TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍 የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ያናሷቸው ጥያቄዎች ምንድናቸው ? የካማሺ ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ዓለሙ በሽር  ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የዞኑ አስተዳደሮች ይሄ ጥያቄ በዞኑ የሚመለስ እንዳልሆነ አስረድተው፣ በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ንግግር በማድረግ መልስ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።…
#Kasmashi📍

የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ከዚህ በፊት እርቅ ለመፈፀም ካስቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች የትኞቹ ተሟሉ ?

👉 የታሰሩ ጉህዴን አመራሮች እንዲፈቱ ጠይቀው፤ በርካታ የታጠቂው ኃይሎች ከእስር ተፈተዋል፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር የታሰሩ የጉህዴን አመራሮች የካቲት 17 እንዲፈቱ አድርጓል። ከነዚህ ውስጥ የጉህዴን ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉደታ የሚገኙበት ሲሆን ከ20 ቀናት ገደማ በፊት ነው የተፈቱት። ባለፉት 2 ሳምንታት 400 ገደማ የፓርቲው አባላትም ከእስር መፈታታቸውን ጉህዴን አረጋግጧል።

👉 የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና ለሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆኑ ጠይቀው፤ አካባቢው ሰላም ከሆነ የክልሉ መንግስት ነዋሪዎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና በየትኛውም ቦታ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችል ለታጣቂዎቹ ገልጿል።

👉 በካማሺ እና መተከል ዞን ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም የሌሎች ክልል ልዩ ኃይሎች አካባቢዎቹን ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀው፤ ክልሉ የተጠቀሱት የጸጥታ ኃይሎች እንዲወጡ በቅድሚያ ሰላም መምጣት እንዳለበት ከብዙ ውይይት በኋላ ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል፤ ጉህዴን ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ውይይት አላደረግንም ብሏል፤ ከዕርቁ በኋላ በጉዳዩ ላይ ወይይት እንደሚደረግበት ገልጿል።

🔹 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጥቀው በየጫካው ያሉ ታጣቂዎች፤ ትጥቃቸውን ፈትተው የተሃድሶ ስልጠና የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ መምከር ከዕርቁ በኋላ የሚኖረው አንዱ ዋነኛ ጉዳይ ነው ብሏል። ጉህዴን በተመሳሳይ ከዕርቁ በኋላ ከክልሉ መንግስት ጋር የሚደረግ ውይይት አለ ያለ ሲሆን ታጣቂዎቹ ትጥቅ መቼ እንደሚፈቱ የሚወሰነው በውይይት ነው ብሏል። እስከዛ ግን ታጥቀው እንደሚቆዩ ገልጿል።

@tikvahethiopia