ ነው።

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤት አልተመለሰም ደጋግመን ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም።

ከጄኔራል ተፈራ ጋር የተገናኙት ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረውናል።

ከዚያ በኋላ ግን የደረሰበትን ማወቅ አልቻልንም።

ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ብንጠይቅም በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ ገልፀውልናል።

በአሁኑ ሰዓት ሊኖርበት ይችላል ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋ ቀጥለናል።

ባለቤቴ የስኳር ሕመምተኛ ነው ፤ የታዘዘለትን መድኃኒት እየወሰደ ነበር ፤ መድኃኒቱን ካልወሰደ ይታመማል ይህም ስጋት ውስጥ ከቶናል።

ከሚኖርበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጣው በእግሩ ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ ነበር።

እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን የጤናው ሁኔታ ነው። "

#ብርጋዴር_ጄነራል_ተፈራ_ማሞ

@tikvahethiopia
#Assosa

ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#Wecare

በህፃናት ላይ የሚታዩ አስጊ የጤና ምልክቶች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ።

የ WeCare ET ሕክምና መተግበሪያ ሥመጥር ስፔሻሊስት ሐኪሞችን ባሉበት ቦታ ሆነው ለማማከር የሚያስችል መተግበሪያ ነው።

መተግበሪያውን ለመጫን ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ለበለጠ መረጃ 9394 ላይ ይደውሉልን።
መረጃዎችን ለማግኘት wecare.et ን ይጎብኙ
Wecare Et social medias

📌 Telegram: https://publielectoral.lat/WeCareET
#selamdoctor #wecareet
#Update

#ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO

➡️ የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አን ሊንዴ ሀገራቸው የNATO አባል እንድትሆን ማመልከቻ መፈራረማቸው ተነግሯል። ሚኒስትሯ የፈረመት የአባልነት ጥያቄ ማማልከቻ ከፊንላንድ የNATO ማመልከቻ ጋር አብሮ ይቀርባል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

➡️ ዛሬ የፊንላንድ ፓርላማ የNATO ወታደራዊ ጥምረት አባል ለመሆን የቀረበውን ሀሳብ በ188 ድምጽ በስምንት ተቃውሞ አፅድቋል።

➡️ ፊንላንድ ለNATO አባልነት ማማልከቻ ልታቀር መሆኑን ተከትሎ ሩሲያ የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ አስወንጫፊ ሚሳየሎችን ወደ ፊንላንድ ድንበር ማስጠጋቷ ተነግሯል ፤ ወደ ፊንላንድ ድንበር ያስጠጋ የኢስካንደር ሚሳየሎች እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ ስዊድን ለNATO አባልነት ጥያቄ ለማቅረብ ከውሳኔ ላይ መድረሷን ተከትሎ ሩሲያ በብሔራዊ ደህንነቷ ላይ የሚደርሰውን ስጋት ለመቅረፍ ወታደራዊ-ቴክኒካል እና ሌሎች የምላሽ እርምጃዎችን እንደምትወስድ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በድጋሚ ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ለመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ አረጋግጠዋል። ሀገራቱ ወደ አንካራ የአግባቢ ልዑክ ይልካሉ እየተባለ ሲሆን ኤርዶጋን ግን " አቋማችን ግልፅ ነው ወደ አንካራ ልኡክ በመላክ ባትለፉ እኛንም ባታስቸግሩን ይሻላችኃል " ብለዋቸዋል።

ቱርክ ፤ ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ለመሆን የሚያደርፉትን እንቅስቃሴ ለምንድነው የማትደግፈው ? ይህን ያንብቡ ፦ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/70164?single

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሲጂቲኤን ፣ ቴሌግራፍ፣ ኤፒ ፣ ዬል ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በመጀመሪያ ዕጣ 7 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የልዩ -2 ሎተሪ አጣ ዛሬ ወጥቷል።

የልዩ -2 ሎተሪ ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆኗል።

1ኛ. 7,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0759162

2ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0134613

3ኛ.1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0299997

4ኛ. 400,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1037132

5ኛ. 100,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0530065

6ኛ. 50,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0516747

7ኛ. 30,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 1185534

8ኛ. 12 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 01329

9ኛ.12 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 31649

10ኛ. 12 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 400 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 02455

11ኛ. 120 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 4335

12ኛ. 120 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 0652

13ኛ. 1,200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 768

14ኛ. 12,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 60 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 50

15ኛ. 120,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 40 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 6 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሀገር እንደ ልብስ አትበጣጠስም " - ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ

ዛሬ የ2014 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።

በዚሁ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ስለ #ሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው ፥ " በአሁን ጊዜ በቤተክርስቲያናችን በኩል ያለው ከሚመጣው መከራ የተነሳ ምዕመናን ከመሞታቸው ፣ ካህናት ሰማዕት ከመሆናቸው የተነሳ ቤተክርስቲያኒቱ መከረኛ ሆናለች ፤ ድሮም መከረኛ ናት በእርግጥ የሰማዕታት ቤት ናት ፤ ስለዚህም ተግተን ልንፀልይ ሰላምንም ልናስገኝ ይገባል " ብለዋል።

" ሁሉ የተጣላበት ዘመን ነው " ያሉት ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ " በሰዎች ዘንድ ፣ በሁሉ ዘንድ ሰላም የለም " ሲሉ ገልፀዋል።

" አንድ አካል ፣ አንድ ህዝብ ፣ አንድ ህብረ አባል፣ አንድ ህብረ ሀገር የሆነች ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ እርስ በእርሱ መጣላት ፣ መጋጨት ፣ መጋደል እየታየ ነው " ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ " ይህችን ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያን ለመከፋፈል የሚሞክሩ የተወገዙ ይሁኑ ፤ ለምንድነው ይሄ የሚሆነው ? ሀገር አትከፈልም፣ ሀገር እንደ ልብስ አትበጣጠስም ፥ ይህኔ ሁሉ ያርቅልን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችን በጥበቡ በቅዱስ ፍቃዱ ያርቅልን " ሲሉ መልዕክታቸውን አስታላልፈዋልን።

ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በነበረው የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር ላይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተገኝተው ነበር።

ፎቶ ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia