TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SpecialOlympics

የሚዲያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ስፔሻል ኦሎምፒክስን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ተሳታፊ የሚያደርገው ስፔሻል ኦሎምፒክስን የሚድያ ባለሙያዎች እንዲያዙ ጥሪ የቀረበው ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አዳራሽ ለሚድያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው።

የስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንደገለፁት በሀገራችን ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር የሚኖሩ በርካታ ልጆች ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንዳይቀሩና ያላቸውን ልዩ ተሰጥኦ በአደባባይ እንዲያሳዩ ስፔሻል ኦሎምፒክስ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ የሚድያና የኮምንኬሽን ባለሙያዎች ለጉዳዩ ሰፊ የሚድያ ሽፋን በመስጠት አጋር እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

በቀዳማዊት እመቤት ክብርት ዝናሽ ታያቸውና አጋር አካላት አነሳሽነት በቅርቡ የተመሰረተው ስፔሻል ኦሎምፒክስ ኢትዮጵያ ፤ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ኢትዮጵያን በመወከል በዱባይና ግብፅ በተደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች የወርቅና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንዲሆኑ አስችሏል ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
" የባንክ፣ የመብራት እና የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች ወደነበሩበት ይመለሱ " - አቶኒዮ ጉተሬዝ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል ፤ የትግራይ ባለስልጣናትም ግጭት ለማቆም ያሳዩትን ቁርጠኝነትን አድንቀዋል።

ጉተሬዝ ፤ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ አስከፊ ስቃይ አስከትሏል ብለዋል።

አሁን የታዩት አዎንታዊ ለውጦች በፍጥነት ወደ መሬት ወርደው መተርጎም አለባቸው ሲሉም ገልፀዋል።

ዋና ጸሃፊው ፤ በትግራይ ህዝባዊ አገልግሎት ማለትም የባንክ፣ የመብራት እና የቴሌኮሚኒኬሽን ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም አካላት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች በሙሉ ሰብአዊ እርዳታዎች ያለመስተጓጎል እንዲገባ እንዲያመቻቹ አሳስበዋል።

ጉረቴዝ ፤ ሁሉም ወገኖች አሁን በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረት ግጭት የማቆም ውሳኔያቸውን ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ማሸጋገር አለባቸው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray #Amhara #Afar #Oromia

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች በጸጥታ ችግር እና በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚቀርብ ሰብአዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም የሚውል 134,884,285 ብር መርሃግብር አስጀምራለች።

ይኸው መርሃግብር ለ227,255 ዜጎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን በአፋጣኝ ለማድረስ የሚውል ሲሆን ከእነዚህም መካከል 9,690 ህፃናት 36,199 ተፈናቃዮች እና ተቀባይ ማህበረሰብ ይገኙበታል።

ፕሮጀክቱ የሚከናወነው በቤተክርስቲያኗ የልማት ኮሚሽን 4 ሀገረስብከቶች አማካኝነት በተጠቀሱት 4 ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 7 ዞኖች እና 11 ወረዳዎች ነው።

ገንዘቡን ለማሰባሰብ ድጋፍ ያደረጉት የካሪታስ ዓለም አቀፍ አባል ድርጅቶች እና ሌሎች የቤተክርስቲያን አጋር ድርጅቶች መሆናቸው ተገልፆልናል።

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ ም/ቤት አባሉ ከአንድ አፍሪካዊ ባለሀብት ገንዘብ መቀበላቸው ተረጋገጠ።

ከአንድ አፍሪካዊ ቢሊየነር የገንዘብ ድጋፍ ስለማግኘታቸው ዋሽተዋል የተባሉ የአሜሪካ ም/ቤት አባል ከእንደራሴነታቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ ተነገረ።

ጄፍ ፎርተንቤሪ የተባሉት የኔብራስከካ ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ፣ ከስኬታማው ናይጄሪያዊ የንግድ ሰው ጊልበርት ቻጉሪ ሕገወጥ የገንዘብ ድጋፍ ስለመቀበላቸው ለFBI መዋሸታቸውን የፌደራል ዳኞች እንደደረሱበት ቢቢሲ ፅፏል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በ3 ጥፋቶች አስከ 15 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ለፈረድባቸው ይችላል ተብሏል።

ይህ ጉዳይ የውጭ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ሊያሳድሩ የሚችሉትን ጫና በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረውን ክርክር መልሶ ቀስቅሶታል።

ምንም እንኳን የውጭ ዜጎች ለፖለቲካ ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ባይፈቀድላቸውም የ75 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ቢሊየነር በርካታ የገንዘብ ስጦታዎችን ማበርከታቸው ይነገራል።

ግለሰቡ እኤአ በ2016 ላይ አሁን ጥፋተኛ ሆነው ለተገኙት የምክር ቤት አባል ጄፍ ፎርተንቤሪ በበሌሎች ለጋሾች በኩል በሕገወጥ መንገድ የ30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብሏል።

እንደራሴው 30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የሚገልጽ የተቀረጸ የስልክ ውይይት የተገኘ ቢሆንም፣ ለFBI መርማሪዎች ግን ስለገንዘቡ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ክደዋል።

ሐሙስ በሎስ አንጀለስ ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች ፣ ጄፍ ፎርተንቤሪን ሐሰተኛ ቃል በመስጠትና እውነትን ከፌደራል መርማሪዎች በመደበቅ ጥፋተኛ ብለዋቸዋል።

የምክር ቤት አባሉ ላይ የቅጣት ውሳኔ የሚሰጠው ከወራት በኋላ ሰኔ ላይ ሲሆን፣ አስከዚው ድረስ ግን እንደራሴው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል። በዚህም እስካሁን ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዱ ፓርቲዎች ብልጽግና ፣ ህዳሴ ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ፣ ጋህነን መሆናቸውን አመልክቷል። እንደ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በጊዜ ገደቡ መሰረት ቀን ያሳወቁ 3 ፓርቲዎች አሉ። ቦርድ 12 ፓርቲዎች…
#OFC

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

የፓርቲው ጉባኤ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ሲሆን በተለያዩ የፓርቲው ውስጣዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በዛሬው የፓርቲው ጉባኤ መክፈቻ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ ጀዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እና አባላቶች ተገኝተዋል።

የጉባኤውን ሂደት ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

ፎቶ ፦ ኡቡንቲ ሚዲያ እና Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#Tigray

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆመ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ከመንግስት ውሳኔ በኃላም ከትግራይ ክልል በኩል በጎ ምላሽ መኖሩ ለበርካታ ወራት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እና ከክልሉ ውጭ ላሉ ቤተሰቦች በጎ ተስፋን ያጫረ እንደሆነ ይታመናል።

ነገር ግን ከዚህ በፊት የመከላከያ ኃይል ባለበት ፀንቶ ይቆያል ከሚለው ውሳኔ በምን ይለያል የሚል ጥያቄ የሚነሳ ሲሆን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፦

"የመጀመሪያው ወደ ትግራይ አካባቢ አልገባም አለ እንጂ የተለያዩ ትንኮሳዎች ካሉ አፀፋ አልመልስም አላለም።

የተለያዩ አካባቢዎች ላይ አደጋዎች ሊኖሩ ይችላሉ ብሎ በሰጋ በየትኛውም ጊዜ እርምጃ ከመውሰድ የሚያግድ ነገር አልነበረም።

የአሁኑ ግን ለበረራዎች ደህንነት ሲባል፣ የህወሓት ሚሊሻም በተለያየ መልክ ስጋት ውስጥ ገብቶ መንገዱን እንዳይዘጋው የትኛውም አይነት ግጭት ከማድረግ እቆጠባለሁ ነው ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

ከውሳኔው በኃላ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል የሚደረግ ጥረት በተመለከተ ዶ/ር ለገሰ፥

"...በሳምንት እስከ3 ጊዜ ይካሄድ የነበረ በረራ አሁን መጠኑን የመጨመር አንዱ ነው።

ሌላው ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የገንዘብ ፍሰት ጋር የተያያዘ የታገዱ ነበሩ እነሱ በተወሰነ ደረጃ የመጨመር እንቅስቃሴ ነው። ገደቦች ነበሩ ገደቦቹን የማሻሻል ስራ ይሰራል" ብለዋል።

ሌላው፥ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታው መቀላጠፍ የህወሓት ኃይሎች በጉልበት ከያዛቸው አካባቢዎች ለቀው እንደሚወጡና ዋናውን የ " አብዓላ ኮሪደር " መስመርን እንዲከፍቱ ጠይቋል፤ ከያዙት ቦታ ባይለቁ ለሚለው ጥያቄ ዶ/ር ለገሰ " እሱን በሂደት ብናየው ይሻላል ከአሁኑ መገመት ተገቢ አይሆንም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
🌧 ቦረና 🌧

ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ አስከፊ ድርቅ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ጥሏል።

ይህም ነዋሪዎች ላይ ደስታን ፈጥሯል።

ከሰሞኑን በእነዚህ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ የሚያሳይ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ይገኛሉ።

ቃላቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል የሰጡት የቦረና ዞን ኤልዋዬ ወረዳ ነዋሪው አባ ሾባ ሞሉ ዝናብ በማግኘታቸው እጅግ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ዝናብ ከረቡዕ ማታ ጀምሮ አንደዘነበ የተናገሩት አባ ሾባ ሁሉም ቦታ ተመሳሳይ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ለኤልዋዬ እና ያቤሎ ግን በጣም መልካም የሚባል ቀን እንደነበር ገልፀዋል።

የቦረና ማህበረሰብ ዝናብ በማጣት በድርቅ እንዳይቸገር አንደሚፈራው ሁሉ ከድርቅ በኃላ ዝናብ ሲገኝም የሚመጣውን ጎርፍ ትኩረት ሰጥቶ ይከታተላል። ለምን ? ከተባለ ከባዱ ዝናብ በድርቅ የተጎዱ ከብቶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤ ሊገላቸው ይችላል በሚል ነው።

ለዚህም ነው " ፎሮሪ ሮቢ ዋቅ / 'forori roobi waaq' " የሚለው፣ ይህ ማለት " ያልበዛ ፣ያላነሰ አድርገህ አዝንብልን " እንደ ማለት ነው።

አባ ሾባም ያሉት ይህንኑ ነው ፤ " ይህ ዝናብ ከባድ ሆኖ ዘንቦ ከብቶችን አልጎዳም። ቀስ እያለ ነበር የዘነበው። አሁንም እየዘነበ ነው ። ጥሩ ደመናም ውጥቷል "

ነገር ግን ከአንድ ወር በፊት አንድ ቀን ብቻ የጣለው ዝናብ ከብቶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶ ነበር ። በጎርፉ ወደ 13,000 ከብቶች አንዳለቁ ተገልጿል። በሰው ህይወት ላይም ጉዳት አድርሶ ነበር።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BORANA-03-26

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የብራዚል መንግስት በ" ኮቪድ - 19 ወረርሽኝ " ወቅት በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ብራዚልን አግዘዋል ላላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አመራሮች በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሚሰጠውን ከፍተኛ የሪዮ ብራንኮ ሜዳይ አበረክቷል።

የአየር መንገዱ የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከፍተኛውን የክብር ማእረግ ሲበረከትላቸው በብራዚል እና በደቡብ አሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግሩም አበበን ጨምሮ ሁለት የአየር መንገዱ የስራ ሀላፊዎች ደግሞ ሜዳዮ ተበርክቶላቸዋል።

የክብር እና የእውቅና ስነ-ስርዓቱ አዲስ አበባ በሚገኘው በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ሊዊ ኤድዋርዶ መኖሪያ የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና መፍቲን ጨምሮ በርካታ የክብር እንግዶች ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ ዋፋ ማርኬቲንግ

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ። የፓርቲው ጉባኤ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ሲሆን በተለያዩ የፓርቲው ውስጣዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። በዛሬው የፓርቲው ጉባኤ መክፈቻ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ ጀዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እና አባላቶች…
#Update

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 18 የሚያካሂደውን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምራል።

በዛሬው ዕለት በነበረው የጉባኤው ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና ንግግር አድርገዋል።

ፕ/ር መረራ በንግግራቸው " በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የኦሮሞ ወጣት (ቄሮና ቀሬዎች ) የደም ዋጋ ከፍሎበታል። ብዙዎችን አጥተንበታል " ብለዋል።

" ለውጡ መጥቶ አዲስ መንግስት ተመስርቶ ወንድሞቻችን ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ሲገቡ ትንሽ ስራቸው አሳስቦኝ በግፋ በለው ባይሄዱ አልኩኝ " ያሉት ፕ/ር መረራ " በዚያ በግፋ በለው መንገድ በመሄዳቸው በእነዚህ አራት ዓመታት ሀገራችንንም ሆነ ህዝባችንን ብሎም ፓርቲያችንን ከፍተኛ ዋጋ አስከፍለዋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከምንም በላይ ደግሞ ምርጫውን ያለ ብሄራዊ መግባባት ብናደርግ ሰላም እና መረጋጋትን እድገት እና ብልፅግናን ብሎም ዴሞክራሲን አያመጣም በፈጣሪ ስም ወደ ብሄራዊ መግባባት እንሂድ ብለን ጠይቀን ነበር " ብለዋል።

" ነገር ግን በእንቢተኝነት ተሄደበት ውጤቱ ደግሞ የምታዩት ነው ፤ ኃይል በእጃቸው ያለው አይሆንም እኛ በቀድሞ ህግ መሰረት ነው የምንሄደው ብለው ምርጫ አካሄዱ ያ ደግሞ ጦርነት መዘዘ " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕ/ር መረራ " ጦርነቱ እንዳይጀመር ተማፅነናል " ያሉ ሲሆን " ከተጀመረም እንዳይቀጥል በተደጋጋሚ ነው የጠየቅነው አሁን ያ ሁሉ ህይወትና ንብረት ወድሞ ወደእርቅ ተመጥቷል " ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ ፤ 2014 ዓ/ም ላይ ከተካሄደው ምርጫ ተገፍተው መውጣታቸውን ገልፀው የፓርቲያቸው ጥያቄ የነበረው እውነተኛ የምርጫ ቦርድ ፣ ምህዳሩ የሰፋ የፖለቲካ ስርዓት እንደነበር አስረድተዋል።

የሃጫሉን ህልፈት ተከትሎ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች ወደ እስር ቤት መታጎራቸውን ፤ ከ206 ፅህፈት ቤቶችም 203ቱን መዘጋታቸውን ይህን ተከትሎ ተገፍተው ከምርጫ መውጣታቸውን ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፤ በትግራይ ምርጫ እንዳልተካሄደና በኦሮሚያም አንድ ፓርቲ ከራሱ ጋር መወዳደሩን አንስተዋል።

በመጨረሻ ፕሮፌሰር መረራ " ሰሞኑን መንግስት ከህወሓት ጋር ጦርነቱን አቁሞ ወደ ብሄራዊ መግባባት እንሂድ እየተባለ ነው የሚገኘው የኛዎቹስ ? ኦነግ ሸኔ የተባሉትን በአንድ ወር እናጠፋለን እያሉ ነው በጦርነቱ ማንም ያሸንፍ ማን የኦሮሞ ህዝብ ግን የከፋ ዋጋን ያስከፍለዋል በፈጣሪ ስም አስቡበት በሏቸው። " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፓርቲያቸው ለሰላም በሚደረገው ትግል፣ ለሀቀኛ ዴሞክራሲ በሚደረገው ትግል፣ ይሄን ሀገር ለመለወጥ እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ውስጥ የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 18 የሚያካሂደውን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምራል። በዛሬው ዕለት በነበረው የጉባኤው ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና ንግግር አድርገዋል። ፕ/ር መረራ በንግግራቸው " በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የኦሮሞ ወጣት (ቄሮና ቀሬዎች ) የደም ዋጋ ከፍሎበታል። ብዙዎችን አጥተንበታል…
#NewsAlert

የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ መረጠ።

አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ተመርጠዋል።

ፕ/ር መረራን ለሊቀመንበርነት የጠቆሟቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ሲሆኑ የጉባኤው አባላቶች ለሊቀመንበርነት እና ለተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርነት አቶ ጃዋር መሀመድን ቢጠቁሙም ጥቆማውን Decline ማድረጉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ የተካሄደ ሲሆን አቶ ጃዋር መሀመድ እና አቶ ሀምዛ አዳነ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው መመረጣቸውን ኡቡንቱ ቲቪ ከስፍራው ዘግቧል።

የምርጫ ሂደቱ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ የዘለቀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የሊቀመናብርት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት ዝርዝር ፦

👉 ፕ/ር መረራ ጉዲና (ሊቀመንበር)
👉 አቶ በቀለ ገርባ (ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር)
👉 አቶ ጃዋር መሀመድ (ምክትል ሊቀመንበር)
• አቶ ሙላቱ ገመቹ
• አቶ ጥሩነህ ገምታ
• አቶ ደጀኔ ጣፋ
• አቶ አንዋር ሳኒ
• አቶ ጉርሜሳ አያኖ
• አቶ ሀምዛ አዳነ
• አቶ ሞቲ ቤጊ
• ወ/ሮ ሂሮዋቅ ግርማ
• አቶ ሻቡዲን ሼክ ኑራ
• አቶ ፍቃዱ ባንጃ
• አቶ አማን ካኒሶ
• አቶ ሱልጣን ቃሲም (ከኦዳ ፓርቲ - ሊቀመንበር)
• አቶ ሞሀመድ አብደላ
• አቶ አስፋው አንጋሱ

@tikvahethiopia